እስክንድር በመሀከላችን በመሆኑ በጣም ኩራት ይሰማኛል: ይህን የመሰለ ሰው ማገኘታችን እድለኞች ነን ማለት ይቻላል:: ምናልባትም እስክንድርን የሚያህል ሰው በአሁኑ ሰዓት ያላት አይመስለንም::
አንዳንዶች እስክንድርን ከማህተመ ጋንዲ ጋር ያመሳስሉታል:: ፅናቱ መቼም አስደማሚ ነው:: በቅርቡ በአገራችን በተነሳው ቀውስ እስክንድር ላይ የተደቀነው አደጋ ሁላችንንም አሳሥቦን ነበር:: ግን ነገሮች ወደ ጥሩ ሁናቴ እየተለወጠ ነው:: እስክንድር ከሀገር መውጣቱ ደሞ: ሕልውናውን እንዲያብብ አርጎታል:: እውቅና ካላቸው መንግሥታትና ድርጅቶች ጋር መገናኘቱ: የእሱን ተፈላጊነት ያሳየ እና ጥሩ ጥበቃና ክትትል እንዲደረግለት ያደረገ ነው:: ደፍረን በእስክንድር ላይ ያለው አደጋ ቀንሷል ማለት እንችላለን ::
ግን በጣም ሙገሳና ጭብጨባ በዛ :: እኛ አገር ዛሬ የተጨበጨበለት ነገ ስሙ በአሽሙር እንደሚነሳ እናቃለን:: እናም እስክንድር ይህን ከመጠን ያለፈ ሙገሳ እና ጭብጨባ ማስቆም ነበረበት: አሁንም ማረግ አለበት:: ይህ አጉል ሙገሳ የሚሰራውን ሥራ ሊያሰተጓጉል ይችላል::
እስክንድር የሰውን ሙገሳና ልገሳን ከቁም ነገር መቁጠር የለበትም::
እስክንድር አሁን ወደ አገር ቤት ተመልሶ ስራውን መስራት አለበት:: ባልደራስን ወደ ፓርቲ መቀየርና የአባላት ምዝገባ በሀገሪቱ ሁሉ ማድረግ አስፈላጊ ነው:: ይህ በጣም ወሳኝ ነው::
-
- Member
- Posts: 4208
- Joined: 27 Sep 2017, 21:56