Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
MINILIK SALSAWI
Member+
Posts: 7694
Joined: 24 Aug 2012, 12:02

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 22 Jun 2020, 04:34

በግብጽ የኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 55 ሺህ 233 ደርሷል፤ ትናንት ብቻ 1 ሺህ 475 ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ነው የተረጋገጠው፡፡

የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ትናንት የ87 ሰዎች ሕይወት በቫይረሱ ምክንያት አልፏል፤ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርም 2 ሺ 193 ደርሷል፡፡ የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር መረጃ እንዳመለከተው መዲናዋ ካይሮ፣ ጊዛ እና ቃሊዮቢያ አካባቢዎች ከፍተኛ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች የተመዘገቡባቸው እንደሆኑ ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡

በአፍሪካ ከደቡብ አፍሪካ በመቀጠል ከፍተኛ በቫይረሱ የተያዘ ሰው ያለባት ግብጽ ለ135 ሺህ ሰዎች ምርመራ አድርጋ ነው በ55 ሺህ 233 ሰዎች ላይ ቫይረሱን ያገኘችው፡፡

ደቡብ አፍሪካ 97 ሺህ 302 ሰዎች ቫይረሱ እንዳለባቸው በማረጋገጥ ከአህጉሩ ቀዳሚ ናት፤ ለ1 ሚሊዮን 328 ሺህ 60 ሰዎች ምርመራ በማድረግም ትመራለች፡፡ በቫይረሱ በተያዙ ሰዎች ብዛት ከአፍሪካ 15ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው ኢትዮጵያ 4 ሺህ 532 ሰዎች በቫይረሱ እንደተያዙ አረጋግጣለች፤ ለዚህም 216 ሺህ 328 ሰዎችን መርምራለች፡፡

ከደቡብ አፍሪካ፣ ሞሮኮ እና ጋና በመቀጠል ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው መመርመሯንም የጆን ሆፕኪንስ መረጃ ያመለክታል፡፡


MINILIK SALSAWI
Member+
Posts: 7694
Joined: 24 Aug 2012, 12:02

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 22 Jun 2020, 05:12

በብራዚል የሟቾች ቁጥር ከ50ሺህ ዘለለ

አገሪቱ በቫይረሱ የተያዙባት ሰዎች ቁጥር አንድ ሚሊዮን አልፏል፡፡ የማሕበረሰብ ጤና ባለሞያዎች እንደሚሉት ደግሞ በብራዚል በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር የወረርሽኝ ጣሪያውን እስኪነካ ገና ሳምንታት ይቀራሉ፡፡

https://bbc.in/2YlYw8D


MINILIK SALSAWI
Member+
Posts: 7694
Joined: 24 Aug 2012, 12:02

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 22 Jun 2020, 06:26

WHO concerned over COVID-19 impact on women, girls in Africa

Humanitarian crises, including health emergencies affect men and women differently. As COVID-19 continues to spread in Africa, there are concerns over its impact on women and girls, with vulnerabilities feared to worsen as the pandemic overwhelms health systems.

https://www.capitalethiopia.com/capital ... in-africa/

MINILIK SALSAWI
Member+
Posts: 7694
Joined: 24 Aug 2012, 12:02

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 22 Jun 2020, 06:56

NamibiaCôte d'IvoireBenin registers 2 new deaths and 115 new cases in 48 hours. As of June 20, 2020, there are a total of 765 cases confirmed with Covid-19 infection, with 499 people on treatment, 253 people cured and 13 deaths.Sudan


MINILIK SALSAWI
Member+
Posts: 7694
Joined: 24 Aug 2012, 12:02

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 22 Jun 2020, 07:32

Over 303,000 confirmed COVID19 cases on the African continent - with more than 145,000 recoveries & 7,999 deaths. View country figures & more with the WHO African Region COVID-19 Dashboard: https://arcg.is/XvuSX


MINILIK SALSAWI
Member+
Posts: 7694
Joined: 24 Aug 2012, 12:02

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 22 Jun 2020, 08:01

በአዲስ አበባ በኮሮናቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ከ3000 በለጠ

በአዲስ አበባ ከተማ በኮሮናቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 3,105 ደርሷል። ይህ የቫይረሱ ስርጭት ደግሞ በስፋት የሚታይባቸው ክፍለ ኢትዮጵያ ተሰራጭቶ የሚገኝ ሲሆን እስካሁን ድረስ በዚሁ የተነሳ የ74 ሰዎችን ህይወትም አልፏል። ኮሮናቫይረስን ለመቆጣጠር እያንዳንዱ ሰው ከመንግሥትና ከባለሙያዎች የሚሰጡ መመሪያዎችን ተግባራዊ ሊያደርግ እንደሚገባ ባለሙያዎች ዘወትር ይናገራሉ።

https://www.bbc.com/amharic/live/53133218

MINILIK SALSAWI
Member+
Posts: 7694
Joined: 24 Aug 2012, 12:02

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 22 Jun 2020, 08:19

የኮቪድ-19 አንቲቦዲ (Antibody) የቅኝት ዳሰሳ አስመልክቶ የወጣ መግለጫ

በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ምርመራ ከጥር 29 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ የተጀመረ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ በሁሉም ክልሎች በሚገኙ ላቦራቶሪዎች እስከ ሰኔ 14 ቀን 2012 ዓ.ም 216¸328 ምርመራ ተደርጓል። ይህ የምርመራ አይነት የኮቪደ-19 በሽታ ያለበት ሰው ላይ ቫይረሱን ለመለየት የሚረዳ የሞለኪዩላር ምርመራ ነው። ከዚህ በተጨማሪ በማህበረሰብ ውስጥ ያለውን የበሽታ ስርጭት ለመረዳት (surveillance) እና በአንጻሩ ምላሽ ለመስጠት እንዲሁም ይበልጥ ተጋላጭ በሆኑት የማህበረሰባችን ክፍሎች ላይ ያለውን የኮቪድ-19 በሽታ ስርጭት ለማወቅ የሚረዳ አንቲቦዲ ምርመራ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑ ይታመናል፡፡ ይህ የአንቲቦዲ የቅኝትና ዳሰሳ ምርመራ አይነት በአገራችን ለምርምር ለመጠቀም እና ከላይ የተጠቀሱትን ዓላማዎች ለማሳካት ከሰኔ 15 እሰከ ሀምሌ 7 ቀን 2012 ድረስ በሀገራችን የሚካሄድ ይሆናል።

አንቲቦዲ ማለት ሰውነታችን ለበሽታ በሚጋለጠበት ወቅት ለበሽታው ከተጋለጠ ከአንድ እስከ ሶስት ሳምንት ድረስ በሽታውን ለመከላከል ሰውነታችን የሚያመርታቸው የበሽታ ተከላካዩች ናቸው፡፡ በሰውነታችን ውስጥ የአንቲቦዲ መመረት በእድሜ፣ የአመጋገብ ሁኔታ፣ የምንጠቀማቸው መድሁኒቶች፣ የበሽታው ከባድነት እና ተጓዳኝ በሽታዎች ላይ ይወሰናል፡፡ ምርመራው ከሰውነታችን ከ3-5 ሚሊ ሊትር ደም ናሙና በመውሰድ የሚደረግ ሲሆን የበሽታው ተከላካዮች (አንቲቦዲ) እንደየበሽታው ዓይነት የሚለያዩ ሲሆን ምርመራው ኮቪድ-19 ለመካላከል እና ለ መቆጣጠር ለሚደረገው የቅኝት ዳሰሳ ውጤታማነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው፡፡ ነገር ግን የአንቲቦዲ ምርመራ ውጤትን ብቻ ተጠቅሞ ህክምና መስጠት አይቻልም፡፡

ይህ የቅኝት ዳሰሳ በሀገራችን ያለውን የኮሮና ቫይረስ በሽታ (ኮቪድ-19) ስርጭት ለማወቅ ከሰኔ 15 ቀን 2012 ጀምሮ በአዲስ አበባ፣ ድሬደዋ ከተማ አስተዳደሮችን ጨምሮ በሁሉም ክልሎች ይካሄዳል፡፡ በመሆኑም ህብረተሰቡ፣ የጤና ባለሙያዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ለትግበራው አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ እንጠይቃለን፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 በመደወል ወይም በኢሜል አድራሻችን [email protected] በመጠቀም ወይም ባሉበት ክልል በተዘጋጁ ነፃ የስልክ መስመሮች በመደወል ሪፖርት እንዲያደርጉ ወይም በአካባቢው ለሚገኙ ጤና ተቋማት በስልክ እንዲያሳውቁ እንጠይቀለን፡፡

ሰኔ 15 ቀን 2012 ዓ.ም


MINILIK SALSAWI
Member+
Posts: 7694
Joined: 24 Aug 2012, 12:02

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 22 Jun 2020, 08:50

Somaliland Ministry of Health Development records 7 new COVID19 cases in the last 24 hours, bringing the total cases to 663 positive and 28 death. Total Recovery is 147 .
MINILIK SALSAWI
Member+
Posts: 7694
Joined: 24 Aug 2012, 12:02

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 22 Jun 2020, 10:04

በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓታት ተጨማሪ 1 ሰው የኮሮናቫይረስ ተገኘበት፤ 15 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል፡፡

በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓታት ለ601 ናሙናዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ በአንድ ወንድ ላይ ቫይረሱ መገኘቱን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡

ቫይረሱ የተገኘበት የ19 ዓመት ወጣት በሰሜን ሸዋ ዞን ሞጃና ወደራ ወረዳ በለይቶ ማቆያ ያለ መሆኑን ተገልጧል፡፡

በአማራ ክልል እስከ ዛሬ ሰኔ 15/2012 ዓ.ም ድረስ ለ10 ሺህ 521 ሰዎች የናሙና ምርመራ ተደርጎ በ 275 ሰዎች ላይ ቫይረሱ መገኘቱን የአማራ ክልል ጤና ቢሮ አስታውቋል።

በክልሉ ባለፉት 24 ሰዓታት 15 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል፤ ዛሬ በቫይረሱ ምክንያት ሕይወቱ ያለፈም ሆነ በጽኑ ሕመም የሚገኝ ሰው እንደሌለ ቢሮው አስታውቋል፡፡

ቫይረሱ ተገኝቶባቸው በለይቶ ሕክምና መስጫ ማዕከላት የሚገኙ ሁሉም ታካሚዎች በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙም ተገልጧል፡፡


MINILIK SALSAWI
Member+
Posts: 7694
Joined: 24 Aug 2012, 12:02

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 22 Jun 2020, 10:22

COVID-19 LIVE updates

US coronavirus deaths near 120,000
India's infections soaring in rural areas
Thailand reports 3 new imported cases
New Zealand to extend ban on cruise ship arrivals


https://aje.io/mkz9u

Indonesia's COVID-19 death toll reaches 2500, with over 46,000 infections - https://aje.io/2x4t6

South Korea says it is battling a 'second wave' of coronavirus | https://aje.io/y7b8g

MINILIK SALSAWI
Member+
Posts: 7694
Joined: 24 Aug 2012, 12:02

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 22 Jun 2020, 10:45

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት በፖለቲካ ምክንያት መባባሱን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ
****************
የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ውስጥ ዓለም አቀፍ አመራር እና አንድነት አለመኖሩ ከወረርሽኙ ይበልጥ ትልቅ ስጋት መደቀኑን የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ገለጹ።

ወረርሽኙን ፖለቲካዊ የማድረጉ ነገር ደግሞ ነገሮችን ይበልጥ ያወሳሰበ መሆኑን ተናግረዋል።

ዋና ኃላፊው በግልጽ ባያብራሩትም የዓለም ጤና ድርጅት በአንዳንድ ሀገራት በተለይም በአሜሪካ ሲተች ቆይቷል።

አሜሪካ ድርጅቱ በሽታውን ከመከላከል አንፃር የተዳከመ እንዲሁም ቻይናን ማዕከል ያደረገ ነው የሚል ትችት ስታቀርብበት ቆይታለች።

ሌሎች ሀገራት ደግሞ ድርጅቱ ወረርሽኙን በተመለከተ የወሰደውን እርምጃ ዳግም እንዲያየው ጠይቀዋል።

አውስትራሊያ በበኩሏ ድርጅቱ ለጤና ቀውሶች አፋጣኝ ምላሽ ይሰጥ ዘንድ የበለጠ ኃይል እንደሚያስፈልገው አሳስባለች።

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ኃላፊ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በዓለም መንግሥታት ጉባዔ አስተባባሪነት በዱባይ በተዘጋጀው እና በኢንተርኔት በተካሄደው የጤና ፎረም ላይ ባደረጉት ንግግር፣ "ዓለማችን የሀገራት አንድነት እና ዓለም አቀፍ ትብብር በሚያስፈልጋት ወሳኝ ጊዜ ላይ ትገኛለች፤ ወረርሽኙን ፖለቲካዊ ማድረግም ጉዳዩን ይበልጥ አባብሶታል" ብለዋል።

"አሁን ያጋጠመን ትልቁ ስጋት ቫይረሱ ራሱ ሳይሆን የዓለም አቀፍ ትብብር እና ዓለም አቀፍ አመራር እጦት ነው" ሲሉም አክለዋል።
አንዳንድ ዓለም አቀፍ የጤና ሕጎች ግቦቻቸውን መምታት እንዲችሉ የግድ መጠናከር እንደሚገባቸውም አሳስበዋል።

የትኞቹ የሕጎቹ ክፍሎች መጠናከር እንደሚገባቸው በይፋ ባይጠቅሱም ሕጎቹን በሙሉ አቅም ለመተግበር በአግባቡ የተደራጁ፣ የሚተነበዩ፣ ግልጽነት ያላቸው፣ መሠረተ-ሰፊ የሆኑ እና በቂ በጀት ያላቸው ማድረግ ይገባል ሲሉም አክለዋል።

ጠንካራ የጤና አጠባበቅ ሥርዓት ለዓለም አቀፍ የጤና ደህንነት እንዲሁም ለማኅበራዊ እና ለኢኮኖሚያዊ ዕድገት መሠረት መሆኑን ያስታወሱት ዶ/ር ቴድሮስ፣ ሁሉም ሀገራት ዓለም አቀፍ የጤና አጠባበቅን ቀዳሚ ሥራቸው ማድረግ ይገባቸዋል በማለት ማሳሰባቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።


MINILIK SALSAWI
Member+
Posts: 7694
Joined: 24 Aug 2012, 12:02

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 22 Jun 2020, 11:02

ADDIS ABEBA Covid 19 Update

በአዲስ አበባ ከተማ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 3203 ደረሰ

በአዲስ አበባ በ 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላቦራቶሪ ምርመራ ዘጠና ስምንት (98) ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን፣ በከተማው ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ሶስት ሺህ ሁለት መቶ ሶስት (3203) ደርሷል፡፡

ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ በከተማው በተደረጉ የአስከሬን ምርመራዎች አንድ (1) ሰው በበሽታው ሕይወቱ አልፏል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ በትላንትናው እለት ሰባ ዘጠኝ (79) ሰዎች ከአዲስ አበባ ከኮሮና በሽታ አገግመዋል፡፡


Last edited by MINILIK SALSAWI on 22 Jun 2020, 14:21, edited 2 times in total.MINILIK SALSAWI
Member+
Posts: 7694
Joined: 24 Aug 2012, 12:02

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 22 Jun 2020, 12:18

SOMALIA

> New cases confirmed today: 33
> Puntland: 21
> Somaliland: 7
> Galmudug: 5

> Male: 30
> Female: 3
> Recovery: 36
> Death: 0
----------------------
Total confirmed cases: 2,812
Total recoveries: 818
Total deaths: 90MINILIK SALSAWI
Member+
Posts: 7694
Joined: 24 Aug 2012, 12:02

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 22 Jun 2020, 14:00

Global COVID-19 cases surpass 9 million

Brazil passes 50,000 coronavirus deaths
WHO says it will issue guidance on air travel in coming days
The Netherlands records no deaths for first time since March


https://aje.io/bycuj


Post Reply