Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Maxi
Member+
Posts: 5951
Joined: 06 Mar 2014, 04:33

አማራ ሜዲካል አክሲዮን ማህበር (በምስረታ ላይ)

Post by Maxi » 18 Jan 2020, 09:20



አማራ ሜዲካል አክሲዮን ማህበር (በምስረታ ላይ)

Amhara Economic Think Tank S.C.

ወሳኝ መግለጫ!

እንኳን አደረሣችሁ!

አማራ ሜዲካል አክሲዮን ማህበር (በምስረታ ላይ)

በምስረታ ላይ የሚገኘው የአማራ ሜዲካል አክሲዮን ማህበር በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ፣ ውጤታማ እና የተቀናጀ የጤና አገልግሎት አቅራቢ ተቋም ለመፍጠር ራዕይ ሰንቆ የተነሳ የምጣኔ ሃብት አካል ነው።

አማራ ሜዲካል፥ የሀገሪቱ የጤና ፖሊሲ ለግሉ ክፍለ-ኢኮኖሚ የሚሰጠውን ድርሻ፣ እውቅና እና ሙያዊ ኃላፊነት በተገነዘቡ፤ በጤናው ዘርፍ ሰፊ ልምድ ባካበቱ ባለሙያዎች እየተደራጀ ያለ አክሲዮን ነው።

ይህ ባለ ግዙፍ ካፒታል ተቋም፥ የአማራን ህዝብ የኢኮኖሚ ህልውና ብሎም የሃገራችን ገፅታ ግንባታ ሂደት ሚናውን በመጫወት፥
አንደኛው ምሰሶ እንደሚሆን ይጠበቃል።

ተቋሙ ኃላፊነት በሚሰማቸው በዘርፉ ላይ የተሰማሩ ከፍተኛ የጤና መኮንኖች እና በታታሪ ሙህራን አማካኝነት ምስረታ ላይ ያለ ነው።

እነሆ ዛሬ አስፈላጊ ቅደመ ዝግጅቱን በማጠናቀቅ እሁድ ጥር 10፣2012ዓ.ም የመጀመሪያውን የምስረታ እንቅስቃሴና አላማ በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል።

ፕሮግራሙ፥ ባህር ዳር በሚገኘው አቫንቲ ሆቴል፥ ከጥዋቱ 2:30 ጀምሮ እንደሚካሄድ ታውቋል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ፥ የምስረታ ጉባኤ መግለጫው ለህዝብ ይደርስ ዘንድ፥ ሁሉም የመገናኛ ብዙሃን ተገኝተው የመርሃ ግብሩ ተካፋይ እንዲሆኑ ጥሪ ተላልፏል።

ቀን፦ ዕሁድ፥ ጥር 10 ቀን 2012 ዓ.ም.፥
ሰዓት፦ ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ
ቦታ፦አቫንቲ ሆቴል፥

ባህር ዳር

መልካም የከተራ በዓል ይሁንላችሁ!
Last edited by Maxi on 18 Jan 2020, 09:24, edited 1 time in total.

Maxi
Member+
Posts: 5951
Joined: 06 Mar 2014, 04:33

Re: አማራ ሜዲካል አክሲዮን ማህበር (በምስረታ ላይ)

Post by Maxi » 18 Jan 2020, 09:23

አማራ ሜዲካል አክሲዮን ማህበር
(በምስረታ ላይ )

የአማራ ሜዲካል አክሲዮን ማህበር የሀገሪቱ የጤና ፖሊሲ ለግሉ ክፍለ-ኢኮኖሚ የሚሰጠውን ድርሻ፣ እውቅና እና ሙያዊ ኃላፊነት በተገነዘቡ፤ በጤናው ዘርፍ የተለያየና ሰፊ ልምድ ባካበቱ ባለሙያዎች እየተደራጀ ያለ ግዙፍ የጤና ተቋም ነው::

👉ራዕይ:
በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ፣ ውጤታማ እና የተቀናጀ የጤና አገልግሎት አቅራቢ ተቋም ተፈጥሮ ማየት፤

👉 ዋና ግብ:
የተቋሙ መሰረታዊ ግብ ጥራት ያለውና በህክምና ስነ-ምግባር የሚገዛ የጤና ጥበቃና የህክምና አገልግሎት ተመጣጣኝ በሆነ ክፍያ ማቅረብ ነው::

👉አላማዎች:
⁃ የህክምና አገልግሎት ጥራት እና ተደራሽነትን መጨመር
⁃ የማህበረሰባችንን የመክፈል አቅም ያገናዘበ የምርመራ እና የመዳኒት አቅርቦትን ማሳደግ
⁃ በመንግስት እና በግል የጤና ተቋማት መካከል ያለውን የተግባቦት ባህል ማሳደግ

👉 እቅዶች:
⁃ ግዙፍ የመዳኒት ማምረቻ ፋብሪካዎችን ማቋቋም፤ ደረጃውን የጠበቀ የመዳኒት ምርት አቅርቦት እና የሽያጭ አገልግሎት ለሀገር ውስጥ እና ለሀገር ውጭ ገበያ ማቅረብ:
⁃ አለምአቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የላብራቶሪና የኢሜጅንግ ምርመራ አገልግሎት ማቅረብ
⁃ ሀገራችንን በአፍሪካ የህክምና ቱሪዝም መዳረሻ ለመሆን የሚያስችሏት ትልልቅ የህክምና አገልግሎት ማዕከላትን መገንባት
⁃ ሌሎችንም የጤና አገልግሎቶች መስጠት ይሆናል።

👉 የአክሲዮን ሽያጭን በተመለከተ፦

የአማራ ሜዲካል አክሲዮን ማህበር 1,000,000 (1,000,000,000 ብር) የተመዘገቡ መደበኛ አክሲዮኖችን ለመሸጥ እንደሚከተለው አቅርቧል::

- አንድ አክሲዮን መደበኛ ዋጋ - 1000 ብር

- የሚከፈለው የአገልግሎት ክፍያ- 5%

- የአክሲዮን ግዢ የአከፋፈል አማራጮች፦

አማራጭ ሀ)

መግዛት የፈለጉትን ሸር ሙሉ ክፍያ (100%) የአክሲዮን ግዥ ማመልከቻ ቅፅ እንደተሞላ በመክፈል።

ወይም

አማራጭለ)

50% ክፍያ በግዢ ወቅት በመክፈል፥ ቀሪውን 50% በስድስት ወር ውስጥ በአንድ ወይም በሁለት ጊዜ መክፈልና ማጠናቀቅ።

- የሚፈቀደው ዝቅተኛ የኢንቨስትመንት መጠን - 10 አክሲዮን( 10,000 ብር)

- የሚፈቀደው ከፍተኛ የኢንቨስትመንት መጠን- 50,000 አክሲን( 50,000,000ብር)

- ሽያጭ የተጀመረበት ቀን- ህዳር 16, 2012ዓ.ም

- ሽያጭ የሚያበቃበት ቀን - መጋቢት 16, 2012ዓ.ም

👉ክፍያ የሚፈፀምባቸው የባንክ ሂሳብ ቁጥሮች፦

- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ዝግ ሂሳብ ቁጥር- 1000305684663
የአገልግሎት ክፍያ -1000305685128

- የአቢሲኒያ ባንክ
ዝግ ሂሳብ ቁጥር- 21445673
የአገልግሎት ክፍያ - 21445908

- የዳሽን ባንክ :
ዝግ ሂሳብ ቁጥር- 5079154404011
የአገልግሎት ክፍያ - 5079154404021

- የአባይ ባንክ :
ዝግ ሂሳብ ቁጥር- 201 1111019711013
የአገልግሎትክፍያ-2012111019711028

- አዋሽ ባንክ
ዝግ ሂሳብ ቁጥር - 013 38 279 272 100
የአገልግሎት ክፍያ- 013 20 279 272 100

- ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ
ዝግ ሂሳብ- 037 SAV 6423
የአገልግሎት ክፍያ- 037 SAV 6424

-ኦሮሚያ ህብረት ባንክ
ዝግ ሂሳብ- 10000 8382 2272
የአገልግሎት ክፍያ- 10000 8383 1228

-ህብረት ባንክ
ዝግ ሂሳብ- 221 001 678 760 2014
የአገልግሎት ክፍያ- 221 011 678 760 2025

-አንበሳ ባንክ
ዝግ ሂሳብ- 00111200846-83
የአገልግሎት ክፍያ- 00111200850-71

-ቡና ባንክ
ዝግ ሂሳብ- 316 960 1000002
የአገልግሎት ክፍያ-316 960 1000003

👉የድርጅቱ ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አድራሻ:

ፖፒረስ ሆቴል ፊትለፊት፦
ሲግናል ሞል፥አራተኛ ፎቅ፥ቢሮ ቁጥር 408
ባህር ዳር፤ ኢትዮጵያ

በዚሁ አጋጣሚ ተጨማሪ የፕሮጀክት ማስተባበሪያ ቅርንጫፍ ጵ/ቤት በቅርቡ በአዲስ አበባ እንደምንከፍት ልናሳውቅ እንወዳለን::

👉ለበለጠ መረጃ የስልክ አድራሻዎች፦

👉 ሀገር ውስጥ ለምትኖሩ ወገኖቻችን:

-+251 9 04 39 00 18
-+251 9 46 43 10 20
-+251 9 41 46 66 07
-+251 9 27 59 42 84
-+251 9 10 66 82 96
-+251 9 02 59 33 59

👉 በሰሜን አሜሪካና አካባቢው ለምትኖሩ ወገኖቻችን:
+1 202-925-6538

አማራ ሜዲካል አ.ማ የፌስቡክ
ገፃችንን ይወዳጁት፤ ይከተሉት፤ ያጋሩት!!
ከፋለ ስማቸው ተስፋው የሁላችን ነው፡፡ እየቀለድን አይደለም፡ Tesfaye Yimer ሙሉ መረጃ እዚህ ታገኛለህ ወንድም፡፡

Post Reply