Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Hameddibewoyane
Member
Posts: 3890
Joined: 25 Sep 2019, 02:42

የትህነግ የግድያ ሙከራ፣ የዓረና ፈተናና አሳሳቢው የአብይ ዝምታ!

Post by Hameddibewoyane » 22 Dec 2019, 10:31

የዓረናው ጀግና ኃይለኪሮስ ታፈረን በመርዝ ለመግደል የተደረገ ሙከራ በሀኪሞች ብርታት መክሸፉን ሰምተናል። ወንድማችን እንኳን ከሞት አተረፈልን።

ትህነግ እንደ ኃይለኪሮስ ታፈረ የመሰለ በግልጽ የሚኮንናቸው ጀግና አይደለም፣ ፊቱን አይተው የኛ ተቃዋሚ ሳይሆን አይቀርም የሚሉትን ሰው በተለያዩ መንገዶች ሲገድሉ የኖሩ ወንጀለኞች ናቸው። ይህ አካሄዳቸው ደግሞ የስልጣን ምንጫቸው አርገው ይወስዱታል። የትህነግ ታሪክ የተገነባው እነሱ ገዳይ፣ ሌላው ተገዳይ በመሆን ነው።

ጠ/ሚ አብይ አህመድ የባንዳዎች ጥርቅም የሆነውን ትህነግ ቢጠየፍ ተገቢ ነው። እንደ ዓረና ትግራይ የመሰሉ በወጣት ፖለቲከኞች የተገነባ ኢትዮጵያዊ ድርጅት ግን መርዳት ተገቢ ነበር። ለምን? ለኢትዮጵያ ቁጥር አንድ የስጋት ምንጭ የሆነው ትህነግን በግንባር ቀደምትነት እየታገለ ያለ ድርጅት ሌላ ሳይሆን ዓረና ትግራይ በመሆኑ ነው።

ዓረናን አጠናክሮ የትግራይን ህዝብ ከትህነግ የባርነት አገዛዝ ነፃ አውጥቶ፣ በትግራይ ህዝብና በትህነግ ያለችውን ቀጭን ገመድ በጥሶ፣ ትህነግን ወደ መቃብር መሸኘት ሲገባ፣ ዶ/ር አብይ ለሌሎች ተቃዋሚ ድርጅቶች የሚያደርገውን ድጋፍ የሰናፍጭ ታክል እንኳን ለዓረና ለምን ሊሰጥ እንዳልፈለገ ግራ የሚያጋባ ነው።

ደርግ ትግራይን “ያውላችሁ!” ብሎ ለኢትዮጵያ ጠላት አስረክቦ ሲወጣ፤ ለሀገራዊ ችግር መፍትሄ ያገኘ መስሎት እንጂ እድሜውን እንደሚያጥር አውቆ አልነበረም። አብይም በዚያ ጎዳና እየሄደ ነው። መካሪ ካለህ፤ ተመለስ በለው!
አብርሃ በላይ

Weyane.is.dead
Member+
Posts: 6796
Joined: 19 Oct 2017, 11:19

Re: የትህነግ የግድያ ሙከራ፣ የዓረና ፈተናና አሳሳቢው የአብይ ዝምታ!

Post by Weyane.is.dead » 22 Dec 2019, 11:08

Leba weyanes will do anything to [deleted] tigray dry and bankrupt. Its time for tigrayans to get rid of weyanes using their own medicine, poison.

Digital Weyane
Member+
Posts: 8533
Joined: 19 Jun 2019, 21:45

Re: የትህነግ የግድያ ሙከራ፣ የዓረና ፈተናና አሳሳቢው የአብይ ዝምታ!

Post by Digital Weyane » 22 Dec 2019, 23:12

Beka! I have made up my mind. I will join ARENA and STOP accepting drink offers from my Weyane brother Awash for safety reasons. :roll: :roll: :roll:

Post Reply