Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30898
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ጉራጌ ጉራዕ ከሚባል ያካለ ጉዛይ መንደር ፈለሰ ለምትሉ ስህተተኞች

Post by Horus » 30 May 2020, 01:48

እኔ ሆረስ እባላለሁ ። አለቃ ታየ ይህን ያሉት አለምንም እውቀትና ምርምር ነው ። አለቃ ታየ ጉራጌ አይደሉም። በጉራጌ አልኖሩም ። የጉራጌ ቋንቋ ሆነ፣ ባህል ሆነ ወይም ጥንታዊ እምነት ሆነ ሃይምኖት ቅንጣት የማያውቁ የመሰላቸው የጻፉ ሰውን ተከትለው ዘመናዊ ተብዬ የታሪክ ሰዎች ያንን ስህተት ሲያዳቅሉ ይሀው ዘመን ተቆጠረና ዘመነ ጎሳ ደርሰናል ። አንድ ነገር ልበላችሁ ።

ጉራጌ እጅግ ጥንታዊ የሴም ሕዝብ ስለሆነ በብዙ ብዙ የቋንቋ ዝርያዎች ከሁሉም የኢትዮጵያ ሴማዊ ሕዝብ ጋር የሚጋራቸው ነገሮች አሉ ። አንድ ምሳሌ ልስጣችሁ፤ ለምሳሌ ጤፍ በጉራጌኛ ጣፊ ይባላል። እንጀራ ጣቤታ (ጣፔታ) ይባላል። በኤርትራ ጣይታ የሚባል ይምሰለኛ ። ግን ፒታ (ፔታ) በሁሉን ቦታ እስከ ህንድ ድረስ ጠፍጣፋ ዳቦ ማለት ነው። ሌሎችም ብዙ ብዙ እንደዚህ ያሉ ግንኙነቶች አሉ ።

ነገር ግ ን የሁለት ሕዝቦች ታሪካዊም ሆነ የዘር ትስስር ለመመርመር የሚታዩ ነገሮች አሉ ። ያባት ስም፣ የናት ስም፣ የልጅ ስም፣ የምግብ ስም፣ የቤት ስም፣ የውሻ ስም፣ የድመት ስም፣ ወዘተ። እነዚህ ስሞች ሰው ሲፈልስ አይለወጡም፣ ከዘር ዘር ይቀጥላሉ ።
ለምሳሌ በጉራጌኛ፤
አባት = አቢ
እናት = ኧሚት (እማት)
እህት = ኧቲት
ወንድም = ዘሚ (ዘሞ)
ልጅ = ባይ (ወይም ዴንጋ)
ልጆች = ባዮች (አርዴዎች)
ወንድ ልጅ = ጎሽ (ገሚያ)
ሴት ልጅ = ገረድ
ምግብ = ጉንስ
እንጀራ = ጣቤታ
ቤት = ጌ
ድመት = አንጋቻ
ዉሃ = ዪጋ
ጠላ = ስከር
አይብ = ቃይሳ (ቄሳ)
ቅቤ = ቅብ
እንስራ = ሻማ
ምድጃ = ገርገት
ጸሃይ = ጨበር
ኮከብ = ኢምር
መሶብ = ሌማት
ወዘተ

ስለዚህ እነዚህ ቃላት በግድ አንድ መሆን አለባቸው ። አሁን በአካለ ጉዛይ ትግርኛ እነዚህን ስሞች ንገሩኝ !! ትክክል ነገር የሚገኘው እንደዚህ ነው !! ኬር ዬሁን !!!

simbe11
Member
Posts: 2087
Joined: 23 Feb 2013, 13:02
Location: Addis Ababa

Re: ጉራጌ ጉራዕ ከሚባል ያካለ ጉዛይ መንደር ፈለሰ ለምትሉ ስህተተኞች

Post by simbe11 » 30 May 2020, 02:08

አባት = አቢ =አቦይ
እናት = ኧሚት (እማት)=አደይ
እህት = ኧቲት = ሃፍተይ
ወንድም = ዘሚ (ዘሞ) = ሃወይ
ልጅ = ባይ (ወይም ዴንጋ) = ቆልዓ
ልጆች = ባዮች (አርዴዎች) = ቆልዑ
ወንድ ልጅ = ጎሽ (ገሚያ) = ወዲ
ሴት ልጅ = ገረድ = ጏል
ምግብ = ጉንስ = መግቢ
እንጀራ = ጣቤታ = እንጀራ/ጣይታ
ቤት = ጌ = ቤት/ገዛ
ድመት = አንጋቻ = ድሙ
ዉሃ = ዪጋ = ማይ
ጠላ = ስከር = ስዋ
አይብ = ቃይሳ (ቄሳ)
ቅቤ = ቅብ = ጠስሚ
እንስራ = ሻማ =
ምድጃ = ገርገት = ፈርኔሎ
ጸሃይ = ጨበር = ፀሃይ
ኮከብ = ኢምር =ኾኸብ
መሶብ = ሌማት
ወዘተ

sebdoyeley
Member+
Posts: 5507
Joined: 14 Feb 2020, 04:27

Re: ጉራጌ ጉራዕ ከሚባል ያካለ ጉዛይ መንደር ፈለሰ ለምትሉ ስህተተኞች

Post by sebdoyeley » 30 May 2020, 02:21

Horus wrote:
30 May 2020, 01:48
እኔ ሆረስ እባላለሁ ። አለቃ ታየ ይህን ያሉት አለምንም እውቀትና ምርምር ነው ። አለቃ ታየ ጉራጌ አይደሉም። በጉራጌ አልኖሩም ። የጉራጌ ቋንቋ ሆነ፣ ባህል ሆነ ወይም ጥንታዊ እምነት ሆነ ሃይምኖት ቅንጣት የማያውቁ የመሰላቸው የጻፉ ሰውን ተከትለው ዘመናዊ ተብዬ የታሪክ ሰዎች ያንን ስህተት ሲያዳቅሉ ይሀው ዘመን ተቆጠረና ዘመነ ጎሳ ደርሰናል ። አንድ ነገር ልበላችሁ ።

ጉራጌ እጅግ ጥንታዊ የሴም ሕዝብ ስለሆነ በብዙ ብዙ የቋንቋ ዝርያዎች ከሁሉም የኢትዮጵያ ሴማዊ ሕዝብ ጋር የሚጋራቸው ነገሮች አሉ ። አንድ ምሳሌ ልስጣችሁ፤ ለምሳሌ ጤፍ በጉራጌኛ ጣፊ ይባላል። እንጀራ ጣቤታ (ጣፔታ) ይባላል። በኤርትራ ጣይታ የሚባል ይምሰለኛ ። ግን ፒታ (ፔታ) በሁሉን ቦታ እስከ ህንድ ድረስ ጠፍጣፋ ዳቦ ማለት ነው። ሌሎችም ብዙ ብዙ እንደዚህ ያሉ ግንኙነቶች አሉ ።

ነገር ግ ን የሁለት ሕዝቦች ታሪካዊም ሆነ የዘር ትስስር ለመመርመር የሚታዩ ነገሮች አሉ ። ያባት ስም፣ የናት ስም፣ የልጅ ስም፣ የምግብ ስም፣ የቤት ስም፣ የውሻ ስም፣ የድመት ስም፣ ወዘተ። እነዚህ ስሞች ሰው ሲፈልስ አይለወጡም፣ ከዘር ዘር ይቀጥላሉ ።
ለምሳሌ በጉራጌኛ፤
አባት = አቢ
እናት = ኧሚት (እማት)
እህት = ኧቲት
ወንድም = ዘሚ (ዘሞ)
ልጅ = ባይ (ወይም ዴንጋ)
ልጆች = ባዮች (አርዴዎች)
ወንድ ልጅ = ጎሽ (ገሚያ)
ሴት ልጅ = ገረድ
ምግብ = ጉንስ
እንጀራ = ጣቤታ
ቤት = ጌ
ድመት = አንጋቻ
ዉሃ = ዪጋ
ጠላ = ስከር
አይብ = ቃይሳ (ቄሳ)
ቅቤ = ቅብ
እንስራ = ሻማ
ምድጃ = ገርገት
ጸሃይ = ጨበር
ኮከብ = ኢምር
መሶብ = ሌማት
ወዘተ

ስለዚህ እነዚህ ቃላት በግድ አንድ መሆን አለባቸው ። አሁን በአካለ ጉዛይ ትግርኛ እነዚህን ስሞች ንገሩኝ !! ትክክል ነገር የሚገኘው እንደዚህ ነው !! ኬር ዬሁን !!!
you guys mor close to Oromo Than to the North. but here in Eritrea we all came from all over the place othe Horn of Africa, like bilen Agew came some where from central Ethiopia, dembian came from Gonder area, people emmigrate for different reason and settle where we are now.

EPRDF
Member
Posts: 2162
Joined: 26 Jan 2010, 12:58

Re: ጉራጌ ጉራዕ ከሚባል ያካለ ጉዛይ መንደር ፈለሰ ለምትሉ ስህተተኞች

Post by EPRDF » 30 May 2020, 02:59

ወሄዋሬ ዋጆ Horus አቻምውሄ :mrgreen:

ጉራጌ ሲባል አስር በላይ ነገድ ያለው ብሄረሰብ ነው፣ ቋንቋቸውም አንድ ዓይነት አይደለም፣ አንዱ ከኣንዱ ጭራሽ ጉራግኛ በሚሉት ቋንቋ አይግባባም፣ ታዲያ እንዴትና ለምን በኣንድ ጉራጌ በሚል ቃል መጠርያ እንደሚጠቃለል ነው እኔ የማይገባኝ፣።

ስልጤ እኔ ጉራጌ አይደለሁም ብሎ ከተሰነባበተ ከርሞዋል፣ ወለኔም ጉራጌዎች ደሃና ሁኑ ለማለት በሂደት ላይ ነው ያም ብዙ አይገርምም ምክኒያቱም በቋንቋ አንድነት ያልተሳሰረ ሕዝብ፣ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ፣ በኣንድ ሰውሰራሽ (artificial) ስም ተጠቅልሎ (በጉራጌ) ስለማይዘልቅ ነው። እየታየ ያለውም ይሀው ነው።

ዋጆ፣ እስቲ ከዋሸሁ ወይ ከተሳሳትኩኝ፣ ምን ያህል የኣንዱ ጉራጌ ጎሳ ቋንቋ ከሌላው ከኣንድ ከሁለቱ የጎሳ ቋንቋ ጋር እንደሚቀራረብ ኣሳየንና prove me wrong። ወይንም አዚህ የዘረዘካቸውን (እርግጠኛ ነኝ የሶዶ ጉራጌ ቃላቶች ናቸው)ከሌላው ጉራግኛ የቋንቋ ቃላት ጋር ምን ያህል እንደሚዛመዱ አሳየን። አመሰግናለሁ።

justo
Member
Posts: 3178
Joined: 05 May 2013, 17:54

Re: ጉራጌ ጉራዕ ከሚባል ያካለ ጉዛይ መንደር ፈለሰ ለምትሉ ስህተተኞች

Post by justo » 30 May 2020, 04:08

Horus wrote:
30 May 2020, 01:48
እኔ ሆረስ እባላለሁ ። አለቃ ታየ ይህን ያሉት አለምንም እውቀትና ምርምር ነው ። አለቃ ታየ ጉራጌ አይደሉም። በጉራጌ አልኖሩም ። የጉራጌ ቋንቋ ሆነ፣ ባህል ሆነ ወይም ጥንታዊ እምነት ሆነ ሃይምኖት ቅንጣት የማያውቁ የመሰላቸው የጻፉ ሰውን ተከትለው ዘመናዊ ተብዬ የታሪክ ሰዎች ያንን ስህተት ሲያዳቅሉ ይሀው ዘመን ተቆጠረና ዘመነ ጎሳ ደርሰናል ። አንድ ነገር ልበላችሁ ።
ስለዚህ እነዚህ ቃላት በግድ አንድ መሆን አለባቸው ። አሁን በአካለ ጉዛይ ትግርኛ እነዚህን ስሞች ንገሩኝ !! ትክክል ነገር የሚገኘው እንደዚህ ነው !! ኬር ዬሁን !!!
Horus, you have picked a very interesting topic, I don't know about the origin of the gurage people, the topic itself is interesting and might generate interesting discussion if only stupid people stay away from it.

First off, language with all its evolution can be one of the many, and not the only basis of such things. You have also to look at the distance of time and how the language has evolved since that time. It would be interesting to compare the bilen of Eritrea with the Agew of Ethiopia, since they claim the same origin than is not older than 600 years.

To come back to your topic, the words you list show great affinity to Tigrigna in ways you wouldn't expect (but this can never prove that gurage and gurae are related to each other
ጉራጌኛ ትግርኛ
ኣቢ = ኣቦ
እማት = ኣደ (but ኣማት in Tigrigna means mother-in-law, so you still have the mother connection)
ኣቲ = ሓፍቲ
ዘሞ = ሓዊ (again ዘሞ in Tigrigna means brother-in-law, so you still have the brother connection)
ኣንጋቻ = ኣንጭዋ (you word for cat is close to our word for rat, again interesting similarity)
ጌ 0 ጌዛ (in Tigrigna I always thought it was from the Italian Casa, but may be not, if we have the same base with guragegna
ጣቤታ = ጣይታ
ሌማት = መሶብ (ሌማት close to ስልማት in Tigrigna meaning to adorn, our mothers say ሰሊምያ when they adorn their መሶብ with colors or shapes)
ገረድ = ጓል (but ገረድ you know from Amharic means ሴት ልጅ as in maid)
ዩጋ = ማይ
ባይ = ወደይ

I mention this only to show the hidden similarities that you may miss
Last edited by justo on 30 May 2020, 04:20, edited 2 times in total.

Aurorae
Member
Posts: 635
Joined: 10 Nov 2019, 02:21

Re: ጉራጌ ጉራዕ ከሚባል ያካለ ጉዛይ መንደር ፈለሰ ለምትሉ ስህተተኞች

Post by Aurorae » 30 May 2020, 04:08

Guys, Simbe, whatever is not Eritrean. He is Tigrayan. I don't know what he is trying to get at. He has his own agenda.
Gurae, Eritrea is a small village no more than 100 families or 500 people altogether. The Gurage family is far more complex. Just because Gurae sounds like Gurage hence Gurage is from Gurae defies logic. Only stupid African historians are capable of making such conclusions. The truth is that Aleqa had his own agenda. :lol: That does not mean, Ethiopians and Eritreans do not share ancestry. It just means that Gurages are not any more closer to Eritreans than Oromos, Amharas and other Ethiopians

Horus
Senior Member+
Posts: 30898
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ጉራጌ ጉራዕ ከሚባል ያካለ ጉዛይ መንደር ፈለሰ ለምትሉ ስህተተኞች

Post by Horus » 30 May 2020, 04:11

Simbe 11

አመሰኛለሁ !

አባት = አቢ =አቦይ ፡ በትክክል አባት፣ አቢ ና አቦይ አንድ ቃል ናቸው ። ይህ ዘሩን ባባት ለሚቆጥር የሴም ዘር አንድ ግንድ እንዳላቸው ያሳይል።
እናት = ኧሚት (እማት)=አደይ፡ ጉራጌ አዶዬ (አዳዳ/ አዳዲ) የሚጠቀመው እናት ለሚለው የጥቅል ስም ሳይሆን ያክብሮት ለሸመገሉ እናቶች ነው ። ትልቅ አያት አጋ ይባላል ። የናት ማቆላመጫና አክብሮት አዳዳ እንላለን ። አዶኔ፣ አዶዬ በሴም ጌታ፣ እመቤት ማለት ነው። አዶዬም የጉራጌ ቃል ነው።
እህት = ኧቲት = ሃፍተይ ፡ ሃብቴ ተራ የጉራጌ ስም ነው ግ ን እህት የሚል ምንም ትርጉም የለውም ።
ወንድም = ዘሚ (ዘሞ) = ሃወይ ፡ የነዚህ መመሳሰል ፊሎሎጂ ይፈልጋል ። ባጭሩ መሰሌ ማለት ነው ። ያንድ ጎሳ ህዝብ ይህን ርቀት ሊኖራቸው አይችልም ። ሁለቱም ቃላት መሰሌ፣ ሰመሌ ማለት ነው ። (ጉራጌ ሲዘፍን የኦራይ ሰመሌ እንደ ሚለው ማለት ነው)
ልጆች = ባዮች (አርዴዎች) = ቆል ፤ ይህ በጣም ይለያያል ። ባይ ቀጥታ ስሩ ባ የሚለው ኮፕቲክ ሲሆን በሴም በኒ (ወልድ) የሚለው ነው ልክ እንደ በኒ አመር እንደ ምትሉት ።
ወንድ ልጅ = ጎሽ (ገሚያ) = ወዲ ፤ ወዲ ያው ወንድ የሚለው ነው። ጎሽ ዛሬ ጋሼ፣ ጋሻዬ የሚለው ሲሆን ሜታፎር ነው ። ገሚያ ግን በርቀት አንድ ስር አላቸው ። ያንድ ደም ሰዎች ማለት ነው። በጉራጌ ደሜ፣ ዳማ ተራ ስም ነው ። እሱ ወንድሜ ወይም ወንድሙ እንደ ሚባለው ነው።
ሴት ልጅ = ገረድ = ጏል ፡ በጣም ተቀራራቢ ናቸው። ትርጉሙ ወላዲት፣ እንስት ማለት ነው ።
ምግብ = ጉንስ = መግቢ ፤ በጣም ልዩ
እንጀራ = ጣቤታ = እንጀራ/ጣይታ ፡ አንድ ናቸው ። ግን ያዝ ጤፍን ጣፊ ብሎ ከዚያም ከታፊ (ጣፒ) ጣፔታ የሚል ጉራጌ ብቻ ነው !!
ቤት = ጌ = ቤት/ገዛ ፤ አንድ ናቸው ። ቃሉ ግብጽ ነው ። ምድር፣ቦታ ማለት ነው ። ቦታ ከሚለው ቤት መጣ ፣ ምደር ከሚለው ጌ፣ ገዛ (ጌስ/ጌት/ገዛ) መጣ ። አንድ ጎሳዎች ቤትን በተለያየ ስም አይጠሩም !
ድመት = አንጋቻ = ድሙ ፡ ልዩ ናቸው
ዉሃ = ዪጋ = ማይ ፣ ዪጋ የሚቀርበው ውሃ ከሚለው ነው ። በጉራጌ ማይ ማለት ቀን ወይም እለት ማለት ነው ። ኢታ ማይ ማለት መቼ ወይም ምን ቀን ማለት ነው።
ጠላ = ስከር = ስዋ ፤ ልዩ ናቸው ። ግን በጉራጌ ጠጣ ማለት ስጭ ይባላል፤ እሱን በትግርኛ ስተይ፣ ስጨይ የሚባለው ነው።
አይብ = ቃይሳ (ቄሳ) ??
ቅቤ = ቅብ = ጠስሚ ፍጹም ልዩ ! (ጠስሚ ቢሆን ቢሆን ቀስሚ ወይም ቅስም ማለትም በአጥንት ወስጥ ያለው ቅባት መሆን ነው የሚችለው)።
እንስራ = ሻማ = ??
ምድጃ = ገርገት = ፈርኔሎ ፡
ጸሃይ = ጨበር = ፀሃይ
ኮከብ = ኢምር =ኾኸብ
መሶብ = ሌማት
ወዘተ

justo
Member
Posts: 3178
Joined: 05 May 2013, 17:54

Re: ጉራጌ ጉራዕ ከሚባል ያካለ ጉዛይ መንደር ፈለሰ ለምትሉ ስህተተኞች

Post by justo » 30 May 2020, 04:28

ኧሚት (እማት)= mother-in-law
አዳዳ also አዳዳ in tigrigna
ኧቲት = here you are wrong, ሓፍቲ in Tigrigna and ኧቲ seem to be close enough, ንዕልቲ is also sister-in-law
ዘሚ (ዘሞ) = in Tigrigna is brother-in-law
ድመት = አንጋቻ is close to the word for rat in Tigrigna

your words for mother, sister, brother are the same words for Mother-in-law, brother-in-law, sister-in-law in Tigrigna. You need to dig deeper than just the surface. Why do you think your word for cat is similar to the word for rat in Tigrigna?

ጉራጌዎች ኣይጥና ድመት የደባለቁ ትግሬዎች ናቸው ልበል ••• እንዳልሆኑ እያወቅኩ, the language however shows central affinities if you dig deeper

Horus
Senior Member+
Posts: 30898
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ጉራጌ ጉራዕ ከሚባል ያካለ ጉዛይ መንደር ፈለሰ ለምትሉ ስህተተኞች

Post by Horus » 30 May 2020, 04:39

ጁስቶ
ያንተ ዝርዝር በጣም ተስማምቶኛል ። የሴም ሕዝቦች ተመሳሳይ ወይም ተዛማጅ ቋንቋ ይናገራሉ ማለት ልክ ያልከው ነው በትክክል ። ለምሳሌ የአደሬ መዝገበ ቃላት እኔ በያንስ እስከ 35% ቃላቶቹ ከሰሜን ጉራጌ ቃላት አንድ ናቸው ። ለምን ባንድ በተወሰነ ዘመን አንድ ህዝብ ስለነበርን ! ግን አደረ ከጉራጌ መጣ ወይ ጉራጌ ካደሬ መጣ ትልቅ ስህተት ነው ፣ ያለ ጥናት ማለት ነው ። አደሬ የምልበት ምክን ያት ቋንቋ ለሚያቁ አደሬ ማለት አረሬ ማለት አንድ ቃል ስለሆኑ ነው ።

ስለዚህ አው አማት፣ ምራት፣ ወዘተ ቢወራረሱ ቢቀራረቡ እጅግ ትክክል ነው። ግ ን ትግርኛ የሴም ቋንቋ አንዱ እንጂ ግንድ አይደለም ። ትግርኛ የጉራጌ ቋንቋ ግንድ ወይም አባት አይደለም ። እኔ የሰሜን ወንሞቼን ምላቸው ይህ ነው። አንተ ከዚህ መታህ ፣ እሱ ከዚያ መጣ ለማለት ሳይንሳዊ ፋክት ያስፈልጋል ። ፖለቲካ ቅስቀሳና እውቀት ለየቅል ናቸው ። ይልቅስ የተለያዩ የሴም ቋንቋ ሚያውቁ እንደዚህ ቢማማሩ ስለ ራቸው ሁሉ ብዙ መማር ይችላሉ ። ጉራጌኛ በኡጋሪቴ፣ በአረሜይክ (አረማዊ)፣ በአሲሪያዊ ውስጥ አለ ። ማርቲን በርናል አፍሮ ኤዚአቲክ ቋንቋ ቤቱ መሃል ኢትዮጵያ ሊሆን ይችላል ብሎ ሲከራከር ነበር።

አንድ ምስጢር ልጠይቅህ ? ኢዛና ማለት ምን ማልት ነው? ይህን ቃል እስከ ዛሬ ሚጠቀም የኢትዮጵያ ህዝብ ማነው? !!!

Horus
Senior Member+
Posts: 30898
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ጉራጌ ጉራዕ ከሚባል ያካለ ጉዛይ መንደር ፈለሰ ለምትሉ ስህተተኞች

Post by Horus » 30 May 2020, 04:55

ጁስቶ
በጉራጌ ፡
አይጥ = ኧፉር
ድመት = አንጋቻ (አን ካት ቢሆን አትገረም)
ቤት = ጌ (ገየት፤ ጌያት) ገዛ ወይ ጋዛ ቢባል አትገረም ፤ ግዕዝ የአፍሮ ኤሺያ ግንድ ስለሆነ
አንተ ዘሞ ያለከው (የባል ወንድም) ጉራጌ ዋርሳ ይለዋል ። ባል ሲሞት ወንድም ስለሚወርሳት !

ኬር !!!

Horus
Senior Member+
Posts: 30898
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ጉራጌ ጉራዕ ከሚባል ያካለ ጉዛይ መንደር ፈለሰ ለምትሉ ስህተተኞች

Post by Horus » 30 May 2020, 05:05

EPRDF wrote:
30 May 2020, 02:59
ወሄዋሬ ዋጆ Horus አቻምውሄ :mrgreen:

ጉራጌ ሲባል አስር በላይ ነገድ ያለው ብሄረሰብ ነው፣ ቋንቋቸውም አንድ ዓይነት አይደለም፣ አንዱ ከኣንዱ ጭራሽ ጉራግኛ በሚሉት ቋንቋ አይግባባም፣ ታዲያ እንዴትና ለምን በኣንድ ጉራጌ በሚል ቃል መጠርያ እንደሚጠቃለል ነው እኔ የማይገባኝ፣።

ስልጤ እኔ ጉራጌ አይደለሁም ብሎ ከተሰነባበተ ከርሞዋል፣ ወለኔም ጉራጌዎች ደሃና ሁኑ ለማለት በሂደት ላይ ነው ያም ብዙ አይገርምም ምክኒያቱም በቋንቋ አንድነት ያልተሳሰረ ሕዝብ፣ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ፣ በኣንድ ሰውሰራሽ (artificial) ስም ተጠቅልሎ (በጉራጌ) ስለማይዘልቅ ነው። እየታየ ያለውም ይሀው ነው።

ዋጆ፣ እስቲ ከዋሸሁ ወይ ከተሳሳትኩኝ፣ ምን ያህል የኣንዱ ጉራጌ ጎሳ ቋንቋ ከሌላው ከኣንድ ከሁለቱ የጎሳ ቋንቋ ጋር እንደሚቀራረብ ኣሳየንና prove me wrong። ወይንም አዚህ የዘረዘካቸውን (እርግጠኛ ነኝ የሶዶ ጉራጌ ቃላቶች ናቸው)ከሌላው ጉራግኛ የቋንቋ ቃላት ጋር ምን ያህል እንደሚዛመዱ አሳየን። አመሰግናለሁ።
ኢፒዲአራኢፍ እና ያቤሎ
የሚማር አንጎል በቅላቹ ውስጥ ቢኖር ባስተምራችሁ ደስታዬ ። እኔ ሆረስ ነኝ የሸመገለ መሃይም ከማስተምር ዉሻዬን ዳንስ ባስጠናው ይመቸኛል !!! እናንተ ለእኔ ፋይዳ አልቦ ስለሆናችሁ !!1

justo
Member
Posts: 3178
Joined: 05 May 2013, 17:54

Re: ጉራጌ ጉራዕ ከሚባል ያካለ ጉዛይ መንደር ፈለሰ ለምትሉ ስህተተኞች

Post by justo » 30 May 2020, 05:20

Horus wrote:
30 May 2020, 04:39
ማርቲን በርናል አፍሮ ኤዚአቲክ ቋንቋ ቤቱ መሃል ኢትዮጵያ ሊሆን ይችላል ብሎ ሲከራከር ነበር።

አንድ ምስጢር ልጠይቅህ ? ኢዛና ማለት ምን ማልት ነው? ይህን ቃል እስከ ዛሬ ሚጠቀም የኢትዮጵያ ህዝብ ማነው? !!!
Dear Horus,
Even the Nobel Prize winning neurobiologist Erik Kandell, in his textbook, Principles of Neuroscience says that the origin of language, religion and culture were in what he calls Eritrea, but can be taken to mean also Ethiopia, in short the Horn region.

His reasoning was that there is no society in the globe that does not have language, religion and culture. So either these three things were first developed in one place before mankind went its separate ways, or they are so important than men would create language, religion and culture wherever they went. And he preferred the first alternative, since the basic syntax of language is the same everywhere.

About Ezana, I really don't know, please do enlighten us, I only know that his name was not listed in the list of Kings, so I suspect the word Ezana may be a title or something and not a name, I don't know.

justo
Member
Posts: 3178
Joined: 05 May 2013, 17:54

Re: ጉራጌ ጉራዕ ከሚባል ያካለ ጉዛይ መንደር ፈለሰ ለምትሉ ስህተተኞች

Post by justo » 30 May 2020, 05:29

Horus wrote:
30 May 2020, 04:55
ጁስቶ
በጉራጌ ፡
አይጥ = ኧፉር
ድመት = አንጋቻ (አን ካት ቢሆን አትገረም)
ቤት = ጌ (ገየት፤ ጌያት) ገዛ ወይ ጋዛ ቢባል አትገረም ፤ ግዕዝ የአፍሮ ኤሺያ ግንድ ስለሆነ
አንተ ዘሞ ያለከው (የባል ወንድም) ጉራጌ ዋርሳ ይለዋል ። ባል ሲሞት ወንድም ስለሚወርሳት !

ኬር !!!
This is very interesting, rat in Tigrigna is ኣንቻዋ and ዋርሳ we call the Sawa generation which are the inheritors of the liberation movement generation እናንተ የስልሳዎቹ ትውልድ የምትሉት. The role of the older liberation era generation was inherited by the ዋርሳ generation
Young Eritrean soldiers are called ዋርሳ because ታላቅ ውንድማቸው ሲሞት እነሱ የሱን ተራ ስለሚወርሱ።

I am curious to hear though about what you make of Ezana

Horus
Senior Member+
Posts: 30898
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ጉራጌ ጉራዕ ከሚባል ያካለ ጉዛይ መንደር ፈለሰ ለምትሉ ስህተተኞች

Post by Horus » 30 May 2020, 05:52

ጁስቶ፤
ትክክል ነው ። እንደ ኒውሮ ላንጉጅ ከሆነ አንድ የሰው ልጅ በሰውነቱ፣ ባካሉ ቅርጽና አሰራር መሰረት ከተፈጥሮ ሜታፎር ወይም ምሳሌ በመስራት ቋንቋ ይፈለስፋል ። አንድ እንሰሳ ድምጽ ሳለው ቋንቋ አለው ማለት አይደለም ። ቋንቋ ቅርጸ ነገር ወይም ኮንሴፕት ይፈልጋል። ያ ምሳሌ ወይም ሜታፎር እንለዋለን ። ጀግና አምበሳ ነው እንደ ማለት ! ሰውዬውን በአምበሳ መሰልነው ማለት ነው ። አሁን ጥያቄው ይህ የምሳሌ ቴክኖሎጂ ካንድ ቦታ ወደ አለም ተሰራጨ ወይስ ሰዎች በያሉበት የራሳቸውን የቋንቋ ቴክኖሎጂ አሳደጉ የሚለው ነው። ሃሳብና ቅርጸ ነገር ልክ እንደ ቫይረስ ነው ፣ በሰው ተሸካሚነት ከቦታ ቦታ ይተላልፋል የሚለው የካልቸራሊስት እስኩል ሞዴል ነው ። ሞዴሉ ልክ የኤፕዲሜኦሎጂ ሞዴል ነው። ሌሎችም አሉ !!! ስለዚህ የሴም ቋንቋ ሚባለው ሚም ወይም ቫይረስ ከየት ተነሳ? እንዲት ተስፋፋ ማለት ሞዴል ነው። ካርታ ነው ። የሰዎች ፈጠራ ነው። አንድ ሰው ኖቤል ተሸለመ ማለት እውነተኛ ነው ማለት አይደለም ። ሸላሚዎቹ ተስማሙ ማለት ነው !! በቃ !

ኢዛና እጅግ ጥንታዊ ቃል ሲሆን ህያው አደገው በየቀኑ የሚጠቀሙበት ሕዝብ ዛሬ ጉራጌዎች ናቸው። ቃሉ በህንድ፣ በአረቦች አገር ሁሉ አለ ።

መጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ ሆሳዕና ሲባል ታገኘዋለህ ። ንጉስ ማለት ነው ። በሆሳዕና ንጉሱ በሰላም ከተማ ገባ፣ ከተማ ያዘ ይባላል። ድሮ ንጉስ ከተማ ሚገባው በጦርነት ስለ ነበር ።

በህንድ ሆሻና ማለት መስፍን ወይም ፕሪንስ ልኡል ማለት ነው ።

በፋርስ ና ኢራን ሻሃ ንጉስ ወይም ሻሃንሻህ ንጉሰ ነገስት ማለት ነው ።

በተራ አጠቃቀም አዚዝ፣ አዛዥ፣ ትዕዛዝ ወዘተ ይባላል።

እዣ ማለት ሃይል፣ ስልጣን ማለት ነው።

ኢዛና ማለት ንጉስ፣ ልኡል ፣ ገዢ፣ ነጋሲ፣ ነጋዢ ማለት ነው። ስለዚህ ዛሬ ራሳቸውን እዣ ብለው ሚጠሩት የጉራጌ ጎሳ የነጋሲ የመሳንፍት ቤት ማለታቸው ነበር። ሌሎች ከሴ፣ በዎዠ፣ ወዘተ ሚሉ ካገዛዝ ጋራ የተያያዙ ቋንቋዎች በብዛት አሉ ። ስለዚህ ይህ ነው የኢዛና ስም ግንድ ። በነገራችን ላይ የኢዛና አያት ነጋሲ ግድር ይባል ነበር ። ግድር ማለት ታላቅ ማለት ነው ። ያ ቃል ዛሬም በጥቅም ላይ የያዙት ጉራጌዎች ናቸው ። በጉራጌ ግድር ማለት ታላቅ ማለት ነው።

Post Reply