Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ጉራጌ የኬር፣ ኦገሬት ሕገ ኦሪት ሕዝብ

Post by Horus » 20 Jun 2020, 03:33

በጉራጌ ሕይወት እግዚአብሄር፣ ጎይታ፣ አላህ ከሚሉት ጽንሶች ቀጥሎ በሁሉም ጉራጌ ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምዕራብ እስከ ዛይ ምስራቅ ጉራጌ የጉራጌ ሙሉ ፍልስፍና፣ ባልህ፤ መርህ፣ ካልቸር፣ ኤቲክስ እና ሰነ ምግባር የኬር ወይም የኦገሬት ይባላል። በአማርኛ ይህን ጽንሰ ነገር በትንሹ የሚቀርቡ ቃላት ልክ መሆን፣ ፍትህ፣ ርትዕ፣ ስነምግባር፣ ስነ ስራ (ሰራ) ወይም ስርኣት፣ ሕግ (ራሱ ሴራ ሕግ ማለት ነው)። ስለዚህ በጉራጌ ማንኛውም ሕይወት ውስጥ ልክ፣ ትክክል፣ ሙሉ፣ ፍጹም፣ ሕጋዊ፣ መልካም ስኬታማ ወዘተ የሆነ ነገር ሁሉ ኬርነት (ኦገሬቶ) ይባላል። ለዚህ ነው ኬርነት የጉርጌ ኮስሞሎጂ ነው የሚባለው !!!




Last edited by Horus on 25 Jun 2020, 23:02, edited 4 times in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 30924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ጉራጌ የኬር፣ ኦገሬት ሕገ ኦሪት ሕዝብ

Post by Horus » 20 Jun 2020, 04:08

ኬሮ ማለት (በቀምጥ) ወይም ኦሪት ማለት (ሴማዊያንና ግሪኮች ከቀኝ ወደ ግራ ጽፈውት) አንድ ቃል ሲሆን የተፈለሰፈው በጥንታዊ ግብጾች ነው። እሱም የፍጥረት ሁሉ ሕግ ማለት ነው። ማንኛውም ነገር የተሰራበት ፍጥረቱ፣ ህጉ፣ በዛሬ አነጋገር ዲዛይኑ፣ ጽንሰ ሃሳቡ፣ ጽንሰ ነገሩ ማለት ነው። ሳይንስ ጂን ይለዋል ። ይህም ያንድ ነገር ትክክለኛ ምንነት ልክ፣ መለኪያ ማለት ነው። ነገሮች ሁሉ ትክክል፣ ራይት፣ እውነት፣ ኮሬክት ፣ ሃቅ የሚሆኑት ይህን የራሳቸው ፍጥረተ ሕግ ሲኖራቸው ብቻ ነው ። አልያ ቆማጣ፣ ሽባ፣ ጎደሎ፣ ያልተሟላ፣ ስንኩል ፍጥረት ይሆናሉ ። ይህ ለምሳሌ በኦርቶዶሽ እምነት ኦርቶ ወይም ርትዕ የሚባለው ነው ። በሳይንስም፣ በሁሉም ነገር በተሰራ በተፈጠረ ነገር ሁሉ የነገሩ ሴራ፣ የነገሩ ኬርነት መኖር አለበት ። ያ ከሌለ ነገሩ አይጸናም፣ አይቆምም፣ ህላዌም ሆነ እድገት አያገኝም ። ይህ ነው የኬር ሴራ ማለት፣ የጉራጌ ኦገሬት ካልቸር ማለት !!

Horus
Senior Member+
Posts: 30924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ጉራጌ የኬር፣ ኦገሬት ሕገ ኦሪት ሕዝብ

Post by Horus » 20 Jun 2020, 04:21


Horus
Senior Member+
Posts: 30924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ጉራጌ የኬር፣ ኦገሬት ሕገ ኦሪት ሕዝብ

Post by Horus » 20 Jun 2020, 04:34

ቴዲ አፍሮ

'ኬር ይላል ጉራጌ' (ያስተሰርያል) !!


Horus
Senior Member+
Posts: 30924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ጉራጌ የኬር፣ ኦገሬት ሕገ ኦሪት ሕዝብ

Post by Horus » 20 Jun 2020, 05:11

እስከ ዛሬ በደርስኩበት የቋንቋ ምርምር መሰረት በኦሪተ ሴራ አንድ የነበሩና ስማቸው ካንድ ቃል የሚቀዳ ሕዝቦች እንደርታ፣ አርጎባል፣ አደሬና ጉራጌ ናቸው ። ጥናቴ ይቀጥላል ። የ ዲ ኤን ኤ ቲክኖሎጂ የገባ ቀን ምርምሬን እንደ ሚያረጋግጥ ጥርጥር የለኝም ።

Horus
Senior Member+
Posts: 30924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ጉራጌ የኬር፣ ኦገሬት ሕገ ኦሪት ሕዝብ

Post by Horus » 20 Jun 2020, 20:08


Horus
Senior Member+
Posts: 30924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ጉራጌ የኬር፣ ኦገሬት ሕገ ኦሪት ሕዝብ

Post by Horus » 21 Jun 2020, 04:01


Horus
Senior Member+
Posts: 30924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ጉራጌ የኬር፣ ኦገሬት ሕገ ኦሪት ሕዝብ

Post by Horus » 21 Jun 2020, 17:17


Horus
Senior Member+
Posts: 30924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ጉራጌ የኬር፣ ኦገሬት ሕገ ኦሪት ሕዝብ

Post by Horus » 22 Jun 2020, 03:05

ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ እንዳሉት'

የጉራጌ የሕግ እና ያስረዳደር ሴራዎች (ሴራት/ሰርዓት) ሁሉም ተጽፈው ከዘመናዊ የወንጀርና የፍትሃ ብሄር ሕግጋት ጋት መነጣጠር አለባቸው።

ለምሳሌ፣

ቅጫ፤

(ቅጥ፣ እኩል፣ ጀስት) ማለት ሲሆን ቅጣት፣ መቀጮ፣ ቅጥነት፣ ጀስቲስ፣ እኩልነት ወይም አንድን ነገር እኩል አድርጎ መፍረድ ነው።

ተራ የጉራጌ ቃል ቅጥ (እኩል) ይባላል።

ቅጥ ያለው ማለት ቀጥ ያለ፣ ትክክል፣ ርቱዕ ማለት ነው። ቅጥ ያጣ ማለት አንጀስት፣ የተዛባ፣ ወንጀለኛ ማለት ነው ።

Horus
Senior Member+
Posts: 30924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ጉራጌ የኬር፣ ኦገሬት ሕገ ኦሪት ሕዝብ

Post by Horus » 22 Jun 2020, 04:35


በእኔ አስተያየት ጉራጌ በአስቸኳይ የሚፈልገው የመደራጀት አይነት የዜና ሚዲያ ብቻ ሳይሆን የእውቀት፣ የጥናት፣ የምርምር፣ የታሪክ፣ የባህል፣ የቋንቋ፣ የኤቲክስ እና የአርት ምርምር ተቋም ነው።

ጉራጌ ቢያንስ በአራት ግዙፍ መስኮች እውቀት መር ሳይንስ ገፍ የሆኑ ስራዎች ተጋርጠውበታል ።

ጉራጌ አንድነቱ የሰመረ ፣ ጠንካራ፣ የተረጋጋ፣ የሰከነ ሕዝብ መሆን ግድ ይለዋል ። ይህን አለ መሆን ወድቀት ነው። ያንድ ህዝብ ተቀደዳሚ አላማ ይህ ነው።

ጉራጌ ዴሞክራሳዊ፣ ነጻ፣ ፍትሃዊ፣ በግለሰብ ልዕልና፣ በሰው ልክ ክቡርነት፣ በጉራጌ ዴንጋ፣ በጉራጌ አርዴ ሁሉ ወንድማማችነት፣ ዘማችነት የረጋ ማህበረሰብ እድዲሆን ድግ ነው ። ይህን አለመሆን ውድቀት ነው። የጉራጌ ነፍሰ ህዋስ፣ የህልውናው ሁሉ ትርጉም የእያንዳንዱ ጉራጌ ሰብ ልዑልነት ስለሆነ ።

ጉራጌ የበለጸገ፣ ባለጸጋ፣ ሃብታም፣ የተማረ፣ ባለ ሳይንስ፣ ባለ ቴክኖሎጂ፣ ባለ እውቀት እና ጤነኛ፣ አካላዊ፣ አይምሮአዊ፣ ሳይኮሎጂአዊ፣ አስተሳሰባዊ ህይወቱ ጤና የሆነ ሕዝብ ሊሆን ግድ ነው። ድሃ ሕዝብ፣ ያልተማረ ሕዝብ፣ ቴክኖሎጂ የሌለው ሕዝብ፣ ጤነኛ ህይወት የሌለው ሕዝብ የወደቀ፣ የከሸፈ፣ ስኬት አልባ ደካማ ሕዝብ ስለሆነ ።

ጉራጌ ሲጀመርም ፈጣሪ ሕዝብ ነው። የጉራጌ ካልቸር የፈጠራ፣ የስራ፣ የፍልሰፋ፣ የኪነት፣ የስነት፣ ካልቸር ነው ። ጉራጌ ሲጀመርም ከተፈጥሮ ጋር በሰላም፣ በኬርነት የሚኖር ካልቸር ነው። ጉራጌ ጥልቅ መንፈሳዊ፣ ቸር ፣ ርዕታዊ፣ ትሁት፣ የሰከነ ካልቸር ያበለጸገ ሕዝብ ነው። ይህን ወድ መንፈሳዊ፣ ክሬቲቭ ካልቸር መጠበቁ ግድ ይላል።

ይህ ሁሉ እንዲሆን ጉራጌ ታሪኩን፣ ቋንቋውን፣ እምነቱን፣ እሴቱን፣ ባህሉን፣ የኢኮኖሚ ፣ የፖለቲካ፣ የሶሺያ፣ የካልቸር፣ የሳይንስ፣ የቴክኖሎጂ ምርምር፣ ግስጋሴና አቅጣቻ የሚቀድ አንድ ግዙፍ የመላ ጉራጌ ኢንስቲቲዩት ባስሸኳይ ማቆም ግድ ይለናል።

ትልቁ ቁም ነገር ዞን፣ ክልል፣ አገር ማምን አይደለም ። ዛሬ እነዚህን እጅግ ታሪካዊ ግቦች ላይ ስኬታማ መሆን ነው። ኬር ዬሁን !!


Last edited by Horus on 22 Jun 2020, 18:27, edited 1 time in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 30924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ጉራጌ የኬር፣ ኦገሬት ሕገ ኦሪት ሕዝብ

Post by Horus » 22 Jun 2020, 18:06


Horus
Senior Member+
Posts: 30924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ጉራጌ የኬር፣ ኦገሬት ሕገ ኦሪት ሕዝብ

Post by Horus » 25 Jun 2020, 23:01

Horus wrote:
22 Jun 2020, 18:06

Horus
Senior Member+
Posts: 30924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ጉራጌ የኬር፣ ኦገሬት ሕገ ኦሪት ሕዝብ

Post by Horus » 27 Jun 2020, 15:46

የጉራጌ ክልላዊ መንግስት ሲቆም የሚገዛው በጉራጌ ሴራ ሕግጋት መሰረት ነው ።

የብልጽግናና የኢዜማ አባልት ካሁኑ ይህን ተገንዘቡ ።

የጉራጌ ከፍተኛ ምክር ቤት የሚሆነው የጉራጌ ሴራ ጉባኤ ነው ። እነዚህ ያገር አባት የጉራጌ ባሊቆች ናቸው የመጨረሻው ወሳኝ ሚሆኑት ።

እያንዳንዱ የጉርጌ ማህበረ ሰቦች እነ የጆካ፣ እነ ጎርደና 16ቱ በሁሉ በውስጥ እየሰሩ ባገር ጉባኤና ከፈተኛ የፍርድ ጉዳይ በጉራጌ ሴራ ክንግሬስ ነው ሚሆኑ ።

ከዚህ ባለፈ የካድሬ ፣የክራይ ሰብሳቢ የጎሳ ንግድ በጉራጌ ምድር እንደ ማንፈቅድ ካሁኑ እንዲታወቅ ይሁን።

Horus
Senior Member+
Posts: 30924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ጉራጌ የኬር፣ ኦገሬት ሕገ ኦሪት ሕዝብ

Post by Horus » 27 Jun 2020, 19:49

ይህ አስገራሚ ጥንታዊ ባህል እኔ አገር ቤት ሳድግ በሰሜን ጉራጌ በሃዘን እና የልቅሶ ይዘቱ ሰው ሲሞት የሚደረግ ሙሾ ነበር/ነው ። ሴቶችሁ እጃቸውን አንስተው የሚያወዛውዙት 'ዋቡስ' ይባላል ፣በክስታኔኛ ። በጉራጌኛ ዋቡስ የሚለው ቃል ዋበጽህ፣ ታበጽህ የሚለው የግዕዙ ቃል ነው ። እሱም ማንሳት ማለት ነው። ኢትዮጵያ ታበጽህ (ታቦስህ) እደዊሃ አበ እግዚአብሄር ሲል ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ አግዚአብሄር ታነሳለች የሚለው ነው።

የወጣቶቹ ባህል ግን ከሙሾው ጋር ተለይቷል። በአቢይ ጽም፣ ስቅለትና ዳግማዊ ትንሳኤም የሚደረገው ክስታኔዎቹ የረሱት ይመስላል ። መመለስ አለበት ።


Post Reply