Page 1 of 1

ከባድ ፍንዳታ በኤርትራ!* በ87 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የሚገነባው ይህ መንገድ 183 አነስተኛ ድልድዮችን ይዞአል። 10 ግዙፍ ድልድዮች። ረጅሙ ድልድይ 140 ሜትር ይረዝማል።/ ተስፋዬ ገብረአብ

Posted: 14 Jan 2020, 11:12
by MatiT
ከባድ ፍንዳታ በኤርትራ!

በሓበላ እና በሊባን በኩል እስከ ማይ ሓሊብ ተጉዤ ገና አሁን ተመልሼ አስመራ ገባሁ። ከአዲጉዋእዳድ እስከ አቆርዳት የሚሰራው መንገድ እየተጣደፈ ነው። "ሓበላ የሽፍታ አገር" ተብሎ ይታወቃል። ቁልቁለቱን ወርደን የማይ ሓሊብ ወንዝ በሩቅ መታየት ሲጀምር ከባድ ፍንዳታ ምድሩን አንቀጠቀጠው። ተራሮቹን በTNT እየደረመሱ መሆኑ ገባኝ።

በ87 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የሚገነባው ይህ መንገድ 183 አነስተኛ ድልድዮችን ይዞአል። 10 ግዙፍ ድልድዮች። ረጅሙ ድልድይ 140 ሜትር ይረዝማል። ኮንትራቱን ወስዶ የሚሰራው አንድ የቻይና ኩባንያ መሆኑን ተረድቻለሁ። እንደገና ታላቅ ፍንዳታ ሰማሁ። ሓበላ እና ሊባን ተንቀጠቀጡ!!