Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
MINILIK SALSAWI
Member+
Posts: 9495
Joined: 24 Aug 2012, 12:02

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 06 Sep 2020, 13:40

Over 1.2 million confirmed COVID19 cases on the African continent - with more than 1 million recoveries & 31,000 deaths cumulatively.

View country figures & more with the WHO African Region COVID-19 Dashboard: https://arcg.is/XvuSX



MINILIK SALSAWI
Member+
Posts: 9495
Joined: 24 Aug 2012, 12:02

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 06 Sep 2020, 13:53








MINILIK SALSAWI
Member+
Posts: 9495
Joined: 24 Aug 2012, 12:02

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 07 Sep 2020, 01:17

WHO ስለኮሮና ቫይረስ ክትባት!

ለኮቪድ-19 መከላከያ የሚሆን ደህንነቱ የተረጋገጠና ውጤታማ የሆነ ክትባት በስፋት ጥቅም ላይ ለማዋል እስከ መጭው የአውሮፓውያን አመት አጋማሽ ላይደርስ እንደሚችል የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል።

ሰዎች ክትባቱ ፈጥኖ ሊደርስልን ነው የሚለውን ጉጉትና ተስፋ በልክ እንዲያደርጉ የጤና ባለስልጣናት እየመከሩ ይገኛሉ።

በጤና ላይ አደጋ የማያስከትልና በደንብ ውጤት የሚያመጣ ክትባት እንደዚሁ በይድረስ ይድረስ ተቻኩሎ መስራት የሚሆን አይደለም፤ጊዜ ይጠይቃልም ብለዋል።

የዓለም ጤና ድርጅት ክትባት ፍለጋው በተገቢው መንገድ የማከናወኑ ሂደት በደንብ እየተካሄደ እንደሆነ እየገለፀ ነው።

ከስድስት እስከ ዘጠኝ የሚደርሱ ክትባቶች በአሁኑ ጊዜ በሶስተኛ ምዕራፍ የሰው ሙከራ ደረጃ ላይ እንደሚገኙም አመልክቷል።

በእነዚህ በጥንቃቄ በተዘጋጁት ሙከራዎች በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እየተሳተፉ መሆናቸው የWHO ቃል አቀባይ ማርጋሬት ሃሪስ ገልፀዋል።

የኮሮና ቫይረስ ክትባት ጥቅም ላይ እንዲውል ከመፈቀዱ በፊት የጤና ስጋት የማያስከትልና ቢያንስ በሙከራው ከሚሳተፉት 50 በመቶውን ከቫይረሱ መከላከል መቻሉ መረጋገጥ አለበት ሲሉ አሳስበዋል።

አያይዘው በተጨባጭ ያለውን ሁኔታ ካየን ከመጭው የአውሮፓውያን 2020/2021 አጋማሽ በፊት ክትባት ለህዝብ መስጠት ይጀመራል ብለን አንጠብቅም ብለዋል።

ከዚህ ባለፈም ቃል አቀባይ ማርጋሬት ሃሪስ ለቬኦኤ እንደተናገሩት መንግስታት ክትባት መቼ በአጣዳፊ ሁኔታ ወይም ለአጠቃላይ ጥቅም እንደሚያውሉ WHO አይነግራቸውም የየራሳቸውን ውሳኔ መውሰድ አለባቸው ሲሉ ተናግረዋል። ነገር ግን ይህን ወረርሽኝ ድራሹን የሚያጠፋ ክትባት እየደረሰ ነው ብሎ ለህዝብ ያልሆነ ተስፋ መስጠት እንደማይገባ እናስጠነቅቃለን ማለታቸውን ቪኦኤ ዘግቧል።

MINILIK SALSAWI
Member+
Posts: 9495
Joined: 24 Aug 2012, 12:02

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 07 Sep 2020, 08:23

"ኮሮናቫይረስ ጠፋም አልጠፋ" በሚቀጥለው ዓመት ኦሊምፒክ ይካሄዳል ተባለ

በኮሮናቫይረስ ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሞ የነበረው የቶኪዮ ኦሊምፒክ በሚቀጥለው ዓመት በማንኛውም ሁኔታ እንደሚካሄድ ዓለም አቀፉ የኦሎምፒክ ኮሚቴ አስታወቀ።
የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ምክትል ፕሬዝዳንት "ኮቪድ-19 ጠፋም አልጠፋ በሚቀጥለው ዓመት ኦሊምፒክ ይካሄዳል" ብለዋል።
ጆን ኮትስ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንዳረጋገጡት በሚቀጥለው ዓመት ኦሊምፒክ የሚጀምረው በሐምሌ 23 ይሆናል።
ኦሊምፒክ መካሄድ የነበረበት ዘንድሮ በሐምሌ ወር ነበር። ሆኖም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት ተከትሎ ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሞ ነበር።
ሆኖም ውድድሩን እ.ኤ.አ ከ2021 ወዲያ መግፋት ስሜት የሚሰጥ ነገር አይደለም ብለዋል።
በሐምሌ ወር የቶክዮ 2020 ኦሊምፒክ ሊቀመንበር ቶሺሮ ሙቶ "ውድድሮቹን በዝግ ስታዲየም ማካሄድ ይቻል ነበር። ያንን ስላልፈለግን ነው ያዘገየነው" ብለው ነበር።
ምናልባት ከየአገሩ የሚመጡ ወኪሎችን ቁጥር በመቀነስ፣ በየውድድሩ የሚታደሙ ተመልካቾችን በማሳነስ፣ እንዲሁም የመክፈቻና መዝጊያ ሥነ ሥርዓቱን ቀለል በማድረግ የሚካሄድበት መንገድ ሊቀየስ ይችላል።
ከመላው ዓለም 11 ሺህ አትሌቶች ከ200 አገራት እንደሚገኙ ይጠበቅ ነበር።
በሚቀጥለው ዓመት ሐምሌ ላይ ውድድሩ ሲታሰብ የጉዞ ገደቦችን በተመለከተ የተባለ ነገር የለም።
ሚስተር ሙቶ የኦሊምፒክ ውድድሩን ለማድረግ የኮቪድ-19 ክትባትን መጠበቅ አይኖርብንም ብለዋል። የጤና ባለሙያዎች በበኩላቸው በወረርሽኝ መሀል ክትባት ሳይኖር እንዲህ ዓይነት ውድድር ሊካሄድ አይችልም ይላሉ።
"ክትባት ከተገኘ መልካም፤ ካልተገኘ ግን እሱ እስኪገኝ ኦሊምፒክ አይቆምም" ብለዋል ሊቀመንበሩ።
የውድድሩ አስተባባሪ ዮሺሮ ሞሪ በሚያዝያ ወር ኦሊምፒክ በ2021 ካልተደረገ እስከናካቴው መሰረዝ ነው ያለበት ብለው ነበር።
ከዚህ ቀደም የኦሎምፒክ ውድድር በጦርነት ምክንያት ሳይካሄድ ቀርቶ ያውቃል እንጂ የሚካሄድበት ጊዜ ሲገፋ ይህ በታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ መሆኑን ቢቢሲ በዘገባው አመልክቷል።

MINILIK SALSAWI
Member+
Posts: 9495
Joined: 24 Aug 2012, 12:02

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 07 Sep 2020, 09:54


MINILIK SALSAWI
Member+
Posts: 9495
Joined: 24 Aug 2012, 12:02

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 07 Sep 2020, 10:21

Please wait, video is loading...

MINILIK SALSAWI
Member+
Posts: 9495
Joined: 24 Aug 2012, 12:02

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 07 Sep 2020, 10:40

COVID-19 LIVE updates

Over 200 UN staff in Syria infected
Malaysia fears new coronavirus cluster
Mexico reports more than 4,600 new cases
Russia to complete early-stage trials on vaccine


https://aje.io/qjfgc



India overtakes Brazil as country second-worst-hit by COVID-19, with over 4.2 million cases https://aje.io/9bazp

More than 200 UN staff in Syria test positive for COVID-19 https://aje.io/jqvpz

MINILIK SALSAWI
Member+
Posts: 9495
Joined: 24 Aug 2012, 12:02

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 08 Sep 2020, 06:06


MINILIK SALSAWI
Member+
Posts: 9495
Joined: 24 Aug 2012, 12:02

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 08 Sep 2020, 06:22


MINILIK SALSAWI
Member+
Posts: 9495
Joined: 24 Aug 2012, 12:02

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 08 Sep 2020, 10:09

በሀገራችን ስለ ኮሮና ቫይረስ ያለው ግንዛቤና የመከላከያ መመሪያዎች ተግባራዊነትስ ምን ይመስላል?

ሊንኩን በመጫን ትዝብታችሁን አካፍሉን?


https://forms.gle/zMLsUPMUjrNpkeCj9

MINILIK SALSAWI
Member+
Posts: 9495
Joined: 24 Aug 2012, 12:02

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 08 Sep 2020, 11:03

WORLDWIDE COVID 19 UPDATE

Coronavirus Cases: 27,556,030
Deaths: 897,922
Recovered: 19,654,325


Active Cases

Currently Infected Patients : 7,003,783
In Mild Condition : 6,943,503 (99%)
Serious or Critical : 60,280 (1%)


MORE : https://www.worldometers.info/coronavirus/#countries

MINILIK SALSAWI
Member+
Posts: 9495
Joined: 24 Aug 2012, 12:02

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 08 Sep 2020, 11:15

በነሐሴ ወር ብቻ በኢትዮጵያ ከ37 ሺህ በላይ ዜጎች ኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል .. የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ

(ኢዜአ) በነሐሴ ወር በተደረገ የምርመራና የንቅናቄ ዘመቻ ከ37 ሺህ በላይ ዜጎች የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለጹ።ሚኒስትሯ ዛሬ እንዳስታወቁት በነሐሴ ወር የማኅበረሰብ ንቅናቄና የምርመራ ዘመቻው በሁሉም የአገሪቱ ክልሎች ተካሂዷል።በዚህም 1 ሺህ 95 ወረዳዎችን በማዳረስ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ለቫይረሱ ተጋላጭ የሆኑ የማኅበረሰበ ክፍሎችን ለማግኘት እንደተቻለ ጠቁመዋል።

ዘመቻው ከተጀመረ ጀምሮ በድምሩ 575 ሺህ ሰዎችን መመርመር እንደተቻለና በቀን የመመርመር አማካይ አቅም 19 ሺህ መድረሱንም ተናግረዋል።በዚህም በነሐሴ ወር ብቻ 37 ሺህ 748 ሰዎች ቫይረሱ እንዳለባቸው በምርመራ መረጋገጡን ነው ሚኒስትሯ የገለጹት።“ይህም እስካሁን በአገሪቱ በአጠቃላይ ከተያዙት ሰዎች ቁጥር 64 በመቶውን ይሸፍናል” ብለዋል።

በቫይረሱ በጠና የታመሙ ሰዎች ቁጥር በማሻቀቡ በፊት ከነበረበት 1 በመቶ በአሁኑ ወቅት 4 ነጥብ 5 በመቶ መድረሱን ገልጸዋል።ከንቅናቄው በፊት በቫይረሱ ምክንያት 368 ሰዎች ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን ከንቅናቄው በኋላ ይህ አሀዝ ወደ 550 ከፍ ማለቱንም ዶክተር ሊያ አመልክተዋል።እስከ ነሐሴ መጨረሻ ድረስ በአጠቃላይ ከወረርሽኙ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 21 ሺህ መድረሱንም ተናግረዋል።

“ምንም እንኳን በዘመቻው ኅብረተሰቡ ስለ ኮሮናቫይረስ ያለውን ግንዛቤ ማሳደግ ቢቻልም ወረርሽኙ አሁንም በስፋት እየጨመረ መጥቷል” ብለዋል።
በዚህም በጽኑ የሚታመሙና ህይወታቸውን የሚያጡ ሰዎችም ቁጥር እየጨመረ መሆኑን ጠቁመው ለዚህም የኅብረተሰቡ መዘናጋትና ቸልተኝነትን በምክንያትነት ጠቅሰዋል።

ዶክተር ሊያ እንዳሉት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በሁሉም የዕድሜ ክልል ላይ መሰራጨቱን በዚሁ የማኅበረሰብ ንቅናቄ ወቅት ለማወቅ ተችሏል።አሁንም ከጤና ባለሙያዎች የሚቀርቡትን የመከላከያ ስልቶች ኅብረተሰቡ ተግባራዊ የማያደረግ ከሆነ ወረርሽኙ ከዚህ በላይ እንደሚዛመት አስጠንቅቀዋል።
በመሆኑም በአዲሱ ዓመት ኅብረተሰቡ ለቫይረሱ ተጋላጭ እንዳይሆን ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት አሳስበዋል።

ከንቅናቄው የተቀመረውን ልምድ በመውሰድ ኮቪድ-19ኝን ጨምሮ ሌሎች በሽታዎችን ለመከላከል በትኩረት እንደሚሰራም ሚኒስትሯ አረጋግጠዋል።በተመሳሳይ በዚሁ የነሐሴ ወር ሌሎች መደበኛ የጤና አገልግሎቶች እንዳይስተጓጎሉ በርካታ ሥራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውንም ገልጸዋል። ለአብነትም የቢጫ ወባ፣ ኮሌራና ኩፍኝ ወረርሽኞች በኅብረተሰቡ ላይ የከፋ ጉዳት ሳያስከትሉ መቆጣጠር መቻሉን አስረድተዋል።




የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን በመቆጣጠር ሂደት በጎ ላደረጉ እውቅና ተሰጠ

የጤና ሚኒስቴር የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን በመከላከልና በመቆጣጠር ሂደት ውስጥ ኃላፊነታቸውን ለተወጡና በጎ ላደረጉ አካላት የአምባሳደርነት እውቅና ሰጥቷል፡፡የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ የአምባሳደርነት እውቅና ስንሰጥ አንድም እስካሁን ለሰሩት በጎ ስራ ምስጋና በሌላ በኩል ደግሞ ለወደፊቱ የቫይረሱን ስርጭት በመቆጣጠሩ ስራ ላይ ይህንኑ ተግባራቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ኃላፊነት እየሰጠን ነው ብለዋል፡፡

የጤና ሚኒስቴር የኮሮና ወረርሽኝን በመከላከልና መቆጣጠር ሂደት ውስት በጎ አድርገዋል ላላቸው ለኢትዮጵያ ሀይማኖት ተቆማት ጉባኤ፣ ለኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ዳዊት ከበደ እንዲሁም ለአርቲስት ሰለሞን ታሼ ጋጋ የአምባሳደርነት እውቅና ሰጥቷል፡፡

የኢትዮጵያ ሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ጸሀፊ ቀሲስ ታጋይ ታደለ ወረርሽኙን ለመቆጣጠር ሲባል ቤተክርስትያንና መስጂዶች እንዲዘጉ ሲወሰን ውሳኔውን ለተቀበሉ፣ ህብረተሰቡን ላስተባበሩ እና ለተገበሩ የሀይማኖት አባቶች ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

ወቅቱ ሁሉም በየሀይማኖቱ ጾምና ጸሎት ሊያረግበት የሚገባ በመሆኑም በተመረጡ የቴሌቪዝን ጣቢያዎች ሀይማኖታዊ መርሀግብሮች እንዲተላለፍ ተደርጓል ብለዋል፡፡

ዶ/ር ዳዊት ከበደ የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ እውቅናው ባልተመቸ ሁኔታ ውስጥ ከቤተሰቦቻቸው ተነጥለው ወረርሽኙን ለመቆጣጠር እየሰሩ ላሉ የህክምና ባለሙያዎች ይበልጥ ብርታት የሚሰጥ ነው ብለዋል፡፡

ህብረተሰቡም የቫይረሱ ስርጭት ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ በመሆኑ የመከላከያ ዘዴዎችን በመተግበር ከጤና ባለሙያዎች ጎን እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
አርቲስት ሰለሞን ታሼ ጋጋ በበጎ ፍቃደኝነት በተሸከርካሪው ላይ የተለያዩ ስለ ቫይረሱ ግንዛቤ የሚያስጨብጡ ጽሁፎችን በመለጠፍና በማስተማር ለሰራው የበጎ ፍቃድ ስራ ጤና ሚኒስቴር የአምባሳደርነት እውቅና ሰጥቶታል፡፡

MINILIK SALSAWI
Member+
Posts: 9495
Joined: 24 Aug 2012, 12:02

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 08 Sep 2020, 13:01


MINILIK SALSAWI
Member+
Posts: 9495
Joined: 24 Aug 2012, 12:02

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 08 Sep 2020, 13:14


MINILIK SALSAWI
Member+
Posts: 9495
Joined: 24 Aug 2012, 12:02

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 09 Sep 2020, 04:21


MINILIK SALSAWI
Member+
Posts: 9495
Joined: 24 Aug 2012, 12:02

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 09 Sep 2020, 04:55


MINILIK SALSAWI
Member+
Posts: 9495
Joined: 24 Aug 2012, 12:02

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 09 Sep 2020, 05:15


MINILIK SALSAWI
Member+
Posts: 9495
Joined: 24 Aug 2012, 12:02

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 09 Sep 2020, 08:42

COVID-19 pandemic hurting efforts to curb child mortality in 77 countries, says UN report

https://aje.io/j3jve



MINILIK SALSAWI
Member+
Posts: 9495
Joined: 24 Aug 2012, 12:02

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 10 Sep 2020, 03:20




MINILIK SALSAWI
Member+
Posts: 9495
Joined: 24 Aug 2012, 12:02

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 10 Sep 2020, 03:42


Post Reply