Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum

sebdoyeley
Member+
Posts: 5507
Joined: 14 Feb 2020, 04:27

Re: Tplf declares war on eritrea, by telling eritrean army tigrai is their country.

Post by sebdoyeley » 24 Feb 2020, 12:16

agame we degrade you for reason put a name sahsah agame so no Eritrean with right mind will or wish to associet with u

Lovetarik
Member
Posts: 349
Joined: 10 Apr 2018, 00:39

Re: Tplf declares war on eritrea, by telling eritrean army tigrai is their country.

Post by Lovetarik » 24 Feb 2020, 13:01

The two people have no blood relation. Hamasien people are different from Tigray people. Read about it and learn:

በቬሮኒካ መላኩ
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

ትግራዮች በተለምዶ ትግሬዎች እየተባሉ ይጠራሉ። ይሄ ትግሬ የሚለው ስም ሌላ ኤርትራ እና ሱዳን ውስጥ ካለ ትግረ (ሐይሻ) በሚል ከሚጠራ ብሔር ጋር እንዳይመሳሰል ላስገነዝብ ወዳለሁ። ኢትዮጵያውያን ትግሬ እያልን የምንጠራቸው ባብዛኛው አሁን ትግራይ እየተባለ በሚጠራው ክልል ውስጥ በአደዋ፣ ሽሬ(ሽረ)፣ መቀሌ(መቐለ) የሚኖሩትን ትግርኛ ተናጋሪዎች ሲሆን አሁን ያሉት እነዚህ ከላይ በተጠቀሱት ቦታዎች የሚኖሩ ትግርኛ ተናጋሪዎች ራሳቸውን በክልላቸው ስም ትግራይ እንዲሁም ተጋሩ እያሉ መጥራትን ይመርጣሉ ። እኔም በዚህ ፁሑፍ ላይ መጠራት በፈለጉበት ስያሜ ትግራዮች እያልኩ እጠራቸዋለሁ።

ወደ ዋናው ነገራችን ስንመጣ ብዙ ወገኖች ትግራዮች እና የኤርትራ ብሄረ ትግርኛ አንድ አይነት ብሔር ይመስሉዋቸዋል። በመሰረቱ ግን ሁለቱ ፍፁም የተለያዩ ነገዶች ናቸው። ትግራዮች "የኤርትራ ብሄረ ትግርኛን ትግራዮች ናቸው አንድ ብሔር ነን" ብለው ያስባሉ። ብዙ ትግራዮችም ኤርትራዊ የመሆን ፍላጎት አላቸው። የባድመ ጦርነት ከመነሳቱ በፊት ብዙዎቹ ትግራዮች ራሳቸውን ኤርትራዊ እያሉ ይጠሩ ነበር። ከባድመ ጦርነት በሁዋላ እነዚህ ትግራዮች ከፍተኛ የሆነ የማንነት ቀውስ ውስጥ ገብተዋል። በተቃራኒው የኤርትራ ብሄረ ትግርኛዎች ስለ ትግራዮች ያላቸው ስሜት ምን እንደሆነ ሲጠየቁ ትግራዮች ወይም አጋሜዎች እያሉ ይጠሩዋቸዋል። (Hassan Adem, M.T., Tekle B, 2010) እነዚህ ኤርትራውያን ብሄረ ትግርኛዎች ትግራዮችን የማይታመኑ እና ልባቸው የማይገኝ አድርገው በአሉታዊ መንገድ ይስሉዋቸዋል። ”Eritreans sometimes contemptuously refer to them- cannot be trusted and never could.” (Smith,et al. 2003, Africa, volume 73, p.377) ።

በኤርትራውያን ብሄረ ትግርኛዎች ላይ በተደረገው በዚህ አንትሮፖሎጅካል ማህበራዊ ጥናት ላይ አንድ የ EPLF ታጋይ የነበረ ለፕሮፌሰር ሪድ ”አባቶቻችን እና ቅድመ አያቶቻችን እነዚህ ትግራዮች አደገኛ ናቸው በደንብ እናውቃቸዋለን ብለው አስጠንቅቀውናል” ብሎ ኤርትራውያን ነፃነታቸውን ባወጁበት ዓመተምህረት በአውሮፓ አቆጣጠር በ1991 ወይም በ1983 ኢ.አ ምስክርነት ሰጦ ነበር። “Be careful, these people are dangerous, we know them well!” (Smith,et al. 2003, Africa, volume 73, p.377 )

የኤርትራ ብሄረ ትግርኛዎች ከትግሬዎች የተለየ ማንነት እንዳላቸው እያሳወቁ ትግሬዎች የኤርትራ ብሔረ ትግርኛዎችን እንደራሳቸው ብሄር አድርገው ለምን ይቆጥሩዋቸዋል?

የኤርትራ ብሄረ ትግርኛዎች ኤርትራዊ የሚባል ሃገራዊ ማንነት ሲገነቡ ትግራዮች ከየኤርትራ ብሄረ ትግርኛዎች የተለየ ብሔራዊ ማንነት መገንባት ለምን ተሳናቸው?

በትግራዮች ዘንድ የሚታየው የማንነት ቀውስ ምንጩ ምንድን ነው? ለመሆኑ ይህ የኤርትራ የብሔረ ትግርኛዎች ለትግራዮች ያላቸው አሉታዊ አመለካከት እንዴት ሊመጣ ቻለ?

የነገድ ማንነት ትርጉም በተለያዩ የማህበራዊ ሳይንስ ተመራማሪዎች እና ፀሐፊዎች የተለያየ ፍች ይሰጠዋል። ነገድ ጎሳ እና ብሄር የሚሉት ቃላት ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ባለው ተቀራራቢ ፍች ነው ያላቸው። ብሔር ከሀገር ጋር ጎሳ ከቁዋንቁዋ ጋር ስለሚዛመዱ ethnicity ለሚለው የእንግሊዘኛ ቃል በጣም ተቀራራቢ የሆነው ቃል ነገድ የሚለው ስለሆነ ነገድ እያልኩ እጠቀማለሁ።

ማክስ ዌበር የነገድ ማንነትን ተመሳሳይ የሆነ ውጫዊ አቁዋም ወይም ልምድ ስላለን አንድ የጋራ የነገድ ምንጭ አለኝ ብሎ የማመን ግላዊ እሳቤ ነው ይለዋል። የአንድ ነገድ አባልነት እውነተኛ የደም ትስስር ቢኖረም ባይኖረም ዋና አላማው ፖለቲካዊ ቡድን ወይም ማህበረሰብ መፍጠር ነው ይላል።

“Those human groups that entertain a subjective belief in their common descent because of similarities of physical type or of customs or both, or because of memories of colonization and migration; this belief must be important for group formation; furthermore it does not matter whether an objective blood relationship exists…ethnic membership does not constitute a group; it only facilitates group formation of any kind, particularly in the political sphere. On the other hand it is primarily the political community, no matter how artificially organized, that inspires the belief in common ethnicity.” (1978, Max Weber, p. 389)


ፕሮፌሰር ጆሹዋ ደግሞ የነገድ ማንነት የሚወሰነው በዋናነት በስነልቦና ነው ይላል። አንድ ሰው የአንድ ነገድ አባል ነኝ ብሎ ራሱን ማሳመን እና መግለፅ ይኖርበታል ይላል።

The psychological dimension of ethnicity is perhaps the most important because, regardless of variations in the biological, cultural, and social domains, if a person self-identifies as a member of a particular ethnic group, then he or she is willing to be perceived and treated as a member of that group. Thus, self-ascribed and other-ascribed ethnic labels are the overt manifestations of individuals’ identification with a particular ethnicity. (2001, Joshua A. Fishman, p.115)


የነገድ ማንነት ከሃይማኖት ከቋንቋ እና ባህል ጋርም ይያያዛል። ግን በሃይማኖት እና ቋንቋ መቀራረብ አንድ የጋራ ነገድን አይፈጥርም። ለምሳሌ ጀርመኖች እና ኦስትርያዎች ተመሳሳይ ቋንቋ አና እምነት እንዲሁም ተቀራራቢ ባህል እና ወግ ቢኖራቸውም ራሳቸውን እንደ ሁለት የተለያዩ ነገዶች ነው የሚያዩት። ሁቱ፣ ቱትሲ እና ትዋ ሶስቱም ነገዶች ሩዋንዳ ሩንዲ የተባለ ተመሳሳይ የአፍ መፍቻ ቋንቋ ነው ያላቸው። ሃይማኖታቸውም ባመዛኙ ተመሳሳይ ካቶሊክ ነው። ባህላቸውም ተቀራራቢ የባንቱዎች ባህል ነው። ነገር ግን ራሳቸውን እንደተለያዩ ነገዶች ነው የሚቆጥሩት። በደቡብ ሱዳን ያሉ ዲንቃዎች ቋንቋ ብዙ አይነት አነጋገር ቢኖረውም አንድ ዲንቃ ነገድ ነን ነው የሚሉት። የ ኑዌሮች እና የ ሺልቆች (Shilluk) ቋንቋ በጣም ተመሳሳይ ቢሆንም ሁለቱ ራሳቸውን እንደተለያዩ ነገዶች ነው የሚያዩት።

ለየኤርትራ ብሄረ ትግርኛ ነገድ ትግርኛ የቋንቋቸው መጠሪያ እና የነገዳቸው መጠሪያ ስያሜ ምንጭ ነው።

”In official papers distributed by the Eritrean Government, the ‘language’ (Tigrinya) is used as an ethnic term of the group” (1998, Kjetil Tronvoll, P. 30).ኤርትራ ውስጥ ያሉ ሌሎች ነገዶችም የቋንቋቸው ስም የነገዳቸው መጠሪያ ሁኑዋል። ”Nearly all the ethnic groups in Eritrea are also named after their language, including the Tigre, Kunama, Afar, Nara, Saho, Hedareb, and Bilen” (Hassan Adem, M.T., Tekle B, 2010)


ብዙ በዓለም ላይ ያሉ ነገዶች ስም እና ቋንቋ የተመሳሰለበት ግዜ አለ። አማራ እና አማርኛ ፣ ኦሮሞ እና ኦሮምኛ፣ እንግሊዝ እና እንግሊዘኛ፣ ፍሬንች እና ፈረንሳይኛ ወዘተረፈ። በ 1990ዎቹ በተደረገ ጥናት አብዛኛዎቹ የኤርትራ ብሄረ ትግርኛዎች ራሳቸውን የሚገልፁት ሐማሴን፣ አካለ ጉዛይ እና ሰራዬ በሚል ነበር።

“However, people from the highlands do not speak of themselves as “Tigrinyans.” When asked they would usually reply as did Tewolde, a 60-year old villager from Mai Weini: “Tigrinya is just the language, it is not the tribe (aliet). The tribe is Kebessa (highland). Or, when in the highlands, the tribe is Akele-Guzai, Seraye or Hamasien”( Kjetil Tronvoll, P. 30,1998 )”


የመጀመሪያው በትግርኛ የተፃፈ ፅሁፍ የተገኘው የአሁኗ ኤርትራ ውስጥ ሲሆን ትግርኛ ቋንቋ ሁለት አይነት የአነጋገር ዘየዎች አሉት። የአስመራ እና የትግራይ። የትግርኛ ቋንቋ መደባዊ ቋንቋ የአስመራ ዘዬ ነው ። ሃማሴኖች በንጉስ ላሊበላ እና በአፄ ሰርፀ ድንግል ከወሎ እና ጎንደር በውትድርና የሄዱ እንደሆኑ ብዙ የታሪክ ድርሳናት ያትታሉ።

ከእንግዲህ በየኤርትራ ብሄረ ትግርኛ በትግራይ እና በየኤርትራ ትግረ መካከል ያለው ዝምድና ”ትግ” የምትለው ቃል ናት። ይህም እነዚህ ሶስት ህዝቦች ከዘመናት በፊት ከአንድ ተቀራራቢ የዘር ሐረግ መጠው ሊሆን ይችላሉ። ዳሩ ግን ከዘመናት በፊት ሁሉም የሰው ልጅ ከአንድ የዘር ግንድ እንደተነሳ ይታመናል። በዘመናት ሂደት ይህ አንድ የሰው ዘር በቦታ እና በአካባቢ ልዩነት የራሱን ቋንቋ እና ባህል እንዲሁም ነገድ ማህበራዊ ቡድን እየፈጠረ እንደመጣ ይታመናል።

ከእንግዲህ እነዚህ የኤርትራ ብሄረ ትግርኛዎች ራሳቸውን ከትግራዮች ጋር እንደ አንድ ነገድ የማያዩት ለምድን ነው? ምክንያቱም ተመሳሳይ የሆነ ስነልቦና እና አብሮ የመኖር ትስስር ስለሌላቸው ነው። የኤርትራ ብሄረ ትግርኛዎች እና ትግራዮች ለዘመናት የተለያዩ ግዛቶች እንደነበሩ በታሪክ ተጠቅሱዋል። አብዛኛዎቹ የኤርትራ ብሄረ ትግርኛዎች ጎንደሬዎች ቤጃዎች እና በለዎች እንደሆኑ በስፋት ተጠቅሱዋል።

“The 9th century Arab geographer Al-Ya’qubi wrote of six Beja kingdoms located in what is today Eritrea. Beja place names are found throughout the central and northern highlands of Eritrea, suggesting widespread Beja interaction with other communities (Schmidt, Curtis, Teka , p. 284, 2008)”


የኤርትራ ብሄረ ትግርኛ እና ትግራዮች ተቀራራቢ ቋንቋ ቢጠቀሙም የተለያዩ ሁለት ነገዶች መሆናቸውን በአካባቢው ጥናት ያደረጉ ተመራማሪዎች ፅፈዋል። ሮይ ፓተማን የኤርትራ ብሄረ ትግርኛ እና ትግራዮች ሁለቱ የተለያዩ ነገዶች መሆናቸውን እንዲህ አስቀምጦታል። አስትርያዎች ጀርመኖች እና የተወሰኑ ስዊዞች ጀርመንኛ ቢናገሩም ሁሉም የተለያዩ ህዝቦች እነሆኑት ሁሉ በኤርትራ ከፍታማ ቦታዎች የሚኖሩት እና ትግራዮች ከጥንት ጀምሮ የተለያዩ ነገዶች ናቸው ስል ፅፉዋል።

“Even in those distant times, however, it is clear that the land and people of highland Eritrea were distinct from people of Tigray, even though they spoke the same language-just as the Austrians, Swiss Germans and the Germans of today are very different people (Roy Pateman, P.33, 1998).”


ከላይ እንደገለፅኩት ሁቱ እና ቱትሲ ተመሳሳይ የአፍ መፍቻ ቋንቋ እና ተመሳሳይ ሃይማኖት ቢኖራቸውም ራሳቸውን እንደ ሁለት የተለያዩ ነገዶች ነው የሚቆጥሩት። ፖርቹጋላዊው ፍራንሲስኮ አልቫሬዝ በ 16ኛው ክፍለ ዘመን ወደ ምስራቅ አፍሪካ በመጣ ግዜ ያየውን እንዲህ ገልፁዋል።

”ይህ መረብ የተባለው ወንዝ ባህረ ነጋሽ እና ትግራይን የሚለያይ ድንበር ነው” ”Here; this river, the Mareb, separates the country of the Bahar Nagash from that of Tigray” ( Francisco Alvarez al et , P. 91, 1540)።


ባለባበሳቸው እና በባህላቸውም የተለያዩ መሆናቸውን ገልፁዋል

”The men (of Medri-Bahri) wear different costumes; so also the women who are married or living with men. Here (Tigray), they wear wrapped round them dark coloured woolen stuffs, with large fringes of the same stuff, and they do not wear diadems on their heads like those of the Barnagasi (Midri-Bahri people)”. ( Francisco Alvarez, P. 91-2 ,1970)


ስኮትላንዳዊው ጀምስ ብሩስም ባህረ ነጋሽ የአሁኑ ኤርትራ ከትግራዮች የተለየ መሆኑን እና ድንበራቸው መረብ ወንዝ መሆኑን አስቀምጡዋል። በምዕራብም በኩል የትግራይ ድንበር ተከዜ ወንዝ እንደሆነ ቁልጭ አድርጎ አስቀምጡዋል። ትግራዮች ከየኤርትራ ብሄረ ትግራይ ጋር በታሪክ አብረው የኖሩበት ግዜ አልተመዘገበም። የአሁኖቹ አንዳንድ የትግራይ ምሁራን ከየት አምጥተው ነው የኤርትራ ብሄረ ትግርኛን እና ትግራይን የለያየው ምንሊክ ነው የሚሉት? ከዚሁ ጋር በተያያዘ ወልቃይት ጠገዴ ጠለምት እና ታች አርማጭሆን አፄ ምንሊክ ነው ወደ ጎንደር ያስገቡት የሚሉት ሁሉ ውሸት መሆኑን የጀምስ ብሩስ ማስረጃ ያሳያል።

“The greatest length of Tigre (Tigray) is two hundred miles, and the greatest breadth one hundred and twenty. It lies between the territory of the BaharNagash (which reaches to the river Mareb) on the east, and the river Tacazze on the west.” ( James Bruce, p.83,1860)


በ1838 ወደ አካባቢው ያቀናው አሳሽ ጆን ሚልስም የትግራይ እና የባህረ ነጋሽ ድንበር መረብ ወንዝ መሆኑን ቁልጭ አድርጎ አስቀምጡዋል። ”መረብ የትግራይ እና የባህረ ነጋሽ ግዛት ድንበር ነው”። እውነታው ይህ ሁኖ ሳለ የማንነት ቀውስ ያለባቸው አንዳንድ የትግራይ ልሂቃን በፈጠራ እኛ እና የኤርትራ ብሄረ ትግርኛ አንድ ነበርን ምንሊክ ነው የለያየን የሚል የሐሰት ክስ ያቀርባሉ። እውነቱ ግን ምንሊክ ሳይወለድ በፊት ትግራይ እና የኤርትራ ብሄረ ትግርኛ በአንድ ግዛት ኑረው አያውቁም። አንድ ነገድ ሁነውም አያውቁም።

“the Mareb, which forms the boundary between Tigre (sic, Tigray) and the Kingdom of Baharnagash.” ( John R. Miles, P. 131,1846)


በ19ኛው ክፍለ ዘመን ወደ አካባቢው ያቀናው እንግሊዛዊው ፕሎውደን ትግራዮች የኤርትራ ብሄረ ትግርኛን እንደ ራሳቸው ነገድ አያዩትም ነበር ሲል ቁልጭ አድርጎ አስፍሩዋል። ” ከራስ ሚካኤል ግዜ ጀምሮ የሐማሴን እና ሰራዬ ሕዝብ ከትግራዮች ጋር ተመሳሳይ ቁዋንቁዋ ቢናገሩም ትግራዮች በየኤርትራ ብሄረ ትግራይ ላይ ተደጋጋሚ ጦርነት ያደረጉባቸው ሲሆን አንድ ነን ብለውም አያስቡም”

“The people of Hamazain and Serowee, since the time of Ras Michael, though speaking the same language, are still scarcely (hardly) considered by the people of Teegray as a portion of that country whose governors, since that period, have made war on them….” (Walter Chichele Plowden, P. 39, 1868)


ከእንግሊዝ ጋር ተዋውለው የእንግሊዝን ጦር አቅጣጫ እየጠቆሙ በትግራይ በኩል በማስገባት የባንዳነት ሥራ የሰሩት እና በመቅደላው ጦርነት አፄ ቴዎድሮስ እጅ አልሰጥም ብለው ራሳቸውን ከሰዉ በሁዋላ በእንግሊዞች መሳሪያ እርዳታ ስልጣን የያዙት ብዝብዝ ካሳ ወይም አፄ ዮሐንስ ወደ ባህረ ነጋሽ ጦራቸውን ልከው ከፍተኛ ጭፍጨፋ መፈፀማቸው ይታወቃል። በወሎ እና ጎጃም ሕዝብ ላይ የጅምላ ፍጅት የፈፀሙት በዝብዝ ካሳ ወደ ኤርትራም ራስ አሉላን ልከው ሁለት ሶስተኛ የሚሆነውን የባህረ ነጋሽ ሕዝብ ጨፍጭፈዋል። (, Lyda Favali and Roy Pateman, p. 36, 2003 ) (, Hagai, and Erlikh, p.35, 1996) (Hassan Adem, M.T., Tekle B, 2010)

አፄ ዮሐንስ አደዋ ላይ ከእንግሊዙ አድሚራል ሂወት ጋር በተዋዋሉት በሕወቴ ውል (Hewett Treaty) መሰረት ለእንግሊዞች አግዘው በመሰለፋቸው ድርቡሾች መተማ ላይ በተደረገ ጦርነት ገለው አንገታቸውን ወስደውታል። አፄ ዮሐንስ ከሞቱ በሁዋላ ራስ አሉላ በምንሊክ ከመገዛት ነፃ የትግራይ መንግስት ለማቁዋቁዋም ለጣልያኖች ከመረብ ማዶ ያለውን ባህረ ነጋሽ እንዲወስዱ ስምምነት ማድረጋቸውን የታሪክ ፕሮፌሰር ጌታቸው መታፈሪያ እና የፖለቲካ ሳይንስ ፕሮፌሰር ጳውሎስ ሚክያስ The Battle of Adwa: Reflections on Ethiopia’s Historic Victory Against European Colonialism በተባለው መፃህፋቸው አስፍረዋል። (Milkias, Metaferia, p.69, 2005)

ትግራዮች የኤርትራ ብሄረ ትግርኛን እንደራሳቸው አንድ ነገድ አድርገው እንደማያዩ ራስ አሉላ ከዚህ በታች ለጣልያኖች ያቀረቡት የድርድር ሃሳብ ፍንትው አድርጎ ያሳያል።

”ቤታችሁን ለመስራት እርሻ ለማረስ ቤተክስርስቲያናችሁን ለመገንባት እስከ መረብ ድረስ ሀገር ከፈለጋችሁ ምኒልክ ሳይሆን እኛ ለናንተ እንሰጣችሁዋለን። የጣሊያን ወታደሮች ወደ አድዋ ይምጡ እንደ ወዳጅ አስተናግዳቸዋለሁ” “You want the country to the Mareb (Eritrean highlands/Medri Bahri) to cultivate your gardens, to build your houses, to construct your churches….? We can give it to you. [And not menilek.] Let the Italian soldiers come to Adwa, I shall come to meet them like a friend.” (1996, Ḥagai Erlikh, P. 164)


ራስ አሉላ እና ሌሎች የ19ኛው ክፍለ ዘመን የትግራይ መሳፍንት ሙሉ በሙሉ ባህረ ነጋሽን ጣሊያኖች እንዲጠቀሙ ነበር የተስማሙት። የኤርትራ ብሄረ ትግርኛዎችን እንደ ራሳቸው ነገድ ቆጥረዋቸው አያውቁም።
” እናንት ጣሊያናውያን ለምን እሩቅ ወዳጅ ትፈልጋላችሁ? እኛ ጎረቤታሞች ነን እርስ በርስ መጠቃቀም እንችላለን። መንገድ እንዲከፈትላችሁ ትፈልጋላችሁ እኔም እፈልጋለሁ። እናንተ እስከ መረብ ድረስ ያለውን ጠብቁ እኔም እስከ ጎንደር እና ከጎንደርም አልፎ ያለውን እጠብቃለሁ። በእግዚአብሔር እርዳታ ሀገራችንን ትግራይ ለማልማት ወደ ባህሩ ዳርቻ ድረስ በመሄድ መነገድ አለብን። ምኒልክ ሩቅ ነው ለናንተ የሚጠቅማችሁ ነገር የለም። በመካከላችን ወዳጅነት እንመስርት” (ራስ አሉላ)


“And you (Italians), why do you need to look for distant friends? We are neighbors (meaning Medri Bahri and Tigray) and can serve each other. You want the road to be open and I want the road to be open. You should guard to the Mereb River and I will guard it to Gondar and even beyond Gondar. We must be able to go to the coast to trade in order that our country (meaning Tigray) would flourish, with the help of God, Menelik is too far to be of any use to you. Let us make friendship between us. (1996, Ḥagai Erlikh, 164)”


አሁን ከምኒልክ በሁዋላ ባሉት 100 አመታት ያለውን እንኩዋ ብናይ ትግራይ እና የኤርትራ ብሄረ ትግርኛ አንድ ነገድ ሁነው አያውቁም። የኤርትራ ብሄረ ትግርኛዎች ትግራዮችን ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ነገዶች ሁሉ እንደ ዝቅተኛ እና ተንኮለኛ አድርገው ነው የሚያዩዋቸው። ከባድመ ጦርነት በፊት ብዛት ያላቸው ትግራዮች በተለያዩ የጉልበት እና የቤት ሰራተኝነት ስራዎች ላይ ተሰማርተው ኤርትራ ውስጥ በሚሰሩበት ጊዜ የኤርትራ ብሄረ ትግርኛዎች ትግራዮችን እንደ አንድ የራሳቸው ነገድ አይተዋቸው አያውቁም። በመሰረቱ የኤርትራ ብሄረ ትግርኞች የነፃነት ትግል ባደረጉበት ግዜም በኤርትራ ሃገራዊ ማንነት ላይ የታገሉ ሲሆን ትግራዮች ደግሞ በነገዳቸው ስም ነው የታገሉት። ሁለቱ አንድ ነገድ ቢሆኑ ኑሮ ከደርግ ውድቀት ማግስት የራሳቸውን አንድ ሀገር ለመገንባት የሚያግዳቸው አካል አልነበረም።

እውነቱ ግን የኤርትራ ብሄረ ትግርኛዎች ትግራዮችን እንደ አንድ ነገድ አይተዋቸው አያውቁም። ደርግን ለመጣል ስልታዊ ትብብር ከማድረግ ያለፈ ምንም አይነት የተለየ ግንኙነት የላቸውም። የኤርትራ ብሄረ ትግርኞች በነገዳቸው ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ስላልደረሰባቸው እና አሁን ያለውን የኤርትራ ሃገራዊ ማንነት በመገንባት ሂደት ጉልህ ሚና ስለተጫወቱ ወደ ብሄረ ትግርኛ የነገድ ማንነታቸው የሚያስገባ ምንም አይነት ምክንያት የለም። አሁን ኤርትራ ውስጥ አለ የሚባለውም አምባገነናዊ አስተዳደር እንጂ ብሄርተኛ ወይም በነገድ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት የሚፈፅም ስርዓት አይደለም።

የትግራይ ብሄርተኞች አሁን ከገቡበት የፖለቲካ አጣብቂኝ ለመውጣት የሌለ ትግራይ ትግርኛ የሚባል ማንነት ለመፍጠር ቢሞክሩም መሬት ላይ ያለው እውነት ግን ”ልቢ ትግራይ” ነው የሚለው። የትግራይ ብሄርተኞች በምስራቅ አፍሪካ ከታሪክ አንፃር ፣አብሮ ከመኖር (በክፉም በደጉም)፣ ከባህል እና ከስነልቦና አንፃር ከማንም በላይ የሚቀርባቸው እና የተዛመዳቸው የአማራ ሕዝብ ላይ በወልቃይት በወሎ እና በመላው የሀገሪቱ ክፍሎች ጦርነት ሲያውጁበት እና ታይቶም ተሰምቶም የማይታወቅ ግፍ ሲፈፅሙበት ያኔ ነው በምስራቅ አፍሪካ እና በዓለም ላይ ያላቸውን አጋር ሕዝብ ያጡት። ያኔ ነው ለልጅ ልጅ የሚተላለፍ ጥል ቁርሾ እና ቂም የተከሉት።

Ethoash
Senior Member+
Posts: 26144
Joined: 20 Apr 2013, 20:24

Re: Tplf declares war on eritrea, by telling eritrean army tigrai is their country.

Post by Ethoash » 24 Feb 2020, 13:20

i know this guy is the best long time ago when he rises Ethiopian phone subscription from one million to 65 million and kick out the Western phone company and give the partnership to Huawei... and move Ethiopia to G5 phone system.. even before no body walk up the doctor know Huawei is a winner.. even the usa try to stop Huawei

second as chief commander of Golden state. he ignore the war cry from Amhara they blocked the road for two years. ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል said when god gives you lemons make lemonade... this blockage is good dry run for independent it help golden state to live independently... soon they will develop and become beneficent

now if a war started it would be God sent for the Golden state .. Eritrea will be landlocked state. no Eritrean Army will die for issu .. second Assab and Massawa port become their own nation .. that is on the table if the Eritreans cant say no body did not tell us.. dont start war. dont even say goooooooooooooooood about the golden state keep your distance dont interfere just wait for your badme until u r given .. anything less u r signing good bye for your two port and become landlocked trust me America would have love it..



Post Reply