Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abaymado
Member
Posts: 4213
Joined: 27 Sep 2017, 21:56

ደብረብረሃን በኢንቨስትመንት የተንበሸበሸች ከተማ! 29 ቢልዮን ብር በላይ ያስቆጠሩ ባለሀብቶች ሲንቀሳቀሱባት: 20 ኢንዱስትሪዎች ሥራ ላይ ናቸው!

Post by Abaymado » 10 Dec 2019, 14:09

በአገራችን ይሄን ያህል ከፍተኛ ብር ያስመዘገቡባት ከተማ መኖሯ ያጠራጥራል; ምናልባት አዲስ አበባ ብቻ ናት የምትሆነው::

ኢንዱስትሪዎቹ ከ 10,000 በላይ ሰራተኞች እንደቀጠሩ ነው የሚነገረው:: በግንባታ ላይና በሃይ እጥረት ላይ ke236 የኢንደስትሪ ዘርፎች ሲጠናቀቁ 48,000 በላይ ሰዎችን መቅጠር ይችላል::
ሌሎቹ የአማራ ከተሞች ከሁለት ቢልዮን ብር በላይ የኢንቨስትመንት ፍስት እንደሌላችው ሲነገር ጎንደር ብቻ ግን 8 ቢልዮን ብር ላይ ትገኛለች:: የደብረብረሃን ግን በጣም የሚገርም አርጎታል::
ደብረብረሃን ከሌሎቹ በተለየ ኢንደስትሪውችዋ የተለያዩ ምርቶችን ያወጣሉ::

"
በችግሮችም ውስጥ ደብረ ብርሃን የኢንዱስትሪ ብርሃን እየፈነጠቀች ነው።
ለክፍለ ዘመናት የተዳደረችበት ግብርና በ21ኛው ክፍለ ዘመንም ጥያቄዎቿን መመለስ አላስቻለም፡፡ አሁን ፊቷን ወደ ኢንዱሰትሪ መር ማዞሯን ተከትሎ ለብልፅግና የጣለችው መሠረት ዓይን እንዲበዛባት አድርጓታል፡፡ የቀድሟዋ ደብረ ኤባ በአፄ ዘርዓ ያዕቆብ የስም ለውጥ አድርጋ ደብረ ብርሃን ተብላለች፡፡

ክፍለ ዘመናትን የተሻገረ ታሪክ ያላት ደብረ ብርሃን ዘመናዊ ታሪኳን ልታዘምን በአዲስ የኢንቨስትመንት መነቃቃት ላይ ትገኛለች። በአርብቶ እና አርሶ አደር ቀንበር እየጎተተች ዘመናትን ተሻግራ ከዚህ ደርሳለች፡፡ ከ10 ዓመታት በፊት በደብረ ብርሃን ብርድ ልብስና በአኳ ሴፍ ውሃ ፋብሪካ ብቻ ትታወቅ ነበር፡፡ ባለፉት አምስት ዓመታት ደግሞ የሕዝቧቿ ቁጥር ማደግ ፣ ከዘመናዊ ስልጣኔዎቿ ጋር መላመድ በመጀመራቸው ሀገሪቱ የኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ ለመፍጠር በምታደርገው ጥረትም ከአማራ ክልል ከተሞች ቀዳሚነቷን እያሳየች ነው፡፡
ያልዘመነው የሀገሪቱ የኃይል አገልግሎት እና የመሠረተ ልማት አለመሟላት ፈተና ቢሆናትም የመሪዎቿ የኢንቨስትመንት ርሀብ፣ የዜጎቹ የመልማት ጥያቄ 461 ከፍተኛ የአገልግሎት እና የአምራች ዘርፍ ድርጅቶች ተሠማርተዋል፡፡ ከ29 ቢሊዮን 102 ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሀብቶች የሚያለሙባት ደብረ ብርሃን የከተማ አስተዳደሩ ቀልጣፋ መስተንግዶ የሕዝቦቿ ሠላማዊነት እና ተባበሪነት ምክንያት ኢንቨስትመንቱ በተረጋጋ አሠራር ቀጥሏል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ከኢንዱስትሪ መንደር ውስጥ እና ውጭ 20 ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች ሥራ ጀምረው ከ4 ሺህ 600 በላይ የሥራ ዕድል ፈጥረዋል፡፡ ሥራ የጀመሩ ስምንት በግብርና ኢንቨስትመንት ፕሮጀክት፣197 የአገልግሎት ኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን ጨምሮ 20 የኢንዱስትሪ አምራች ዘርፎች በከተማዋ ከ10 ሺህ 500 በላይ ጊዜያዊ እና ቋሚ የሥራ ዕድል መፍጠሩን ከደብረ ብርሃን ከተማ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ በኃይል እጥረት እና በግንባታ ሂደት ላይ ያሉ 236 የኢንዱስትሪ ዘርፎች ሲጠናቀቁ ከ48 ሺህ 700 በላይ ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል የሚፈጥሩ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
የደብረ ብርሃን የኢንዱስትሪ ተሰፋ በአማራ ክልል ካሉ ጎንደር፣ ደብረ ታቦር፣ ወልዲያ እና ደሴ ከተማ ካሉ የኢንቨስትመንት እና ኢንዱስትሪ እንቅስቃሴዎች በድምር በእጥፍ የተሻለ እንደሆነ የአብመድ ጋዜጠኞች ቡድን ተዘዋውሮ ሲመለከት አረጋግጧል፡፡ በእነዚህ ከተሞች ያለው ዘርፍ የሥራ ዕድል ከፍተኛው 500 ሌሎች በአማካኝ 200 ዜጎችን ብቻ ሊቀጥሩ የሚችሉ ሲሆኑ ደብረ ብርሃን ላይ ግን ከ10 ሺህ 500 በላይ የሥራ ዕድል መፍጠር ተችሏል።
አብዛኛው በአማራ ክልል ከተሞች የኢንቨስትመንት ተሳትፏቸው ከዱቄት እና የንፅህና መስጫ ማምረት የዘለለ አይደለም፡፡ ደብረ ብርሃን ግን በአራቱም የኢንዱስትሪ መንደሮች እና ከኢንዱስትሪ መንደር ውጭ ተመጋጋቢ ፋብሪካዎች የሚገኙበት የኢንዱስትሪ ከተማ ናት፡፡ በደብረ ብርሃን ከ29 ቢሊዮን ብር በላይ ያስመዘገቡ ባለሀብቶች የከተማዋን ኢኮኖሚ ማዕከልነት ሊያረጋግጡ ሥራ ላይ ናቸው፡፡ በሌሎች የአማራ ክልል ከተሞች ጎንደር ከተማ 8 ቢሊዮን ብር በላይ ካለው በቀር በአማካኝ 2 ቢሊዮን ብር ገደማ ካፒታል ናቸው፡፡
በደብረ ብርሃን አስተማማኝ ሠላም እንዲፈጠር ነዋሪዎቿ ያደረጉት ርብርብ ለኢንዱስትሪው መስፋፋት ትልቅ ሚና ተጫውቷል ይላሉ የከተማዋ ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ገብረሕይወት፡፡ ሌላው ደግሞ የባለሀብቶችን ኢንቨስትመንት ጥናት የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በ10 ቀናት ውስጥ ተወያይቶ ያለቢሮክራሲ የመሥጠት ልምዱ ማደጉ እንደሆነ አመልክተዋል፡፡
የአማይራ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ የሰው ሀብት አስተዳድርና የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ ተወካይ ጌታቸው ጫኔ "በደብረ ብርሃን ከዞን እስከ ከተማ አስተዳድር ያሉ ኃላፊዎች ለኢንቨስትመንት እጅግ ቅርብና እንደ ጓደኛ በቅንነት ነው የሚያስተናግዱ" ብለዋል፡፡ አቶ ጌታቸው ለከተማዋ ኢንዱስትሪ ማዕከልነት ከመሪዎች ቁርጠኝነት በተጨማሪ በድርጅታቸው የተቀጠሩ 98 ቋሚ ሠራተኞች የሥራ ባሕል ዘርፍ እንደሚያበረታታ ተናግረዋል፡፡
ከስድስት ዓመታት በፊት በ150 ሺህ ካፒታል ተነስቶ የቺዘር ወተት ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ባለቤት የሆነው ወጣት መለኮት እሸቱ የደብረ ብርሃን ከተማ መሪዎች ለኢንቨስትመንት ቅርብ በመሆናቸው ሥራውን ወደ ፋብሪካ እንዲያሳድገው እንደረዱት ተናግሯል፡፡ ከ2 ሺህ አርሶ አደሮች ጋር የወተት ግብይት የገበያ ትስስር የፈጠረው ፋብሪካው 70 ቋሚ እና 50 የሚደርሱ ጊዜያዊ የሥራ ዕድል ተጠቃሚዎችን መያዙን ወጣት መለኮት ነግሮናል፡፡
ከቺዘር ወተት ፋብሪካ ላይ በቋሚ የሥራ ዕድል በየወሩ ከሦስት ሺህ ብር በላይ እየተከፈላት የምትሠራዋ ወይዘሪት ማርየ ዘውዴ በተመረቀችበት ሙያ በመሥራቷ ሙያዋን እንድታዳብር እንደረዳት ተናግራለች፡፡ "በደብረ ብርሃን ኢንዱስትሪዎች መስፋፋታቸው ከመንግሥት ብቻ ይጠበቅ የነበረውን የሥራ ዕድል የግሉ ዘርፍ መጋራት መጀመሩ የሚበረታታ ነው" ብላለች፡፡
የጄኬ ኩኩቤራ አሉሙኒየም ፋብሪካ ባለቤት አቶ ኑኬንግ ጋርግ "ደብረ ብርሃን የሁሉም ከተማ ናት" ብለዋል፡፡ ይሁንእንጂ በኃይል አቅርቦት ችግር ምክንያት ፋብሪካዎች ሥራ ላይ ባለመዋላቸው ለኢኮኖሚው እና ለባለሀብቱ ከፍተኛ ኪሳራ እያመጣ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡ ለ50 ዜጎች የሥራ ዕድል የፈጠረው ድርጅታቸው ባለፉት ሦስት ወራት በኃይል አቅርቦት ችግር ምክንያት በጀነሬተር እየተጠቀመ በቀን አምስት ሺህ ብር ለነዳጅ እያወጡ ለኪሳራ እየተዳረጉ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
በደብረ ብርሃን ከጄኬ ኩኩቤራ አሉሙኒየም ፋብሪካን፣ ከራህማ ኑርየ አልሙኒየም እና ፕላስቲክ ፋብሪካን ጨምሮ ከስድስት ሺህ በላይ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር የሚችሉ 24 ፋብሪካዎች ግንባታ እና ማሽን ተክለው በኃይል አቅርቦት ምክንያት ብቻ ሙሉ በሙሉ ሥራ አልጀመሩም፡፡ በኃይል አቅም ማነስ ምክንያትም አብዛኞቹ ፋብሪካዎች በከፊል ለመሥራት መገደዳቸውን የአብመድ ጋዜጠኞች ቡድን ተዘዋውሮ ተመልክቷል፡፡
በከተማዋ በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ካሳ ከፍለው መሥራት የሚፈልጉ ባለሀብቶች በየዓመቱ ቢጨምርም የፌዴራል መንግሥት በዘርፉ አዋጅ እንጂ የአፈፃፀም መመሪያ ወይም ደንብ ባለማመላከቱ ለአሠራር መቸገራቸውን የከተማዋ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡ የውኃ እጥረትም የፋብሪካዎቿን የውኃ ጥም መቁረጥ አለመቻሉን የፋብሪካ ባለሀብቶች ተናግረዋል፡፡
‹‹ደብረ ብርሃን ከችግሯ ጋር ተጋፍጣ ለደረሰችበት ሂደት አብነት ለመሆን በቂ ነው ብላ አልተቀመጠችም›› ያሉት የኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ጽሕፈት ቤት ኃላፊው አቶ ብርሃኑ ገብረ ሕይወት "የኃይል እጥረቱን ሙሉ በሙሉ የሚፈታ 320 ሜጋ ዋት የሚያመነጭ ሰብስቴሽን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ገንብቷል" ብለዋል፡፡ ይሁን እንጂ ወደ ፋብሪካዎች ለመውሰድ የሚያስችለውን መስመር መዘርጋት የክልሉ ኃላፊነት በመሆኑ 9 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር ግምት አስወጥተው ምላሹን እየተጠባበቁ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ የውኃ እጥረቱን ለመፍታት ኢንዱሰትሪ ፓርኮች በየአቅራቢያቸው በማኅበር በመሆን የጥልቅ ጉድጎድ ቁፋሮ በማድረግ ችግሩን በራሳቸው እንዲፈቱ መነጋገራቸውንም አስታውቀዋል፡፡
"የኃይል እጥረቱን በቅርቡ እንደሚፈታ እምነት አለኝ" ያሉት ኃላፊው ከዚህ በፊት 10 ፕሮጀክቶች የአካባቢ ባለሀብቶች ተደራጅተው እንዲሠሩ የተደረገውን ተሞክሮ በማስፋትና 74 ተመጋጋቢ አምራች የኢንዱስትሪ ፋብሪካዎች እንዲኖሩ ዕቅድ ይዘው እየሠሩ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
በኢንዱስትሪዎች ልክ የሥራ ዕድል ፈጠራው እና የኢንዱስትሪ ሠራተኞች የደሞዝና የጥቅማጥቅም አሠራር ፍትሐዊ እንዲሆን በላቀ ርብርብ እንደሚሠሩ ለአብመድ ተናግረዋል፡፡"
https://www.facebook.com/AmharaMassMedi ... __tn__=K-R

gadaa2
Member
Posts: 2178
Joined: 15 Oct 2013, 15:40

Re: ደብረብረሃን በኢንቨስትመንት የተንበሸበሸች ከተማ! 29 ቢልዮን ብር በላይ ያስቆጠሩ ባለሀብቶች ሲንቀሳቀሱባት: 20 ኢንዱስትሪዎች ሥራ ላይ ናቸው!

Post by gadaa2 » 10 Dec 2019, 23:52

Abaymado wrote:
10 Dec 2019, 14:09

Good move DB is a city of Abichu people, I love her development. I wish all people in Ethiopia follow the same path.

Post Reply