Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

እየተስረቀረቁ “. . . ያጎደልነው ነገር ካለ መጠየቅ አለብን. . .” አዞዎቹ!

Post by Meleket » 20 Dec 2019, 11:31

https://www.bbc.com/amharic/news-50859219

አሄሄ አሁን ማ’ይሙት ያጎደላችሁት ነገር ጠፍቷችሁ ነው የምትጠየቁት? የሌባ ዓይነ ደረቅ . . . ! :mrgreen:

ከዋንኞቹ አጋሮቻችንና ጎረቤቶቻችን ከኤርትራዉያን ወንድሞቻችን ጋር ያለንን የሰላም አላማ እንዳንተገብር፣ በኤርትራ ልዑላዊ ምድር ሰፍሮ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ሰራዊት ጓዙን ጠቅልሎ እንዲወጣ ባዘዘው መሰረት፣ ከኤርትራ ልዑላዊ ምድር ሊወጣ ሲል እንቅፋት የፈጠራችሁትና ጉዳዩም በሰላም እልባት እንዳያገኝ እንወክለዋለን የምትሉትን ህዝብ ያወናበዳችሁ ብቻ ሳይሆን እንቅፋት እንዲፈጠር ሴራን የጎነጎናችሁ እናንተም’ማደላችሁ? :lol:

በህግ የሚጠየቁ ቀንደኛ ወንጀለኞችን በጉያችሁ ወትፋችሁ የህግ ልዕልና እንዳይከበር ለማእከላዊው መንግስት ወንጀለኞቹን ከማስረከብ አሻፈረኝ ያላችሁ እናንተም’ማደላችሁ? . . . :mrgreen:

ያገሪቱን ካዝና ያጎደላችሁት ሳይሆን ያሟጠጣችሁት እናንተ’ማደላችሁ? . . . :lol:

እያሉ ጠቅላዩና ብልጽግናዎች እንዲጠይቋችሁ ነው እንዴ የፈለጋችሁት . . . አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይሰማም! ሲቆነጥጡት ማለትም ምዥልግ ሲያደርጉት ግን ...!
:mrgreen:

ቁንጥጫዋ ስራዋን ስትሰራ እንዲህ እንዲህም ታለቃቅሳላችሁ . . .

http://www.tigraionline.com/articles/ti ... -abiy.html

ጨው ለራስህ ብለህ ጣፍጥ ነው ነገሩ አለበለዚያ “ንገርኒ’ዶ ሃለፋይን ማፏጨት ነው!” :mrgreen: