Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
simbe11
Member
Posts: 2087
Joined: 23 Feb 2013, 13:02
Location: Addis Ababa

ትንሽ ስለ ጉራዕ (በላኢ በቅሊ)

Post by simbe11 » 31 Mar 2020, 21:25

ትንሽ ስለ ጉራዕ (በላኢ በቅሊ)

ጉራዕ በኤርትራ ምድር ከደቀመሃሪ አቅራቢያ የምትግኝ መንደር ናት:: በቀደመው ዘመን በአካለጉዛይ ምድር ጉራዕን የሚፎካከር እንዳልነበር ይነገራል:: የጉራዕ ተወላጆች ሲሻቸው ደቀመሃሪን አልፈው ወደሰሜን ተጉዘው ወይንም ደሞ ወደምእራብ መረብን ተሻግረው ደቡብም ምስራቅም ሳይቀራቸው ህዝብን እያሸበሩና እየዘረፉ ሲያስለቅሱት ውለው ማደር የዘወትር ተግባራቸው ነበር:: ከሁሉ በላይ ግን የጉራዕ ሽፍቶች የሚታወቁበት ነገር ያገሩን ከብት እየነዱ በመውሰድ ነበር::
በዚህ የጉራዕ ተግባር ከተማረሩት አካባቢዎች አንዱ ታድያ መላ ዘየደ:: ጉራዎች ለዝርፊያ ሲመጡ አርዶ አዘጋጅቶ መጠበቅ:: የተፈራውም አልቀረ የለመደ የጉራዕ ዘራፊ በምሽት መጥቶ አካባቢውን ወሮ ይዞ ሲያበቃ እንደለመደው ያካባቢውን በረትና ሌማት ሲደፋ አነጋ:: ታርዶ ተዘጋጅቶ የጠበቀውንም ብርንዶ/ስጋ አወራርዶ ከበረት የተረፈውንም እየነዳ ወደሃገሩ ተመለሰ::
መንደሩ በጉራዕ ሲወረር ነፍሱን ለማትረፍ ወዳካባቢው ጫካ ገለል ብሎ የቆየው ያካባቢው ሰውን በሰፈሩ ሲመለስ አርዶ ያዘጋጀው የበቅሎ ስጋ ሁሉ ተበልቶ በማግኘቱ ተደሰተ ይባላል:: ከዛን ዘመን በኃላ ጉራዕ የሚለው ስም "በላኢ በቅሊ" በሚለው ተተክቶ ጉራዎች አሁን ድረስ በላኢ በቅሊ እየተባሉ ይጠራሉ:: "በላኢ በቅሊ" ማለት በቅሎ የሚበላ ማለት ነው::

simbe11
Member
Posts: 2087
Joined: 23 Feb 2013, 13:02
Location: Addis Ababa

Re: ትንሽ ስለ ጉራዕ (በላኢ በቅሊ)

Post by simbe11 » 01 Apr 2020, 13:00

Gurai is the place where Gurage is originated from, according to historians.

Noble Amhara
Senior Member
Posts: 11626
Joined: 02 Feb 2020, 13:00
Location: Abysinnia Highlands

Re: ትንሽ ስለ ጉራዕ (በላኢ በቅሊ)

Post by Noble Amhara » 01 Apr 2020, 13:11

Medri Bahri people like you must accept that the name Eritrea is artificial the real historic name is Medri Bahri the Ethiopian Kingdom

Halafi Mengedi
Senior Member+
Posts: 45728
Joined: 30 May 2010, 23:04

Re: ትንሽ ስለ ጉራዕ (በላኢ በቅሊ)

Post by Halafi Mengedi » 01 Apr 2020, 13:36

simbe11 wrote:
01 Apr 2020, 13:00
Gurai is the place where Gurage is originated from, according to historians.
No wonder the Gurage call himself "Harus"???

You are right and logic link to the Kitfo eater of Gurage now including Amhara???

simbe11
Member
Posts: 2087
Joined: 23 Feb 2013, 13:02
Location: Addis Ababa

Re: ትንሽ ስለ ጉራዕ (በላኢ በቅሊ)

Post by simbe11 » 01 Apr 2020, 15:24

What’s you’re saying has nothing to do with the thread.
As far as I’m concerned, you can call it either way.
Noble Amhara wrote:
01 Apr 2020, 13:11
Medri Bahri people like you must accept that the name Eritrea is artificial the real historic name is Medri Bahri the Ethiopian Kingdom

simbe11
Member
Posts: 2087
Joined: 23 Feb 2013, 13:02
Location: Addis Ababa

Re: ትንሽ ስለ ጉራዕ (በላኢ በቅሊ)

Post by simbe11 » 01 Apr 2020, 15:28

I’m not sure of what you just said. But, if the tale and the name Horus are related, it’s better answered by the person called Horus.
Halafi Mengedi wrote:
01 Apr 2020, 13:36
simbe11 wrote:
01 Apr 2020, 13:00
Gurai is the place where Gurage is originated from, according to historians.
No wonder the Gurage call himself "Harus"???

You are right and logic link to the Kitfo eater of Gurage now including Amhara???

Eripoblikan
Member
Posts: 3197
Joined: 15 Sep 2019, 13:49

Re: ትንሽ ስለ ጉራዕ (በላኢ በቅሊ)

Post by Eripoblikan » 01 Apr 2020, 15:30

Noble Amhara wrote:
01 Apr 2020, 13:11
Medri Bahri people like you must accept that the name Eritrea is artificial the real historic name is Medri Bahri the Ethiopian Kingdom
ዛሬ ስንት ኪሎ ባቄላ ነው የበላህ፡ ጓደኛ?

ይሄ ፎረም ፈስ በፈስ ኣረግከው።

:lol: :lol: :lol: :lol: :lol:
:lol: :lol: :lol: :lol: :lol:

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ትንሽ ስለ ጉራዕ (በላኢ በቅሊ)

Post by Horus » 01 Apr 2020, 16:58

እንደ ምታቁት ሲምቤ 11 ከጉራጌ ጋር ግዙፍ የሳይኮሎጂ ችግር ይዞታል ። ድሮ ድሮ አለቃ ታዬ በዘልማድ ተነስተው በወረወሩት ተረት ጉራጌ የሚለው ቃል ጉርአ ከተባለው ያከለጉዛይ መንደር የመጣ ነው ባሉት ሳቢያ ዛሬ ይህም ያም ሳንቲም ስለ ጉራጌ የማያቅ ያላጠና እየተነሳ የማይለው የለም ። የሲምቤ ችግር ግን ሌላ ነው ። የሱ ችግር ጉራጌ ለምን የዎያኔን ቆሻሻ የዘር ፖለቲካ አልተቀላቀለም፣ ለምን የዎያኔን ቆሻሻ ባንዲራ አላራገበም የሚል ነው ። ያ ደሞ ያለቀ የሞተ ጉዳይ ነው ። የዎያኔ አልቦ ነገር በሲምቤ የጃጀው ቅል ውስጥ ያለ ምናባዊ ጭጋግ ነው ። በቃ !

ደሞ ጉራጌ የሚለው ስም ግራ/ቀኝ ከሚለው ቃል ጋር ፍጹም አይገናኝም ። በመላ ጉራጌ ውስጥ ጉራ የሚባል ቦታ የለም። ጉራጌ ለሰውም ይሁን ለቦታ አንድ ግዜ ራሳችህንን ከግራ ወይ ከቀኝ ሚል ስም ሰጥተን አናቅም ።

ይልቅስ ጉራ የሚነሳው ከራሱ ከጉራጌ ያስተዳደር ሴራ ጎርደና ወይም ድሮ ድሮ አጉራ ጠነ ከሚባለው ያገር አስተዳድር ስም ነው ። አጉራ ጠነ በዘመነ ጎንደር እና ከዚያም በፊት የነበረ ራስ ገዝነት ማለት፣ ራስ ገዝ አገር ማለት ነው። ዛሬም ይህ ሴራ ጎርደና ወይም ያገር ጉባኤ ይባላል። በተለያዩት የጉራጌ ማሀረሰብ እንደየ ቋንቋው ስሙ ቃሉ የለያይ እንጂ ሰራቱ ተመሳሳይ ነው ።

ገር አገር ማለት ነው ። ጎራ አገር፣ ማህበር ይባል እንደ ነበረው ። ግሪክችም አጎራ ይሉት እንደ ነበረው ። ስለዚህ ጉራንዳ፣ ጌእንዳ፣ ቤተንዳ፣ እንዳጌ፣ ጎረቤት፣ ቤተጎር፣ እንደጎር፣ እነቆር፣ እነጎር፣ እንደጎር፣ እንደጋኝ፣ ሌሎች እልፍ የጉራጌ ቃላት ትርጉም የማያውቁ ባይተዋሮች ስለጉራጌ ባይቀባጥሩ መልካም ነው እላለሁ ።

እኔ ሆረስ ነኝ፤ ቃላት መፍለጥ አይመቸኝም። ሆረስ ሁለት አይኖች አሉት፣ አንዱ ጸሃይ ሲሆን ሌላው ጨረቃ ነው ። ሆረስ ሁሉን ሚያይ !!! ኬር

simbe11
Member
Posts: 2087
Joined: 23 Feb 2013, 13:02
Location: Addis Ababa

Re: ትንሽ ስለ ጉራዕ (በላኢ በቅሊ)

Post by simbe11 » 01 Apr 2020, 18:50

ሚስተር ሆረስ ፤ እኔ ከወያኔ ጋ ምንም ኝኙነት የለኝም፡፡
ጉራጌን የመስደብም ሆነ የመናቅ ፍላጎትም ሆነ ምኞት የለኝም፡፡ የኔ ችግር ከዘረኞች ጋር ነው፡፡
ጉራዐ አንት እንደምትለው ግራ ማለት አይደለም፡፡ እኔ እስከማውቀው ጉራዐ ማለት ጠንካራ/ብርቱ ወይም ደሞ ዳገት/አቀበት ማለት ነው፡፡
"Gurai is the place where Gurage is originated from, according to historians." ያልኩት አንብበው፡፡
ጉራጌ ሌላ ማንነት ካለው ደሞ ንገረን፡፡

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ትንሽ ስለ ጉራዕ (በላኢ በቅሊ)

Post by Horus » 01 Apr 2020, 20:31

simbe11 wrote:
01 Apr 2020, 18:50
ሚስተር ሆረስ ፤ እኔ ከወያኔ ጋ ምንም ኝኙነት የለኝም፡፡
ጉራጌን የመስደብም ሆነ የመናቅ ፍላጎትም ሆነ ምኞት የለኝም፡፡ የኔ ችግር ከዘረኞች ጋር ነው፡፡
ጉራዐ አንት እንደምትለው ግራ ማለት አይደለም፡፡ እኔ እስከማውቀው ጉራዐ ማለት ጠንካራ/ብርቱ ወይም ደሞ ዳገት/አቀበት ማለት ነው፡፡
"Gurai is the place where Gurage is originated from, according to historians." ያልኩት አንብበው፡፡
ጉራጌ ሌላ ማንነት ካለው ደሞ ንገረን፡፡
ሲምቤው፤

ይሀውልህ ችግርህ ሲወጣ፣ የጉራጌ ማንነትማ ድብን ያለ ኢትዮጵያዊ በጎሳው ጉራጌ ይባላል። ከቢሽ? በቃ!!

ታሪክ ከሆነ ምታወራው ከማን እንዳገኘሀው ለምን አትጠቅስም? ስለማታቀው ነው ። ጉራጌ ከጉራ መጣ ያሉት አለቃ ታየ በዚያች በጢኒሿ የኢትዮጵያ ሕዝብ ታሪክ ብለው ግዙፍ ስም በሰጡት መጽሃፋቸው ነው ። በልጅነቴ ሺ ግዜ አንብቤዋለሁ ።

ጉራ ዳገት ወይም አቀበት ካሉት የዚያ አገር ሕዝቦች ትክክል ነው ። በአማሪኛ ጋራ የሚባለው ነው ። ጉራጌ ጉራ ወይም ጋራ አይልም ። ዳገት ወይም አቀበት ቅበት እንለዋለን ። ትልቅ ተራራ ገገራ እንለዋለን ። ለምሳሌ ዘቢደር ገገራ ነው ።ቡታጀራ ቅበት ነው ።

ጉራአ ጠንካራ ማለት ከሆነም ትክክል ነው ፣ ግን የዚያ ቃል ስር ካራ (ሳንጃ) ሲሆን ጠንካራ ወይም ጎራዴ የምንለው ነው ። በእኔ እምነት አንድ ቦታ ካራ ወይም ጎራዴ አይባልም። ትክክለኛ ትርጉሙ ጉራአ ዳገት (ደጋ እንዲሉ) ወይም አቀበት ማለት ነው።

አለቃ ታየ ያሉት ግን ጉራጌዎቹ በዘመቻ ወቅት ከንጉሱ በግራ በኩል ሰፍረው ስለነበር ነው ያሉት ፣ የግራ ጦር፣ ግራ ሰፋሪ፣ የግራ አዝማች እንደ ቢባለው ። ይህን አባባልቸው ሟቹ የታሪክ ሰው ዶ/ር ታምራት ላይም ተጸኖ ስላረገ ጉራጌዎች በዘመነ አክሱም ወደ ሸዋ የተላኩ ጦር ሳይሆኑ አይቀሩም ብሏል ። እንዲህ እንዲህ እያለው ነው ትክክል ያልሆነ ታሪክ የሚፈበረከው ።

ጉራጌ ከ አስራ አንድ ቋንቋዎች በላይ የሚናገር እጅግ ሰፊ የነበረ፣ ከብዙ ጎሳ ተቀምሮ በሂደት አንድ ስልጣኔ የቆመ ሕዝብ ነው ፣ ልክ እንደ አማራ፣ ልክ እንደ ኦሮሞ፣ ልክ እንደ ትግሬ ።

በእድሜም ቢሆን ማርቲን በርናል እንዳጠናው የጉራጌ ቋንቋዎች እጅግ ጥንታዊና ፕሮቶ ሊሳን ነው። ስለዚህ ከዚህ ቦታ ፈልሶ በዚህ ቀን ሸዋ ገባ የሚሉት ምንም ምርምር ያላደረጉ፣ ሊንጉዊስት ሆነ፣ አንትሮፖሎጂ ሆነ፣ ታሪክ ሆነ፣ አርኪኦዎልጂ ያላረጉ ናቸው ።

ራሳቸው የጉራጌ ልሂቃንም በውል ያላጠኑትን ተነስተው እንዲሰብኩ አንፈቅድም ። ጉራጌ የማንነት ችግር የለውም ፣ እውነተኛ ነገር በሳይንስ ተደግፎ ወደፊት ሁሉም ይታወቃል ። ይህ የጅንኢእቲክስ ዘመን ነውና ።

simbe11
Member
Posts: 2087
Joined: 23 Feb 2013, 13:02
Location: Addis Ababa

Re: ትንሽ ስለ ጉራዕ (በላኢ በቅሊ)

Post by simbe11 » 01 Apr 2020, 22:22

I get that. Gurage are proud Ethiopians. So am I.
My question will be where does the Gurage Semite identity originated from?
That's why I tend to believe the Gurai story.

Horus wrote:
01 Apr 2020, 20:31
simbe11 wrote:
01 Apr 2020, 18:50
ሚስተር ሆረስ ፤ እኔ ከወያኔ ጋ ምንም ኝኙነት የለኝም፡፡
ጉራጌን የመስደብም ሆነ የመናቅ ፍላጎትም ሆነ ምኞት የለኝም፡፡ የኔ ችግር ከዘረኞች ጋር ነው፡፡
ጉራዐ አንት እንደምትለው ግራ ማለት አይደለም፡፡ እኔ እስከማውቀው ጉራዐ ማለት ጠንካራ/ብርቱ ወይም ደሞ ዳገት/አቀበት ማለት ነው፡፡
"Gurai is the place where Gurage is originated from, according to historians." ያልኩት አንብበው፡፡
ጉራጌ ሌላ ማንነት ካለው ደሞ ንገረን፡፡
ሲምቤው፤

ይሀውልህ ችግርህ ሲወጣ፣ የጉራጌ ማንነትማ ድብን ያለ ኢትዮጵያዊ በጎሳው ጉራጌ ይባላል። ከቢሽ? በቃ!!

ታሪክ ከሆነ ምታወራው ከማን እንዳገኘሀው ለምን አትጠቅስም? ስለማታቀው ነው ። ጉራጌ ከጉራ መጣ ያሉት አለቃ ታየ በዚያች በጢኒሿ የኢትዮጵያ ሕዝብ ታሪክ ብለው ግዙፍ ስም በሰጡት መጽሃፋቸው ነው ። በልጅነቴ ሺ ግዜ አንብቤዋለሁ ።

ጉራ ዳገት ወይም አቀበት ካሉት የዚያ አገር ሕዝቦች ትክክል ነው ። በአማሪኛ ጋራ የሚባለው ነው ። ጉራጌ ጉራ ወይም ጋራ አይልም ። ዳገት ወይም አቀበት ቅበት እንለዋለን ። ትልቅ ተራራ ገገራ እንለዋለን ። ለምሳሌ ዘቢደር ገገራ ነው ።ቡታጀራ ቅበት ነው ።

ጉራአ ጠንካራ ማለት ከሆነም ትክክል ነው ፣ ግን የዚያ ቃል ስር ካራ (ሳንጃ) ሲሆን ጠንካራ ወይም ጎራዴ የምንለው ነው ። በእኔ እምነት አንድ ቦታ ካራ ወይም ጎራዴ አይባልም። ትክክለኛ ትርጉሙ ጉራአ ዳገት (ደጋ እንዲሉ) ወይም አቀበት ማለት ነው።

አለቃ ታየ ያሉት ግን ጉራጌዎቹ በዘመቻ ወቅት ከንጉሱ በግራ በኩል ሰፍረው ስለነበር ነው ያሉት ፣ የግራ ጦር፣ ግራ ሰፋሪ፣ የግራ አዝማች እንደ ቢባለው ። ይህን አባባልቸው ሟቹ የታሪክ ሰው ዶ/ር ታምራት ላይም ተጸኖ ስላረገ ጉራጌዎች በዘመነ አክሱም ወደ ሸዋ የተላኩ ጦር ሳይሆኑ አይቀሩም ብሏል ። እንዲህ እንዲህ እያለው ነው ትክክል ያልሆነ ታሪክ የሚፈበረከው ።

ጉራጌ ከ አስራ አንድ ቋንቋዎች በላይ የሚናገር እጅግ ሰፊ የነበረ፣ ከብዙ ጎሳ ተቀምሮ በሂደት አንድ ስልጣኔ የቆመ ሕዝብ ነው ፣ ልክ እንደ አማራ፣ ልክ እንደ ኦሮሞ፣ ልክ እንደ ትግሬ ።

በእድሜም ቢሆን ማርቲን በርናል እንዳጠናው የጉራጌ ቋንቋዎች እጅግ ጥንታዊና ፕሮቶ ሊሳን ነው። ስለዚህ ከዚህ ቦታ ፈልሶ በዚህ ቀን ሸዋ ገባ የሚሉት ምንም ምርምር ያላደረጉ፣ ሊንጉዊስት ሆነ፣ አንትሮፖሎጂ ሆነ፣ ታሪክ ሆነ፣ አርኪኦዎልጂ ያላረጉ ናቸው ።

ራሳቸው የጉራጌ ልሂቃንም በውል ያላጠኑትን ተነስተው እንዲሰብኩ አንፈቅድም ። ጉራጌ የማንነት ችግር የለውም ፣ እውነተኛ ነገር በሳይንስ ተደግፎ ወደፊት ሁሉም ይታወቃል ። ይህ የጅንኢእቲክስ ዘመን ነውና ።

Fillmore88
Member
Posts: 79
Joined: 16 Jan 2020, 07:13

Re: ትንሽ ስለ ጉራዕ (በላኢ በቅሊ)

Post by Fillmore88 » 01 Apr 2020, 22:37

ትንሽ ማስተካከያ
እኔ በተወለድኩበት የጉራጌ አካባቢ ጉራ, ጋፋት, ዳባት እና ሌሎችም የቦታ ስሞች አሉ:: ነገርግን የነዚህ ስሞች መኖር ጉራጌን ከጉራ መጣ ለሚባለው ተረት ተረት መልስ አይደለም

simbe11
Member
Posts: 2087
Joined: 23 Feb 2013, 13:02
Location: Addis Ababa

Re: ትንሽ ስለ ጉራዕ (በላኢ በቅሊ)

Post by simbe11 » 01 Apr 2020, 23:07

I am not saying Gurage came from Gura.
But historians said hat and their claim seem more legit that what you are saying.
If you can, could you tell us where the Gurage Semite heritage came from?
I am willing to learn...
Fillmore88 wrote:
01 Apr 2020, 22:37
ትንሽ ማስተካከያ
እኔ በተወለድኩበት የጉራጌ አካባቢ ጉራ, ጋፋት, ዳባት እና ሌሎችም የቦታ ስሞች አሉ:: ነገርግን የነዚህ ስሞች መኖር ጉራጌን ከጉራ መጣ ለሚባለው ተረት ተረት መልስ አይደለም

Fillmore88
Member
Posts: 79
Joined: 16 Jan 2020, 07:13

Re: ትንሽ ስለ ጉራዕ (በላኢ በቅሊ)

Post by Fillmore88 » 02 Apr 2020, 00:13

A few years ago, a prominent Historian, from Holland asserting that Geez is derived from Guragegna. However our historian Dr. Lapiso wrote in his book, the semetizem existed 10,000 years ago in Ethiopia before such things in the Midlle East. To answer your question, The Gurages are Semite only by the categories of language, culturally more close to the south such as Dorze, Kembata, Wollyeta, and ....etc. to answer your question the Gurages culture and language are indigenous.

Fillmore88
Member
Posts: 79
Joined: 16 Jan 2020, 07:13

Re: ትንሽ ስለ ጉራዕ (በላኢ በቅሊ)

Post by Fillmore88 » 02 Apr 2020, 00:52

SIMBA11
The first comment that I wrote intended to HORUS not for you.

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ትንሽ ስለ ጉራዕ (በላኢ በቅሊ)

Post by Horus » 02 Apr 2020, 00:57

ጉራጌ ሴማዊነቱ በቋንቋው ነው እንጂ በካልቸሩ አይደለም የሚለው አባባል ስህተት ነው። የጉራጌን ሕዝብ ሳይንሳዊ ናሙና (ሳምፕል) ሰብስቦ፣ ትክክለኛ የጄኔቲክ ምርምር ያደረገ ሰው ብቻ ነው የጉራጌ ደም ወይም ዘር ይህን% ከዚህ ያን % ከዛ ለማለት የሚችል። ፊልሞር ስህተት ነህ ። ለምሳሌ ጉራ፣ ጋፋት፣ ዳባት ያልከው ሁሉ ስህተት ነው ። ጋፋት ጉራጌ አይደለም ። ስለዚህ ፊልሞር እውንተኛ ጉራጌ ከሆንክ የት እንደ ሆነ አስታወቀን ።

ጉራጌ የዛሬ 700 አመት አካባቢ እንሰት መትከል እንደ ተማረ ታሪክ አለ። ማለትም ከገበሬነት፣ ከከብት ማርባትና፣ ከእጅ ጥበብ (ዋናው የጉራጌ መገለጫ) ማለት ነው። የጉራጌ ወንድም የነበሩት እንደ ገብጣኖች አፈር (ደወል) አንድደው ብረት (ካስት አይረን) የሰሩ፣ የቴዎድሮስን መድፍ የሰሩ ናቸው።

የጉራጌ ቋንቋ ላጠኑ እንድ ሚያቁት እንደ ሚታወቀው ብዙ የግ ዕ ዝ ቃል ሰሩ (ኤትማው) በጉራጌ አለ ። የማህበራዊ ሴራ በተመለከተ የጎርጢ፣ የጎርደና፣ የጆካ፣ ወዘተ ሲስተሞች የሚመስሉት የጥንታዊ ግሪክ አጎራ እንጂ ሌላ አይደለም ።

እኔ ኢብላይቲክ የሚባለው እጅግ የጥንት የሴም ቋንቋ ተመልክቻለሁ ። ዩጋሪቲክ የሚባለው የአረሜይክ አባት የሆነውን ቋንቋ መዝገበ ቃል መርምሬያለሁ ፣ ዩጋሪቲክ የክርስቶስ ቋንቁ የነበረውን የአረሜይክ አባት ነው ። እነዚህ ወስጥ ሁሉ ጉራጌኛ አለ ። አረሜይክን ጉራጌ ሳይሆን አማራርኛ ተናጋሪ ሊያዳምጠው ይችላል ።

እንዲሁም ራሳቸው ጥንታዊ የሴም ቋንቋና የጥንታዊ ግብጽ ቋንቋ እንዴት ወደ ሴምነት እንደ ተለወጠ፣ ፕሮቶ ኢንዶ ኢሮፕ እንዴት ከቀምጥ (ግብጽ) እንደ ተወለደ የያውቁ የይሁዲና ጀርመን ሰዎች ስለጥንታዊ ጉራጌ ቃላት አባ እውቀት የሌላቸው ጉራጌ ቋንቋ ክሲዳማ ምናምን ተደባለቀ የሚሉ ሁሉ የተሳሳቱ ናችው።
Last edited by Horus on 02 Apr 2020, 01:24, edited 2 times in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ትንሽ ስለ ጉራዕ (በላኢ በቅሊ)

Post by Horus » 02 Apr 2020, 01:55

ፍልሞርና ሌሎች፡

አንድ ምሳሌ ላሳይችሁ፣ በግዕዝና ጉራጌኛ መሃል ያለው ዝምድና እና የማያውቁ ሰዎች ስለሚያደርጉት ስህተት ።

አሁን ግዜው አቢይ ጾም ነው። ስለሆነም ጾም የሚለውን ቃል ያልሰማ ሰው የለም ። እንዲሁም አማኞች ለጾም እና ጸሎት ሱባኤ የገባሉ ። ስለዚህ ብዙ ሰዎች ሱባኤ የሚለውን ቃል ያውቃሉ ። ታዲያ የጾም እና ሱባ ሚሉት ቃላት ሰር ያለው የት ነው።

ጾም
ሱባኤ

መጾም ማለት ከሁሉም ነገር መገለል፣ መለየት ማለት እንደ ሆነ ቤተስኪያን የሄደ ሁሉ ያቃል። ግን አንድ ጉራጌኛ ተናጋር ጾማ፣ ጦማ ሲባል የሚሰማው ብቻ፣ ብቸኛ፣ አንድ ሰው (አሎን) የሚለውን ተራ ቃል ነው። ጦማደ ነሀ ማለት ብችሃን ነህ፣ ብቻህን ምጣ ማለቱን ነው። ስለዚህ ጾማ፣ ቶማ/ቱማ ወይም ጦማ ማለት ብቻ፣ አንድ ብቻ (ኢንዲቪጇል) ማለት ነው። የቃሉ እጅግ ጥንታዊ ስር አንድ ሰው ማለት ነው።

ሰዎች ሱባኤ ይገባሉ ። ሌላው ቀርቶ ታላቁ መናገሻ ፓርክ (መናፈሻ) ራሱ ሱባ ፓርክ ይባላል። ያም ማለት ነገስታትና መነኩሳት ሱባኤ የሚገቡበት ቦታ ማለት ነው። ታዲያ ሱባኤ የሚለው ግዕዝ ስር ቃል ምንድን ነው?

በጉራጌኛ ጉባ ማለት ብቻ ማለት ነው። ያ ነው ስሩ ። ጉባ፣ ሱባ፣ ማለትና ጦማ፣ ጾማ፣ ማለት ሁሉም በጉራጌ ቋንቋ አሉ ። ይህን አይነት ምሳሌዎች በመቶች ማቅረብ እችላለሁ ።

ሙሉ እውቀት የኤላቸው የቋንቋ ተመራማሪዎች ጦማ፣ ቱማ፣ ወዘተ የደቡብ ወይም ያገው ድምጽ ስለመሰሉ ጉራጌኛ የደቡብ ድብልቅ ነው ማለታቸው የራሳቸው እውቀት ውሱንነት ያሳያል ። በቃ !

Fillmore88
Member
Posts: 79
Joined: 16 Jan 2020, 07:13

Re: ትንሽ ስለ ጉራዕ (በላኢ በቅሊ)

Post by Fillmore88 » 02 Apr 2020, 08:02

Horus
I’m gladly to tell you where it’s. GAFAT AND GURA you find them the district of Cheha. As to Dabat, it’s in the district of Eza. You can verify this fact from any Gurage coming from those area. As a matter of fact I’ll Add more interesting cultural fact from that area, which is when the king are crowned the women wore a kind of bracelet called Gonder.

Aurorae
Member
Posts: 635
Joined: 10 Nov 2019, 02:21

Re: ትንሽ ስለ ጉራዕ (በላኢ በቅሊ)

Post by Aurorae » 02 Apr 2020, 09:09

Guys,

If anything, this discussion shows how complex the Gurage society is. But, historians in the third world for the most part sell sensationalism based on emotions not reality. I am not convinced that the man from Gurae is related to the Gurage man, any more than the Oromo man or the amhara man. There is a profound reason why we all look alike and speak with languages that are derivatives of each other. Gurae sounds like Gurage and Gurage is from Gurae? :lol: :lol: However. if it could bring harmony between the two people, that is not a bad thing. It just does not sound logical. Aside from all that, the only Gurages I am related to are, only the young beautiful Gurage girls. You bet I am :lol: :lol: :lol:

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ትንሽ ስለ ጉራዕ (በላኢ በቅሊ)

Post by Horus » 02 Apr 2020, 14:27

Filmore88

በጣም ጥሩ፤
(1) ጎንደር ስላልከው፣ እና ጋፋት፣ ጉራ በቸሃ እና ዳባት በእዣ እንመልከት ።

የጉራጌ ሴቶች ሲዳሩ ጎንደር የሚባል የራስ ጌጥ ያደርጋሉ ስላከው ትክክል ነህ ። ነገር ግን ለምን ያንን ነገር እንዳመጣህው አልገለጽክም ። በሃረጉ ውስጥ ከሚደረገው ወይይት ጋር ምን አገናኘው? እዚህ ያለው ነገር አንዱ፣ ጉራጌ ከጉራ መጣ ወይ ሌላው ጉራ ማለት ምን ማለት ነው የሚሉት ናቸው።

ይህም ሆነ ያ፣ ስለሴቶቹ የራስ ጌጥ ያላወቅከው ነገር ልንገርህ ። ይህ ጌጥ በሰባት ቤት ጎንደር ወይም ጎንደራ ስለመባሉ አንተ ታውቅ ይሆናል ። እኔ ተወልጄ ባደኩበት ክስታኔ ጎንደራ ይባላል ።
የቃሉ ሊተራል ትርጉም የራስ ጌጥ ማለት ነው። ጉነን ማለት ጉራጌኛ ታውቅ ከሆነ ራስ ማለት ነው። በግዕዝ ጉና እንደ ሚባለው ማለት ነው፤ ሴቶቹ ጉንጉን እንደሚሉት። ዶራ ጌጥ፣ ስጦታ ማለት ነው ። በሰሜን ጉራጌ በሰርግ ቀን ብቻ ሳይሆን ሌሎችን ሹርባ ላይ የሚሰኩ የሴት ራስ ጌጦች ጎንደራ ይባላሉ ። ይህ ነው ምስጢሩ!! ቃሉን ስላመጣሀው አመሰግናለሁ ።

በቸሃ ጉራ እና ጋፋት የሚባሉ ቦታዎች ካሉ ያንንም ስለነገርከኝ ጥሩ ነው ። እኔ እዚያ ስላላደኩ። ግን ስለቃላቱ ወይ ስለ ስሞቹ ትርጉም ሆነ ታሪክ የምተልው ነገር አለ ወይ? ልብ በል አሁን የሞተው የጋፋት ቋንቋ የሰሜን ጉራጌ ቋንቋ ተዛማጅ ልሳን እንደ ሆነ ነገሩን ያጠናው ሀርዝ ነግሮናል። በኋላ በኋላ አፈር አንድደው ካስት ብረት የሚሰሩ ጥበበኛ ጎሳ በዘልማድ ጋፋት ይባሉ ነበር ። ስለዚህ ቃሉ ብቻ ሳይሆን ስለኮንቴክስቱ ንገረን ።

ጉራ ሌላ ቀርቶ ባዲስ አበባ ዙሪያ አሁን ኦሮሞ የሆኑት ገላን ገላን ጉራ የሚባል ቦታ አለ። ስለዚህ በቸሃም ጉራ የተባለው ቦታ ጉራ የተባለው ቦታ ጋራ ስለሆነ ነው ወይስ ሌላ ትርጉም አለው? ቸሃ ጉራ ሲል ጋራ ማለቱ ከሆነ ምንም ማለት አይደለም ። ሌላ ትርጉም ካለው ንገረን። በእኔ በኩል ጉራ ማለት ምን ማለት እንደ ሆነ ከላይ ባሉት ፖስቶች ተናግሪያለሁ ።

በእዣ ያለው ዳባት፣ ጅባት ከሚለው የጉራጌ ስም ጋር ተመሳሳይ ነው።

Post Reply