https://www.dw.com/am/ከእገታ-የተለቀቁት-ተማሪዎች ... a-52042962
DW Radio Amharic
ከእገታ የተለቀቁት ተማሪዎች የት ናቸው?
ከደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ወደ ቤተሰቦቻቸው ሲሄዱ ከታገቱ በኋላ መንግስት መለቀቃቸውን ያስታወቀው ሃያ አንድ ተማሪዎች ወደ ደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ መመለሳቸውን የኦሮሚያ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ ከዶይቸ ቬለ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ተናገሩ።
ከእገታ የተለቀቁት ከወላጆቻቸው ያልተገናኙት የስልክ ግንኙነት ባለመኖሩ ነዉ
ከደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ወደ ቤተሰቦቻቸው ሲሄዱ ከታገቱ በኋላ መንግስት መለቀቃቸውን ያስታወቀው ሃያ አንድ ተማሪዎች ወደ ደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ መመለሳቸውን የኦሮሚያ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ ከዶይቸ ቬለ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ተናገሩ። ተማሪዎቹ ከእገታ ከተለቀቁ በኋላ ከወላጆቻቸው ጋር ያልተገናኙት በአካባቢው የስልክ ግንኙነት አገልግሎት ባለመኖሩ የተነሳ መሆኑንም አቶ ጌታቸው ዛሬ ተናግረዋል።
የታገቱ ቀሪ ስድስት ተማሪዎችን ለማስለቀቅም ጥረት እየተደረገ መሆኑንም አመልክተዋል። ከኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ከአቶ ጌታቸው ባልቻ ጋር የስልክ ቃለ-ምልልሱን ያደረገው ታምራት ዲንሳ ነው። ተማሪዎቹ ደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ መኖራቸውን ለማጣራት ወደ ዩኒቨርስቲው ስልክ ብንደውልም ባለመስራቱ ሳይሳካ ቀርቷል።
ታምራት ዲንሳ
ኂሩት መለሰ