Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Revelations
Senior Member+
Posts: 33735
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

ኦፌኮ የምርጫ ቅስቀሳ ውስጥ አልገባሁም ብሏል:- “የአቶ ጀዋርን ዜግነት ለማረጋገጥ እያጣራሁ ነው”

Post by Revelations » 25 Jan 2020, 14:34

Please wait, video is loading...

Revelations
Senior Member+
Posts: 33735
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: ኦፌኮ የምርጫ ቅስቀሳ ውስጥ አልገባሁም ብሏል:- “የአቶ ጀዋርን ዜግነት ለማረጋገጥ እያጣራሁ ነው”

Post by Revelations » 25 Jan 2020, 14:39



- “የአቶ ጀዋርን ዜግነት ለማረጋገጥ እያጣራሁ ነው”

- ዜግነታቸውን ማረጋገጥ ካልቻሉ ፓርቲው ህልውናውን ለማስጠበቅ የሚወስዳቸው እርምጃዎች ይኖራሉ”

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ከምርጫ ቦርድ የቀረበለትን ጥያቄ ተቀብሎ በቅርቡ አባል በአባልነት የተቀበላቸውን የአቶ ጀዋር መሀመድን የዜግነት ጉዳይ እያጣራሁ ነው ብሏል፡፡ ግለሰቡ ማስረጃቸውን ለማቅረብ በሂደት ላይ መሆናቸውንም ፓርቲው ለአዲስ አድማስ አስታውቋል፡፡

‹‹በአቶ ጃዋር በኩል ዜግነታቸውን ለማረጋገጥ እንቅስቃሴ እያደረጉ መሆኑን ተገንዝበናል›› ያሉት የኦፌኮ ዋና ጸሐፊ አቶ ጥሩነህ ገምታ፤ አቶ ጀዋር ዜግነታቸውን ለማረጋገጥ የማይሳካላቸው ከሆነ፣ ፓርቲው ሕልውናውን ለማስጠበቅ የሚወስዳቸው እርምጃዎች ይኖራሉ ብለዋል፡፡ እንዴት ኢትዮጵያዊነታቸውን ሳታረጋግጡ ከጽ/ቤታችሁ መታወቂያ ተሰጣቸው በሚል ከአዲስ አድማስ ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ “በዚህ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ መስጠት አልፈልግም” ብለዋል - ዋና ፀሐፊው፡፡

አቶ ጀዋር የዜግነት ጉዳያቸውን አሟልተው ለፓርቲው የሚያቀርቡበት የጊዜ ገደብም አለመቀመጡን ዋና ፀሐፊው ጠቁመው በዚህ ሂደት ውስጥ ፓርቲው ለምርጫ የሚያደርገውን ዝግጅት አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች በተለያዩ አካባቢዎች እየተዘዋወሩ ከሕዝብ ጋር የመተዋወቅ እንጂ የምርጫ ቅስቀሳ እያደረጉ አለመሆኑንም አቶ ጥሩነህ ለአዲስ አድማስ አስረድተዋል፡፡

የፓርቲውን ፖሊሲ፣ አላማና ደንብ ከማስተዋወቅ በዘለለ የምርጫ ቅስቀሳ ውስጥ አልተገባም ያሉት አቶ ጥሩነህ፤ አንዳንድ የምርጫ ቅስቀሳ የሚመስሉ ጉዳዮችም ሆን ተብለው የተደረጉ አይደሉም ብለዋል፡፡

http://addisadmassnews.com/index.php?op ... F%E1%88%8D

Revelations
Senior Member+
Posts: 33735
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: ኦፌኮ የምርጫ ቅስቀሳ ውስጥ አልገባሁም ብሏል:- “የአቶ ጀዋርን ዜግነት ለማረጋገጥ እያጣራሁ ነው”

Post by Revelations » 25 Jan 2020, 14:49

Please wait, video is loading...

simbe11
Member
Posts: 2087
Joined: 23 Feb 2013, 13:02
Location: Addis Ababa

Re: ኦፌኮ የምርጫ ቅስቀሳ ውስጥ አልገባሁም ብሏል:- “የአቶ ጀዋርን ዜግነት ለማረጋገጥ እያጣራሁ ነው”

Post by simbe11 » 25 Jan 2020, 14:58

Gashe Merara/Eretu,

The president of the republic of Djibouti speaks Ethiopian/Amharic fluent
He also looks Ethiopian/ Somali region

Will you accept him as a member of "OFCO" too?

Just saying

Post Reply