Page 1 of 1

ኢራን የኤርትራ ሲሳይ !!

Posted: 16 Jan 2020, 12:34
by pushkin
በዚህች ተቀያያሪ እና ተለዋዋጭ ዓለም ላይ 'ቋሚ ጠላትም' 'ቋሚ ወዳጅም' የሚባል ነገር የለም። ላለፉት 70 ዓመታት አለም አቀፉ ማህበረሰብ ኤርትራ ላይ የተከተለው ኤርትራውያን ለስቃይ፣ ለእልቂት፣ ለስደት እና ለችግር የዳረገው የተሳሳተ ፓለሲ ኤርትራ ሃጥያት ስለነበራት አልነበረም። ሁሉም የሆነው አካባቢው እና ወቅቱ የፈጠረው አለም አቀፍ የፓለቲካ ውጤት እንጅ። ሁሌም አለም ላይ የሚከሰቱ ትላልቅ ቀውሶች የሚያደርሱት እልቂት እንዳለ ሁኖ የሚፈጥሩት ጥሩ አጋጣሚ ደግሞ አለ። ለምሳሌ የጀርመኖች ናዚ መንግሥት አገር አልባ የነበሩ አይሁዳዊን ስደተኞች ላይ የፈጸሙት ጭፍጨፋ ለሽህዎች ዓመታት ከተበታተኑበት መሬት ተመልሰው አገር እንዲመሰርቱ ምክንያትም ግዴታም ሁኗቸዋል። እሱ ብቻ ሳይሆን ጀርመኖች እና አጋሮቿ በአውሮፓ እና በኢሲያ አገራት የፈጸሙት ወረራ መዘዝ ለዘመናት በወራሪዎች ቀኝ ገዢዎች ስር የነበሩትን የአፍሪካ ሀገራት ነጻነታቸውን እንዲያገኙ የ2ኛው የአለም ጦርነት አስገዷል። ያኔ በተፈጠረው ክስተት ኤርትራ ልክ እንደማንኛቸውም የአፍሪካ አገራት ነጻነቷ ሊሰጣት ቢጋባም ኢ-ፍትሃዊ በሆነ ውሳኔ ኤርትራን ሌላ የ40 ዓመታትን ዋጋ አስከፈላት።

ይህ ታሪክ በ1991 በነጻነት ቢቋጭም ነጻነቷን በአገኘች ከጥቂት ዓመታት በኃላ ተረኛ ሁና በኤርትራ ላይ የተነሳችው የህወሃት መንግስት ናት። ህወሃት ለፈጸመችው ወረራ እና ኤርትራ ላይ ላስከተለችው ጠቅላላ ቀውስ የአለም አቀፍን ድምጽ በብቸኝነት ጠቅልላ በያዘችው የታላቋ አሜሪካ ወሳኝ ድጋፍ ነበር። ይሄም በአፍሪካ ቀንድ በተለይ በሶማሌ እና ሱዳን ለተፈጠረው የአሸባሪዎች እንቅስቃሴ በአሜሪካ ባለስልጣኖች የወያኔ መንግስት ተመራጭ ተደርጎ በመወሰዱ ነበር ኤርትራ ገንሸል የተደረገችው። ባለፋት ዘመናት እንደተፈጠሩት የናዚ፣ የኮሚንስት እና የሶማሌ ቀውስ የመሳሰሉ ዘንድሮም በዚህ ወሳኝ ቀጠና ትልቅ ቀውስ ተፈጥሯል፤ የመን!!

የየመን ቀውስ ለምስኪን የመናዊያን አሰቃቂ እና አሳዛኝ ቢሆንም የሶማሌ ቀውስ እና እልቂት ለወያኔ መንግስት ጥሩ አጋጣሚ እንደ ፈጠረለት የየመን ቀውስም ለኤርትራ አሪፍ አጋጣሚ ፈጥሮላታል። ይህም ለ20 ዓመታት በአሜሪካ የበላይነት ድምጿ እንዲታፈን ተበይኖባት የነበረችው አገራችን የሁቱ አማጽያን እና የኢራን መንግስት በፈጠሩት የአካባቢው ተጽኖ ተገላ(Isolated) የነበረችው አገራችን ተፈላጊ ሁና ቁጭ አለች። በአንጻሩ ሶማሌ ቀውስ ላይ እንጀራውን ስታበስል የከረመችው ወያኔ አስፈላጊነቷ አብቅቶ expired አደረገች። የህወሓት መንግስት የበዛውን የሁለቱን ሀገራት ድንበር ስለምትቆጣጣጠር እና ከፌደራሉ መንግስት ትእዛዝ ስላፈነገጠች በድንበር ያለው እንቅስቃሴ እና የአልጀርሱን ውል ተፈጻሚ ለማድረግ በቅርቡ ባይቻልም፤ ከአሁን ቡኋላ ህወሃት አይደለም አለም አቀፉ ፓለቲካ ላይ ኢትዮ-ኤርትራ ፓለቲካ ላይ እንኳን ተጽእኖም ቦታም የላትም።

ለኤርትራ ግን ይህ ግዜ ከምንግዜውም የበለጠ አመቺ ነው፤ "ለሁሉም ግዜ አለው" እንዳለው ጠቢቡ።
አሁን ግን ወደዳቹህም ጠላቹህም ላለፍት 70 ዓመታት ከኤርትራ ህዝብ ፍላጎት እና ጥቅም ጎን ያልነበረው የሀያላኑ የፓለቲካ ጥቅም ዛሬ ከኤርትራ ጎን ቁሞ መገኘቱ ነው ቁምነገሩ። ይህም ዝም ብሎ የተፈጠረ እና የተገኘ ሳይሆን ህዝባችን በከፈለው ከፍተኛ መስዋእትነት፣ ትእግስት እና ጽናት ነው። ነገርግን ይህን መልካም አጋጣሚ ልክ እንደ 60ዎቹ በፓለቲካ፣ በእምነት እና በብሄር ህዝባችን ከፋፍለው ኤርትራ ሀገራችን ወደ ኋላ ለመጎተት ለሚተጉ ጠላቶቻችን ተለዋዋጭ ዘዴዎቻቸው መንቃት ይገባናል።