Page 1 of 1

የኢዜማ/ግንቦት 7 ከፍተኛ አመራር የሆነው ዳንኤል ሽበሽ ስለ ኢዜማ/ግንቦት 7 የቁም ሞት የሰጠው የኑዛዜ ቃል!!

Posted: 13 Jan 2020, 21:08
by Maxi
የኢዜማ/ግንቦት 7 ከፍተኛ አመራር የሆነው ዳንኤል ሽበሽ ስለ ኢዜማ/ግንቦት 7 የቁም ሞት የሰጠው የኑዛዜ ቃል!! :lol: :lol: :lol:

Daniel Shibeshi

አለን!
... አለን! እየተገለባበጥን፤ ዋሽቶ መኖር ለምዶብን፣ ከደም ሥጋ ተዋህዶልን አለን!!! አዎን አለን! ለሁሉም ምቹ ሎሌ ሆነን፤ ጠቅላዮቻችን ሲቀያየሩ እየተቀያየርን፣ እየተገለባበጥን አለን! ክብሩ ይስፋው ብለን፡፡ በፕሬዝዳንትነት ጀምረው በጠቅላይነት ላጠናቀቁ ርካብ ሆነን፣ እርሳቸውን መስለን፣ ለርሳቸው መንበር ተመቻምቸን፤ ለእርሳቸው የይኑር ምስጢር ቁጥሩ (Password) ተቀይሮባቸው በኃማደ ሲተኩ አቤት ጌታዬ ብለን ቀጥሎም ዐቢይ ሚንስትር'ንም በጭብጨባ አደምቀን፤ ርዕዮተ ዓለም ብን ብሎ ሲጠፋ ምንም ትን ሳይለን አለን ዓይናችንን በጨው አጥበን አክሮባት እየሰራን፤ አለን! እየተገለባበጥን ሳንሰጥ በመቀበል መኖርን ለምደን፥ ነውርን እንደ ክብር ቆጥረን አለን! መጪውን ለመቀበል እየተዘረጋን፥እየተዘጋጅን፡፡

አለን! ከተቀረው ኢትዮጵያ ክፍል ተባርረን አዲስ አበባ ላይ ከትመን፣ አይናችሁ ላፈር ብንባልም ያው አለን ይሉኝታ ቢስ ፈጣጣ ሆነን አለን ሆዳችን አክብረን፤ እንደ ገደል ማሚቱ ያሉንን እየደገምን፤ አ.ዴ ሲሉን አዴ! መደመር ሲሉን መደመር! ብለን ፣ ብልጽግና ሲሉን እዛው ደግመን አለን! መኖር እንዲህ ከሆነ፡፡

አዎን! አለን
እምቢ! ለምን? መጠየቂያችንን ፥ ማሰቢያችንን የነጠቀንን ገዥውን እያመሰገነን፤ ምን ታመጣላችሁ? ለጉንጫችን ይመቸን ለጨጓራችን ይድላልን እንጂ እኛማ አለን ከሚመጣው ሁሉ ጋር ሰልፋችንን አሳምረን፤ የመጣውን ሁሉ መስለን፡፡ አለን! የፖለቲካ ጨዋታ ችለናል ብለን፣ የዕውቀት ጥግ መስሎን፤ ነውርን ተሸልመን፤ አዎን አለን...! ብዙዎችን እምሽክ! ጭጭ ድፍጥጥ አስደርገን! ምንም እንዳልተፈጠረ ቆጥረን ከሚያውቀን ከወለደን ካሳደገን ሕዝብ ራቅ! ዞር! ዞር ብለን አለን ይመስገነው ብለን እሱ ይቀበለው አይቀበለው ባናውቅም፡፡ ..."ባይበላስ ቢቀር"ን ኀላ ቀር ዘፈን ነው ብለን...አለን! ደግሞም ለእንኖራለን ተገዝተን፤ ለሚያኖረን እጅ ነስተን ፡፡

- ፎቶ ክሬዲት ለኢሳት!
- ከህልና መቆሸሽ ይሰውራችሁ! ከነውር ይደብቃችሁ፡፡
- ማስታወሻነት በተመሳሳይ ሙድ ውስጥ ለሚኖሩ አክሮባትስቶች ይሁንልን

Please wait, video is loading...