Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Ejersa
Member
Posts: 3976
Joined: 05 Nov 2019, 10:39

ክብር ለይቅር ባዩ ዶ/ር አብይ!!!

Post by Ejersa » 21 Mar 2020, 13:40

በግሉ ስህተት መስሎ የተሰማውን የአፍ ወለምታ ሰዎችን ላለማስቀየም ሲል ትእቢትና እብሪት ሳይሰማው እራሱን ዝቅ አድርጎ ይቅርታ የጠየቀ የመጀመርያውና ብቸኛው የኢ/ያ መሪ ዶ/ር አብይ አህመድ። 24 ሰዓታት በውሸት አገር ሙሉ ያደነቆረ ስዩም ውሸቱና በ1997 ዓ/ም ድምፃችን ይከበር ብለው አደባባይ ላይ የወጡ የአዲስ አበባ ወጣቶች ግንባር ግንባራቸው በጥይት ፈንክቶ ጨቅላ እድሚያቸው የቀጨ መለስ ሽንታሙ ይቅርታ ሊጠይቁ ይቅርና ይቅርታ እንዲጠየቁ ብዙ ለፍተዋል በድርጊታቸው ደግሞ ተንቀባርረዋል።

Abere
Senior Member
Posts: 11112
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: ክብር ለይቅር ባዩ ዶ/ር አብይ!!!

Post by Abere » 21 Mar 2020, 13:54

ችግሩ እንዴ ሶላት ወይም ጾለት እየደጋገሙ አምስት ጊዜ ይቀርታ መጠየቅ አይደለም - ምን የተለየ ከግፍ የነፃ በጎ ሥራ ተሰራ ነው። እኔ መለሰም ሆነ ዐብይ ከዝንጀሮ ቆንጆ ማን ምንን ይመርጣል ነው። እንዴ እኔ ውሸታም ሰው በጣም አስፀያፊ ነው። ደግሞስ የደረሰውን ብሄራዊ ጥፋት ስናወዳድር በአጭር ጊዜ ውስጥ በዐብይ ዘምን የተከሰተው ሚዛን ይደፋል። ዝም ብሎ ሰውን በቁሙ ወይም በወሬው ብዛት መገመት ትክክል አይደለም።

Post Reply