Page 1 of 1

ኦነግ/ሸኔ በቀድሞው የነቀምት ከተማ አስተዳደር እና የፀጥታ ፅ/ቤት ኃላፊ ላር እርምጃ ወስዶ ገደለውለ!!

Posted: 25 Mar 2020, 15:11
by Gallo
ኦነግ/ሸኔ በቀድሞው የነቀምት ከተማ አስተዳደር እና የፀጥታ ፅ/ቤት ኃላፊ ላር እርምጃ ወስዶ ገደለውለ!!

የቀድሞው የነቀምት ከተማ አስተዳደር እና የፀጥታ ፅ/ቤት ኃላፊ በመኖሪያ ቤታቸው መገደላቸው ተሰማ፡፡ የቀድሞው የከተማዋ አስተዳደር እና ፀጥታ ኃላፊ አቶ ተሾመ ገነቴ ዛሬ በ10 ሰዓት አካባቢ በመኖሪያ ቤታቸው ሳሉ መገደላቸውን ሰምተናል፡፡ወሬውን ለሸገር የተናገሩት የኦሮሚያ ክልል የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ ናቸው፡፡አቶ ተሾመ በማን እንደተገደሉ በምርመራ ላይ መሆኑንም የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊው ለሸገር ተናግረዋል፡፡

Via Sheger FM




Re: ኦነግ/ሸኔ በቀድሞው የነቀምት ከተማ አስተዳደር እና የፀጥታ ፅ/ቤት ኃላፊ ላር እርምጃ ወስዶ ገደለውለ!!

Posted: 25 Mar 2020, 15:12
by Gallo

Re: ኦነግ/ሸኔ በቀድሞው የነቀምት ከተማ አስተዳደር እና የፀጥታ ፅ/ቤት ኃላፊ ላር እርምጃ ወስዶ ገደለውለ!!

Posted: 25 Mar 2020, 15:16
by Gallo
BBC Amharic News

የነቀምቴ ከተማ የቀድሞ የደህንነት ጽ/ቤት ኃላፊ ተገደሉ

የነቀምቴ ከተማ የቀድሞ የአስተዳደር እና የደህንነት ጽ/ቤት ኃላፊ ዛሬ ከሰዓት መገደላቸውን ምንጮች ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።

አቶ ተሾመ ገነቲ መኖሪያ ቤታቸው አቅራቢያ በጥይት ተመተው መገደላቸውን ጉዳዩን ከሚያውቁ ሰዎች ማወቅ ተችሏል።

ነገር ግን የነቀምቴ ከተማ የአስተዳድር እና ደህንነት ጽ/ቤት ኃላፊን ማን እንደገደላቸው እስካሁን አልታወቀም።

የኦሮሚያ ክልል የአስተዳደር እና ደህንነት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ ግን አቶ ተሾመ "በጥይት መመታታቸው ሰምቻለሁ ከዚህ በተጨማሪ ሌላ መረጃ የለኝም" ብለዋል።

በጉዳዩ ላይ ከከተማው እና ከክልሉ ባለስልጣናት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

ተጨማሪ መረጃዎችን እንደደረሱን የምናቀርብ ይሆናል።

አቶ ተሾመ በ2007 እና በ2008 የነቀምቴ ጨለለቂ ክፍለ ከተማ አስተዳዳሪ ሆነው አገልገለዋል። ከዛ በኋላም የከተማዋ የማህበራዊ ጽ/ቤት ኃላፊ በመሆን ካገለገሉ በኋላ የነቀምቴ ከተማ የአስተዳደር እና የደህንነት ጽ/ቤት ኃላፊ በመሆኑ ተሹመው ነበር።

ከአንድ ወር በፊት ግን ከዚህ ኃላፊነታቸው ተነስተው ሌላ የሥራ ምደባ እየተጠባበቁ እንደነበረ መረዳት ችለናል።

እድሜያቸው ከ35-40 ይገመት ነበረው አቶ ተሹመ ባለ ትዳር እና የሁለት ልጆች አባት ነበሩ።

"በኢትዮ ቴሌኮም ኃላፊ ግድያ ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር የዋለ የለም" የነቀምቴ ፖሊስ አዛዥ

ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ መልኩ በምዕራብ ኦሮሚያ የመንግሥት ባለስልጣናት ላይ ያነጣጠሩ ግድያዎች ሲፈጸሙ መቆየታቸው ይታወሳል።




https://www.bbc.com/amharic/52038439