Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum

Revelations
Senior Member+
Posts: 33669
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: [ሰበር ዜና] የክርስትያን ታደለን ፍርድ ቤት ውሎ ለመከታተል የመጡ ብዛት ያላቸው ወጣቶች ተደብድበው ታፍሰዋል [PHOTO]

Post by Revelations » 17 Jan 2020, 07:41

ሰበር ዜና

የአብን አመራሮችንና አባላቶችን ችሎት ለመታደም ወደ ልደታ ያቀኑ ወጣቶች በፖሊስ ተደብድበው ወደ እሥር ቤት ተወሰዱ።


አማራ ሚድያ ማዕከል/አሚማ/
ጥር 8 ቀን 2012 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ

ከሰኔ 15ቱ አሳዛኝ ክስተትን ተከትሎ ታስረው የሚገኙ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን)ከፍተኛ አመራሮች አቶ ክርስቲያን ታደለ፣በለጠ ካሳ እና ሌሎች አባላት ዛሬ ጥር 8 ቀን 2012 ዓ.ም በልደታ የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት እንደሚቀርቡ ይታወቃል።

የዛሬውን ችሎት ለመታደም እና አብሮነታቸውን ለማሳያት የአብንን ቲሸርት ለብሰው ችሎት ለመታደም ወደ ልደታ ባቀኑ ወጣቶች ላይ ፓሊስ ድብደባ በመፈፀም ወደ እሥር ቤት ወስዷቸዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ችሎቱን ለመታደም ወደ ልደታ ያቀኑ በርካታ ወጣቶች በፓሊስ መዋከብ የተፈፀመባቸው ሲሆን ወደ ውስጥ እንዳይገቡና ችሎት እንዳይከታተሉ ክልከላ እየተደረገ መሆኑን አሚማ ከቦታው ታዝቧል።

በልደታ ፍ/ቤት ግቢ ያሉ ታዳሚዎችን በሙሉ ከግቢ እንዲወጡ ከመደረጉም ባሻገር በአደባባይ እያሯሯጡ ድብደባ በመፈፀም በትነዋቸዋል።

ድብደባ እየፈፀሙ ያሉት ፖሊስ፣አድማ ብተና የፌደራል ፖሊስ ሲሆኑ ከ40 በላይ የሚሆኑ ወጣቶችን አንበርክከው በዱላ ሲደበድቡ ተመልክተናል።

በተደረገባቸው ድብደባ የተጎዱ ወደ ጤና ጣቢያ እየተወሰዱ ነው።

የልደታ ፍርድ ቤትና አካባቢው በከፍተኛ የፀጥታ ኃይል እየተጠበቀ እንደሚገኝ አሚማ በቦታው ተገኝቶ አረጋግጧል።

በዛሬው ዕለት የችሎት ቀጠሮ ያላቸው እነ ክርስቲያን ታደለ አባላቶቻችንና ደጋፊዎቻችን ችሎት እንዳይገቡ የሚታገዱ ከሆነ ችሎቱ ላይ አንገኝም ማለታቸው ይታወሳል።




Revelations
Senior Member+
Posts: 33669
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: [ሰበር ዜና] የክርስትያን ታደለን ፍርድ ቤት ውሎ ለመከታተል የመጡ በርካታ ወጣቶች ተደብድበው ታፍሰዋል [PHOTO]

Post by Revelations » 17 Jan 2020, 08:17

Please wait, video is loading...



Revelations
Senior Member+
Posts: 33669
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: [ሰበር ዜና] የክርስትያን ታደለን ፍርድ ቤት ውሎ ለመከታተል የመጡ በርካታ ወጣቶች ተደብድበው ታፍሰዋል [PHOTO]

Post by Revelations » 17 Jan 2020, 13:23

Please wait, video is loading...

Revelations
Senior Member+
Posts: 33669
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: [ሰበር ዜና] የክርስትያን ታደለን ፍርድ ቤት ውሎ ለመከታተል የመጡ በርካታ ወጣቶች ተደብድበው ታፍሰዋል [PHOTO]

Post by Revelations » 17 Jan 2020, 13:32

Please wait, video is loading...

Maxi
Member+
Posts: 5951
Joined: 06 Mar 2014, 04:33

Re: [ሰበር ዜና] የክርስትያን ታደለን ፍርድ ቤት ውሎ ለመከታተል የመጡ በርካታ ወጣቶች ተደብድበው ታፍሰዋል [PHOTO]

Post by Maxi » 17 Jan 2020, 13:58

የፍትህ ስርአቱ ይህን ይመስላል!!

አቶ ወይም ወ/ሮ ማዕዛ አሸናፊ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት (ኦሮሞ) ሲሆኑ ከጎኗ የሚገኘው ደግሞ የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ ኮሚሽነር አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ (ኦሮሞ/ኦነግ) ነው፡፡






Post Reply