Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Ejersa
Member
Posts: 3976
Joined: 05 Nov 2019, 10:39

ቀላል መስዋትነትም ሆነ ጦርነት የለም!

Post by Ejersa » 10 Dec 2019, 06:14

"በአነስተኛ መስዋእትነትም ቢሆን ኃይል ተጠቅሞ ትግራይን ሉአላዊ አገር ማድረግ የግድ ነው"
ጄ/ል ተክለብርሃን ወ/ኣረጋይ

በአሰማኸኝ አስረስ የተፃፈ

ትናንት ብርጋዴር ጀነራል ተክለብርሃን ወ/ኣረጋይ የኢንሳ ዋና ዳይሬክተር በነበሩበት ዘመን በሰፊዋ ኢትዮጵያ አራጊ ፈጣሪ ሆነው በሕዝቡ እራስ ላይ ፊጥ ብለው የኢትዮጵያን ሕዝብ ንብረት ሲመዘብሩ ኖረው ዛሬ በሰሩት ጥፋት ሳይጠየቁ በስልጣን ላይ በነበሩበት ዘመን ትዝ ከማይላቸው የትግራይ ሕዝብ ጉያ ሽጉጥ ማለታቸው ሳያንስ ዛሬ ደግሞ " በቀላል መስዋእትነትም ቢሆን ኃይል ተጠቅሞ ትግራይን ሉአላዊ አገር ማድረግ የግድ ነው" ብለው ይሳለቃሉ።

እርስዎ እውነትዎትን ነው...ልጆችዎ በአውሮፓና አሜሪካ በቅንጡ ኮሌጆች የሚማሩ ኢትዮጵያ የምትባል አገር የማትገባቸው የውጭ ዜጎች ናቸው። ኢትዮጵያ ውስጥ ጦርነት ቢኖርም በፊልም ተገልብጦ ይሄድላቸውና በሰፊ እስክርን እያዩ ይዝናኑ ይሆናል። እርስዎም ቢሆን ወደ ግንባር ሄደው አያዋጉም። መቀሌ ሆነው ውስኪዎን እየጠጡ ለልጆችዎ ብለው ያስቀረጹትን ፊልም እያዩ ዘና ከማለት በዘለለ ጦርነቱ ከተፋፋመ ደግሞ 'ልጆቼን አይቼ ልምጧ' ብለው ወደ አውሮፓ ላጥ ማለትዎ አይቀርም። መከረኛው የትግራይ ሕዝብ በእሳት ይለበለባል።

ለእርስዎ አነስተኛ መስዋትነት ምን ያህል ነው? 100 ሺ ነው? 200 መቶ ሺ ነው? እርስዎ እና ጓደኞችዎ ህይወታችሁን በሙሉ በሰው ደም ስትነግዱና ስትሽቅጡ መኖር አይሰለቻችሁም? በትግራይ ሕዝብ መስዋትነት ያገኛችሁትን ስልጣን መልሳችሁ ለትግራይ ሕዝብ መጠርጠሪያ ማድረጋችሁ ሳያንስ ዛሬ ደግሞ የጦርነት ከበሮ እየደለቃችሁለት ነው። "በቀላል መስዋትነት አገር እናድርግኃለን" የሚል ፕሮፓጋንዳ ጀምራችኋል። መታወቅ ያለበት ቀላል የሚባል ጦርነት የለም። እርስዎም ከማንም በላይ ያውቁታል። የሚሰጥ ወይም የሚወሰድ መሬትም የለም። ሕዝቡን እርስ በእርስ ስታባሉት ትኖሩ እንደሁ እንጂ...

የትግራይ ሕዝብ በደሙና በአጥንቱ ያቆማት ኢትዮጵያ የምትባል ኩሩ አገር አለችው። የትግራይ ሕዝብ ሌላ አገር የለውም፤ አይፈልግምም። እርስዎ እና መሰሎችዎ ምን ያህል የትግራይን ሕዝብ እንደምትጠሉ የሚያሳየው ሁሌም በትግራይ ሕዝብ ደም የራሳችሁን ጥቅም ለማስከበር መንቀሳቀሳችሁ ነው። ድርጅታችሁ ትህነግ በትግራይ ሕዝብ ላይ በተደጋጋሚ የሚሰራው ሸፍጥ አሁንም ተጠናክሮ ቀጥሏል። ከታሪክ እንደምንረዳው በሀውዜን የደረሰው ዘግናኝ ጭፍጨፋ የተቀናበረው በትህነግ ነበር። በትግራይ ሕዝብ ላይ ያን ያህል መከራ አድርሳችሁ በዚያ አሰቃቂ እልቂት ድርጅታችሁ ትርፍ ያሰላ ነበር። ዛሬም ይኸው ተንኮል ቀጥሏል።

ዛሬም እንደትናንትናው የሞት ትርፍና ኪሳራ ማስላት ጀምራችኋል። በሰው ህይወት የሞት ቁጥር ጨዋታ ጀምራችኃል። ከትናንት የማትማሩ፣ መማር የማትፈልጉ ክፉ ቁሞቀሮች ሆናችኋል። የትግራይ ሕዝብ ከዚህ በኋላ የሚከፍለው መስዋትነት ወይም ጦርነት አይኖርም፤ ካለም አገር ለመበተን ሳይሆን ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ይሆናል።

ጦርነት ሁሉ አውዳሚ ነው። ቀላል መስዋትነትም ሆነ ጦርነት የለም!