Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Hameddibewoyane
Member
Posts: 3890
Joined: 25 Sep 2019, 02:42

የምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ፓርቲዎችን አስጠነቀቀ!

Post by Hameddibewoyane » 13 Feb 2020, 11:11

ከተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ ውጭ የምርጫ ቅስቀሳ የሚያደርጉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ አስጠነቀቀ።

የመገናኛ ብዙሃን የምርጫ ዘገባ ተደራሽነትና ሚና ላይ ቦርዱ ከመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ጋር እየመከረ ነው።
በአሁኑ ወቅት ፓርቲዎች ህጉ ከሚፈቅደው ውጭ በቀጥታና በተዘዋዋሪ ቅስቀሳ እያደረጉ መሆናቸውን በተመለከተ የውይይቱ ተሳታፊዎች ጥያቄ አንስተዋል።

የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ ውብሸት አየለ ቦርዱ በመጪዎቹ ጥቂት ቀናት ውስጥ የመጨረሻ የምርጫ ሰሌዳ በማውጣት እንደሚያሳውቅ ገልጸው፣ ከተጠቀሰው ጊዜ በኋላ ህግ የማስከበር ስራው ወደ ተግባር ይቀየራል ብለዋል፡፡

የምርጫ ሰሌዳው የመጨረሻ ቀን ከተቆረጠ በኋላ "እንደ እስከ ዛሬው ተቻችለን የምናልፈው ጉዳይ ሳይሆን እርምጃ የምንወሰድበት ነው" ሲሉም ማሳሰቢያ ሰጥተዋል።

ምክክሩ በሚዲያና የመራጮች ትምህርት፣ የሚዲያ ሚና በመራጮች ትምህርት የውጭ ተሞክሮ፣ ምርጫ ቦርድና በመራጮች ትምህርት ዙሪያ ያለው ዝግጅት እንዲሁም የመገናኛ ብዙሃንና የጋዜጠኞች የምርጫ አዘጋገብ ስነ ምግባርና አሰራርን ለመደንገግ በወጣ መመሪያ ላይ እንሚያተኩር ተገልጿል።
ኢዜአ እንደዘገበው የምርጫ ቦርዱ ባወጣው ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት 'የምረጡኝ ዘመቻ' ጊዜ ከሚያዚያ 27 እስከነሐሴ 5 ቀን 2012 ዓ.ም ነው።

ምንጭ፡-ዋልታ