Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Post Reply
Maxi
Member+
Posts: 5888
Joined: 06 Mar 2014, 04:33

ከሳንባ ቆልፍ (ከኮሮና ቫይረስ) መከላከያ ዘዴዎች!!

Post by Maxi » 01 Apr 2020, 09:32

ኢትዮጵያውያን ኮሮና ቫይረስ "ሳንባ ቆልፍ" ስም ሰጥተውታል!!!

ከሳንባ ቆልፍ (ከኮሮና ቫይረስ) መከላከያ ዘዴዎች!!

የሳንባ ቆልፍ (የኮሮና ቫይረስ) አካል ጉዳተኛ ወገኖች ሊያደርስ የሚችለውን ጉዳት ከወዲሁ እንከላከል!

በመሆኑም የተለያዩ የመከላከያ መንገዶች እና ዘዴዎች በጤና ባለሙያዎች እየተሰጡ ይገኛሉ፡፡
አካል ጉዳት ያለባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች እንደ የአካል ጉዳታቸው አይነት ጉዳት ከሌለባቸው ሰዎች የበለጠ ለቫይረሱ የሚጋለጡበት ሁኔታ ይኖራል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የመከላከያ መንገዶቹን ለመተግበር ብዙ እንቅፋቶች ይደቀንባቸዋል፡፡
ሆኖም አካል ጉዳት ያለባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ልዩ ትኩረት ተሰቷቸው ሳንባ ቆልፍ (ኮሮና ቫይረስ COVID-19) የመከላከያ መንገዶችን እንደየ ጉዳታቸው ነባራዊ ሁኔታ የጥንቃቄ መመሪያዎቹን መተግበር ያስፈልጋል፡፡

የተለያየ አካል ጉዳት ያለባቸው ሰዎች ራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ከሳንባ ቆልፍ (ከኮሮና ቫይረስ) እንዴት ይከላከላሉ?

1. የዊልቸር ተጠቃሚ አካል ጉዳተኞች ማድረግ የሚገባቸውን ጥንቃቄዎች
የአለም ጤና ድርጅት ( WORLD HEALTH ORGANIZATION) እና የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስተር ያወጧቸውን የሳንባ ቆልፍ (የኮሮና ቫይረስ) መከላከያ መመሪያዎችን ተግባራዊ ማድረግ፡፡

I. እጅን በንፁህ ውሃና ሳሙና ደጋግሞ መታጠብ ፤
II. ከሌሎች ሰዎች ጋር አለመጨባበጥ ፤
III. ሰዎች በሚበዙበት አካባቢ አለመቀመጥ፤
IV. በቂ እና ንፁህ አየር ማግኘት ፤
V. ማህበራዊ ርቀትን መጠበቅ፤
VI. በሚያስነጥሱበት ወይም በሚያስሉበት ወቅት አፍና አፍንጫን በእጅዎ ክርን/በሶፍት / መሸፈን፤
VII. በእጅዎ ፊቶን ፣ አፍንጫዎንና አይኖን አይንኩ

- ከላይ የተዘረዘሩት የጥንቃቄ መመሪያዎች እንዳሉ ሆነው ከጉዳትዎ አንፃር የሚንቀሳቀሱበት ዊልቸር በንጽህናና በጥንቃቄ መጠቀም ፤
- ዊልቸሮን ከሌሎች ሰዎች ንክኪ ነፃ በማድረግ እና በውሃና ሳሙና / አልኮል ማፅዳት፤
- ከረዳቶቻቸው ጋር ማንኛውንም የእጅ ንክኪ አለማድረግ እና ረዳቶቻቸውም የአለም የጤና ድርጅት ያወጣቸውን የጥንቃቄ መመሪያዎች ተግባራዊ እንዲደረጉ ማድረግና መከታተል
- ቤተሰቦቻቸውና የቅርብ ጓደኞቻቸው ጋር የሚኖራቸው አካላዊ ንክኪ መጠንቀቅ፤
- የሚጠቀሙበትን የዊልቸወር አካል በተለይም መደገፊያና እጄታዎችን ደጋግሞ በአልኮል ማጽዳት ፤
- የዊልቸር ረዳቶቻቸው የትንፋሽ መከላከያ ማስክ እንዲደርጉ ማድረግ ፤

2. አይነ ስውራን አካል ጉዳተኞች ማድረግ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች

የአለም ጤና ድርጅት (WORLD HEALTH ORGANIZATION) እና የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስተር ያወጧቸውን የሳንባ ቆልፍ (የኮሮና ቫይረስ) መከላከያ መመሪያዎችን ተግባራዊ ማድረግ እንደተጠበቁ ሆነው እንደሌሎች አካል ጉዳተኞች ሁሉ፤

- የሚጠቀሙበትን የእጅ ብትርን ንጽህና መጠበቅ እና ከሌሎች ሰዎች ንክኪ እንዳይኖር መጠንቀቅ፤
- ከረዳቶቻቸው ጋር የእጅ ንክኪ አለማድረግ ፤
- ከቦታ ቦታ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ መቀነስና ሰዎች በሚበዙበት አካባቢ አለመሄድ ወይም አለመቀመጥ ፤
- የሚጠቀሟቸውን መረጃ መሳሪያዎች ለምሳሌ የአይን መነጽሮችን ፣ ኤሌክትሮኒክስ እና የብሬይል እና ሌሎች ቁሳቁሶችን ዘውትር ንጽህናውን መጠበቅ፤
- ያለ ረዳት የሚንቀሳቀሱ አይነ ስውራን አካል ጉዳተኞጭ በሚንቀሳቀሱበት ወቅት ድጋፍ ለሚያደርጉላቸው የሚቀርቡ ሰዎች ከእጅ ንክኪ ይልቅ የክንድ ወይም የብትር ጫፍ ይዞ እንዲረዷቸው ማድረግ ፤

3. ክራንች ተጠቃሚ አካል ጉዳተኞጭ ማድረግ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች

የአለም ጤና ድርጅት (WORLD HEALTH ORGANIZATION) እና የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስተር ያወጧቸውን የሳንባ ቆልፍ (የኮሮና ቫይረስ) መከላከያ መመሪያዎችን ተግባራዊ ማድረግ እንደ ሌሎች አካል ጉዳተኞች ሁሉ፤

የሚጠቀሙበትን ክራንች ፣ ሰው ሰራሽ አካል ፣ አርቴፊሻል ብሬስ እና ሌሎች ቁሳቁሶችን ንጽህና መጠበቅ እና ሌሎች ሰዎች እንዳይነኩ መጠንቀቅ፤

የሚጠቀሙበትን ክራንች እጄታ በአልኮል ማጽዳት፤

ክራንች ተጠቃሚ አካል ጉዳተኞጭ ከቦታ ቦታ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ መቀነስና
4. መስማት የተሳናቸው አካል ጉዳተኞች ማድረግ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች
የአለም ጤና ድርጅት (WORLD HEALTH ORGANIZATION) እና የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስተር ያወጧቸውን የሳንባ ቆልፍ (የኮሮና ቫይረስ) መከላከያ መመሪያዎችን ተግባራዊ ማድረግ እንደ ተጠበቁ ሆነው እንደ ሌሎች አካል ጉዳተኞች ሁሉ፤

- የሚጠቀሙበት መርጃ ቁሳ ቁስ ለምሳሌ የማዳመጫ መሳሪያ / hearing aid ንጽህና መጠበቅ ፤
- ከምልክት ቋንቋ አስተርጓሚዎች ጋር እና ከሌሎች ሰዎች ጋር የእጅ ንክኪ አለማድረግ እና
- ከአስተርጓሚዎ ጋር እና ከሌሎች ሰዎች ጋር የሚኖራቸውን አካላዊ ርቀት ማስፋት፤

5. የአዕምሮ እድገትና የመማር ውስንነት እንዲሁም የኢቲዝም ችግር ያለባቸው አካል ጉዳተኞች

• ወላጆች ፣ አሳዳጊዎች እንዲሁም ተንከባካቢዎች የአለም ጤና ድርጅት WORLD HEALTH ORGANIZATION እና የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር ያወጧቸወን የኮሮና ቫይረስ መከላከያ መመሪያዎችን ተግባራዊ በማድረግ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ ፤
• የለት ተለት ውሏቸውን መከታተል እና ከማንኛውም ሰው ጋር የሚያደርጉትን ንክኪ መቆጣጠር ፤
• ከቤት ውጭ በአከባቢ የሚያደርጉትን ውሎ እንዲቀንሱ ማድረግ / መከልከል፤
• በቫይረሱ ስርጭት እና አስከፊነት ዙሪያ ግንዛቤ እንዲኖራቸው በቤት ውስጥ በሚገባቸው መንገድ ማስተማር እና ሁኔታውን በተግባር ማስረዳት፤

Post Reply