Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Post Reply
QB
Member
Posts: 1094
Joined: 05 Dec 2012, 15:14

Tesfaye Gebreab "አቢይ ለኦሮሞና ለኢትዮጵያ 'Necessary Evil' ነው።"

Post by QB » 13 Jan 2020, 12:20

"አቢይ ለኦሮሞና ለኢትዮጵያ 'Necessary Evil' ነው።"

ዛሬ ማለዳ "ኦሮሚያ! - እንደ ደቡብ አፍሪቃ" በሚል ርእስ አንድ ጽሁፍ አስፍሬ ነበር።

ይዘቱ ባጭሩ "የዳውድ - መረራ ግንባር" በመጪው ምርጫ ኦሮሚያን ቢቆጣጠር በኦሮምያ የሚኖሩ ሌሎች ብሄሮችን እንደማይጎዳ፣ በግልባጩ ሁሉን አቅፎ ሊይዝ እንደሚችል የሚጠቁም በጎ የሚተነብይ ጽሁፍ ነበር።

ጽሁፉ በኔ FB ገጽ ከተሰራጨ ከሶስት ሰአታት በሁዋላ በኢሜይል አንድ አስደንጋጭ መልእክት ደረሰኝ።

በጣም በጣም የማከብረው፣ በሚዛናዊ አስተሳሰቡ ፍጹም የማልጠራጠረው ኦሮሞ ወዳጄ የሚከተለውን ደብዳቤ ላከልኝ።

"ለዳውድ - መረራ ግንባር ድልን የተመኘህበት ወይም የተነበይህበትን Post አይቼ ፈገግ አልሁ። 'ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ ነው' የሚለው የአማሮች ተረት መጣብኝናም ትንሽ ተከዝሁ። 'አልሰሜን ግባ በለው' የሚለውንም አባባል ልትወስደው ትችላለህ። ዳውድ፣ በቀለና ጃዋር የወያኔ ባለሟሎች ሆነው መቅረታቸውን፣ የኦሮሞን ሕዝብ ትግል በገንዘብ መለወጣቸውን እያዘንሁ አረዳሃለሁ። እስከነችግሩ በአብይ ላይ ያነጣጠረ ቀስትህን አውርድ። አቢይ አሁን ለኦሮሞና ለኢትዮጵያ 'Necessary Evil' ነው።"

ይህን ደብዳቤ እንዳነበብኩ ቁጭ ባልኩበት ደነዘዝኩ። በመቀጠል በጣም ስሜታዊ ሆንኩ። ራሴን መቆጣጠር አልቻልኩም። በFB ግጽ ሰሞኑን ስጽፋቸው የነበሩትን ሁሉ ደመሰስኩ። ስልኬን ብሰባብረው ጭምር በወደድኩ።

ህሊናዬ መጣና ጮኸብኝ፣

"ለምን አርፈህ የስነጽሁፍ ስራህን አትሰራም? ውጣ ከፖለቲካ!!"

"ግለሰብ ነኝ። የኦሮሞ ማህበረሰብ አባል ነኝ። መሳተፍ መብቴ ነው!"

"ኦሮሞ አይደለህም። ራስህን አታታልል። ማንም አይቀበልህም።"

"ኦሮሞ ነኝ!"

"እሺ ይሁንልህ! ኦሮሞ ነህ እንበል! ግን በቃ ይቅርብህ። በዚህ ቀውጢ ጊዜ ዳር ቆመህ መታዘብ ይሻልሃል። የ31 አመታት ጥብቅ ኦሮሞ ወዳጅህ የጻፈልህን አየህ? አንተ ከሱ በላይ ኦሮሞ መሆን አትችልም። ከሱ በላይ ለኦሮሞ ልትቆረቆር አትችልም። ይሁን ቢባል እንኩዋ ጊዜው አደገኛ ነው። ከፖለቲካ ራቅ። ምናገባህ?"

"እና ምን ላድርግ?"

"FB ላይ መጻፍ አቁም።"

"መጻፍ ግን እፈልጋለሁ።"

"እንግዲያው ፖለቲካ ውስጥ አትግባ። ከፖለቲካ ውጭ የሆነ ወግ ብቻ ጻፍ። ፖለቲካውን ተው። ፈንጂ ነው። ቁስል ነው። አንተ ደግሞ ኤርትራዊ ነህ።"

ከ2020 ጀምሮ ቢራ መጠጣት አቁሜ ነበር። ባለፉት 12 ቀናት "ጠንቁዋዩ" ተብሎ በሚታወቀው ጥንታዊ የቻይና ስኒ እንኩዋ ቢራ እንዳልቀመስኩ በመሃላ ማረጋገጥ እችላለሁ። ዛሬ ግን ከመጠን በላይ ስለተረበሽኩ ራሴን ለማረጋጋት ወይም ድንጋጤዬን ለመበተን በሁለት ሰአታት ውስጥ አምስት የአስመራ ቢራ ቁዋ-ገጭ አደረግሁ።

ሞቅ ሲለኝ ድንጋጤዬ ለቀቀኝ።

መኪናዬን አስነስቼ ወደ መንደፈራ መንገድ ነዳሁ። በመጠጡ ሃይል ከተገቢው ፍጥነት በላይ መንዳቴ አልታወቀኝም። የሞተረኛ ትራፊክ ፖሊስ ከሁዋላ እንደሚከተለኝ ሳውቅ እየተበሳጨሁ ዳር ይዤ ቆምኩ።

ወረደ እና ሰላምታ ሰጠኝ።
እና ግን ወዲያው አወቀኝ።
በስሜት እንዲህ አለ።

"በቅርቡ ERI TV ላይ ቃለመጠይቅ ስትሰጥ ሰማሁህ። ጥሩ ነበር። በተለይ ስለ ኤርትራውያን ወጣቶች የተናገርከው በጣም ስቦኛል። አምላክ አሳብክን ያስምርልህ። ደህና ነህ ግን?"

ዘና አልኩ።
ከቅጣት መዳኔን አረጋገጥኩ። ትንፋሼ ቢለካ 1300 ናቅፋ እንደምቀጣ አውቅ ነበር።

ጥቂት ካወጋን በሁዋላ፣

"አነዳድህ ልክ አልነበረም።" አለኝ።

"ይቅርታ ተረብሼ ነበር።"

"ምነው በደህና? ምን ሆንክ?"

"ታሪኩ ረጅም ነው።"

"በል ረጋ ብለህ ንዳ! ለዛሬ አምልጠሃል።"

"አመሰግናለሁ ወንድሜ!"

እና ረጋ ብዬ እየነዳሁ ከአስመራ ከተማ ወጣሁ። በእርሻዎች መካከል ስደርስ መኪናዬን አቆምኩ እና ወረድኩ። አይኖቼ በሩቅ ያሉ ተራሮችን አዩ። ለጥ ባለው ሁዳድ ላይ አይኖቼን እስከ አድማስ ዘረጋሁ።

እናም እንዲህ ስል ጮህኩ፣

"ከቶ ሊሆን አይችልም!
በፍጹም! በፍጹም!!
በፍጹም ሊሆን አይችልም!!
በዚህ ወሳኝ ዘመን. . .
የኦሮሞ ህዝብ እየደገፋቸው. . .
የኦሮሞ የፖለቲካ ሃይሎች . . .
ከቶ ወደ ወያኔ ለመሄድ ለምን ይገደዳሉ?
ምን ለማግኘት?
ገንዘብ?
ጭንቅላት?
ህዝብ ብዛት?
ሁሉም አላቸው።
ሰው የሌለውን እንጂ ያለውን አይፈልግም!!
ከቶ ሊሆን አይችልም!!!
ኦሮሞ እንደ እፉኝት ልጆች አባት እና እናቱን አይገድልም!"

ይህን በጩኸት ስናገር በሩቅ እመለከታቸው የነበሩ የከበሳ ኤርትራ ተራሮችን ማየት አልቻልኩም። አይኔ ላይ ብዥ አለብኝ!!

https://www.facebook.com/photo.php?fbid ... =3&theater

Za-Ilmaknun
Member
Posts: 2018
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

Re: Tesfaye Gebreab "አቢይ ለኦሮሞና ለኢትዮጵያ 'Necessary Evil' ነው።"

Post by Za-Ilmaknun » 13 Jan 2020, 13:07

"ለምን አርፈህ የስነጽሁፍ ስራህን አትሰራም? ውጣ ከፖለቲካ!!"

"ግለሰብ ነኝ። የኦሮሞ ማህበረሰብ አባል ነኝ። መሳተፍ መብቴ ነው!"

"ኦሮሞ አይደለህም። ራስህን አታታልል። ማንም አይቀበልህም።"

"ኦሮሞ ነኝ!"

Teshfish is really something... :lol: :lol: :lol: Ahehe How long is this jock going to continue?

Dawi
Member
Posts: 3477
Joined: 30 Aug 2016, 03:47

Re: Tesfaye Gebreab "አቢይ ለኦሮሞና ለኢትዮጵያ 'Necessary Evil' ነው።"

Post by Dawi » 13 Jan 2020, 13:29

QB wrote:
13 Jan 2020, 12:20
"ከቶ ሊሆን አይችልም!
በፍጹም! በፍጹም!!
በፍጹም ሊሆን አይችልም!!
በዚህ ወሳኝ ዘመን. . .
የኦሮሞ ህዝብ እየደገፋቸው. . .
የኦሮሞ የፖለቲካ ሃይሎች . . .
ከቶ ወደ ወያኔ ለመሄድ ለምን ይገደዳሉ?
ቅቤ:

ወደ ወያኔ ለመሄድ የሚገደዱት በአስተሳሰብ ስለሚስማሙ ነው፣ ሌላ ሚስጥር የለውም፤

ክልል በሚሉት የበላይነቱን መቀጠል ይፈልጋሉ፣

በክልላቸው ያለውን "አፓርታይድ" ስርዐት እንዲቀጥል ይፈልጋሉ፤

ከነሱ የተለዩ ብሔሮች የክልል ባለቤት አይደሉም፣ ከአንድ ኬንያዊ የበለጠ መብት የላቸውም።

ይሄ ሰውዬ (ተስፋዬ) የፖለቲካ መሐይም ነው፣ ተረቱን ለመፃፍ መወሰኑ ተገቢ ነው፤

Zreal
Member
Posts: 474
Joined: 15 Mar 2019, 20:33

Re: Tesfaye Gebreab "አቢይ ለኦሮሞና ለኢትዮጵያ 'Necessary Evil' ነው።"

Post by Zreal » 14 Jan 2020, 19:45

Tesfaye Gebreab "አቢይ ለኦሮሞና ለኢትዮጵያ 'Necessary Evil' ነው።" :P :P :P