Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sholagebya
Member
Posts: 494
Joined: 27 Oct 2014, 15:59

የታህሳስ 59ኛው ዓመት መታሰቢያ።

Post by sholagebya » 13 Dec 2019, 19:45

ብርሃኑ አስረስና በሪሁን ከበደ የሚባሉ ሁለት ጎንደሬ የታሪክ ጸሐፊዎች ለንጉሥ አጼ ኃይለሥላሴ ባላቸው ከመጠን ያለፈ ፍቅር የተነሳ መጽሐፋቸው ሚዛናዊ ሊሆን አይችልም :: የአቶ ብርሃኑ አስረስን ስለ ታኅሳሱ ግርግር የጻፉትን መጽሐፍ አላነብኩትም :: የአቶ በሪሁን የበሪሁን ከበደ መጽሐፍ ግን በኢጣሊያን ጊዜ የነበሩ የጎንደር አርበኞች ያሳዘነ መጽሐፍ ነው :: የአርበኞችን ታሪክ ለንጉሡ ያልነበሩበትን የኢጣሊያ የወረራ የጦርነት ታሪክ የፈጠራ የውሸት የጀግንነት ታሪክ መስክረዋል :: መጽሓፉ በጣም ትልቅ ኢንሳይክሎፒዲያ የሚያክል አብዛኛው የውሸት የፈጠራ ታሪክ የታጨቀ ነው :: የሚያሳዝነው አቶ በሪሁን ከበደ ከንጉሡ ለዚህ ትልቅ የውሸት የፈጠራ ታሪክ መጽሐፍ የተሰጣቸው ሹመት በወሎ ክፍለ ሀገር የአንድ የወረዳ ዳኛ መሆን ብቻ ነው :: በርግጥ የአቶ ብርሃኑ አስረስን መጽሐፍን ገዝቸ ለማንበብ እሞክራለሁ :: ሹመትና ከሰዎች ተቀባይነት ለማግኘት አጥብቆ የሚሻ ሰው ግን የታሪክ መጽሐፍ ጸሐፊ ባይሆን ይመረጣል :: የጀኔራል መንግሥቱንና የግርማሜ ንዋይን የመንፈቅለ-መንግሥት ሙከራ ብዙ የአፈጻጻምና ( executions ) ችግር ቢኖርበትም አላማቸው ቀናኢና ለሕዝብ በማሰብ ነበር :: ያ እጅግ ኃላቀር ሥርአትና የዘውድ አገዛዝ ለአብዛኛው የኢትዮጵያ ጭቁን ሕዝብ ምን አይነት እንደነበር የምናውቅ እናውቃለን :: ጀኔራል መንግሥቱና ግርማሜ ንዋይ በዚያ ድቅድቅ ጨለማ ትንሽ የፋኖስ መብራት ለማፈንጠቅ የሞከሩ የመጀመሪያዎች የለውጥ ኃዋሪያት ናቸው :: << ንጉሥ አይከሰስ ሰማይ አይታረስ >> የሚለውን የአምልኮትና የፍራቻ ቆፈን የደፈሩ የእምየ የኢትዮጵያ ልጆች ናቸው ::