Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
YAY
Member
Posts: 943
Joined: 21 Aug 2013, 11:51

Re: ጥያቄ ግዕዝ ቋንቋ ለምታዉቁ

Post by YAY » 15 Dec 2019, 20:43

Dear Naga Tuma: Now, let us see how others have used (what they mean by) the term ህብረብሄር or ኅብረ-ብሔር. What are their similarities and differences?

[6] http://www.assimba.org/Articles/fikare- ... lities.pdf
"በብሔረ ሰብ ላይ የተመሰረቱ ጽንፈኛ አመለካከቶች ኢትዮጵያን እንዳያወድሙብን ዘብ እንቁም"
ከደስታ ቢተው ታኅሕሣሥ 1987 ዓ.ም.


...ከዚህ ጋር የታየ ነገር ደግሞ ብዙ ብሔረሰቦች ኣብረው ይኖሩ በነበሩባቸው ከጠንካራውና ኃይለኛው የተወለዱ የገዥ መደብ ኣባላትም የብሔር ጭቆና ይፈጸምባቸው በነበሩ በርካታ ሀገሮች ውስጥ ኢኮኖሚያዊ፡ ፖለቲካዊ፡ ማኅበራዊ፡ ባህላዊ፡ ተክኖሎጅያዊ ሳይንሳዊ፡ ሥነልቦናዊ ዕድገቶች ብሔረሰቦችን ኣቀራርበውና ኣስተሣሥረው የ ኣንድ ሀገር ዜጎች መሆናቸው እየጎላና ኅብረብሔር የሆነ ሀገር፣ መንግሥት፣ መስተዳድር፣ ሕዝብ እየሆኑ፣ እየቀረጹ መምጣታቸው ነው። ብዕድገት ሂደት ውስጥ ከትንንሽ ጎሣነት፣ ከብሔረሰብነት፣ ከብሔርነት ስሜትና ከክለልተኛ ግንዛቤ በመላቀቅ፣ ይትልቁ ሀገራዊ አሀድ ኣባልነታቸውን ኣጎልብተው ያጎላሉ። ስለሀገር ሕዝብ ያውም ኅብረብሔር በጥቅልሉ ማሰብ፣ መጨነቅ፣ ዕድገትና ልማቱን እየተመኙ ልዚያም ይሠራሉ። ለወገንተኛነት መሥፈርቶቻቸው ከቋንቋ ብሔረሰብ የተለዩ ነገሮች ይሆናሉ። ክጠባብ የብሔርና የጎሣ ኣስተሳሰብ ክልላቸው በማለፍ ኣድማሳቸውን ያሰፋሉ። ስለዚህም ነው የብሔር ብሔረሰብ ጭቆና ታሪካዊና በሁለንተናዊ የኣንድ ሀገርና ሕዝብ ዕድገት ሂደት ውስጥእየተወገደ ተጥሎ ሊታለፍ ይችላል የምለው። ገጽ 5

Naga Tuma wrote:
09 Dec 2019, 04:33
ብሄር የሚለዉ ቃል መሰረቱ ግዕዝ ቋንቋ ነዉ? ከሆነ ትርጉሙ ምንድነው? ህብረብሄር ትርጉም ኣለዉ?

ሌላ ያለኝ ጥያቄ ግዕዝ፣ ኣጋዚ፣ እግዝዮ፣ እና እግዝኣብሄር ይገናኛሉ?
Last edited by YAY on 15 Dec 2019, 22:21, edited 4 times in total.

YAY
Member
Posts: 943
Joined: 21 Aug 2013, 11:51

Re: ጥያቄ ግዕዝ ቋንቋ ለምታዉቁ

Post by YAY » 15 Dec 2019, 20:54

Dear Naga Tuma,

[7] https://www.africanidea.org/Ethiopian_g ... wdewos.pdf
የኢትዮጵያ ጠበቃ እንጂ የአንድ ብሔር አፈቀላጤ አይደለሁም ገላውዴዎስ ኣርኣያ
7/30/2008

በሲምፖዝዮሙ ለመንደርደርያ ያቀረብኩት የመወያያ ርእሰነገር "የጎሳ ፖለቲካና የኢትዮጵያ አንድነት" የሚል ሆኖ ትኵረቱ ግን በተሳሳተ የመንግስት የቋንቋ ክልሎች ፖሊሲ ብቻ ሳይሆን በውጭ ለሚገኙ ኢዮጵያውያን የጎሳ አደረጃጀትም ጭምር ነው። ደግሜ ደጋግሜ እንዳስቀመጥኩት ሁሉ ባሁኑ ግዜ ኢትዮጵያ-አቀፍ (የልዩ ልዩ ብሔሮች አባላት ያሉበት) ድርጅት አለ ማለቱ አዳጋች ሆኖ አግኝቼዋለሁ። ከፍ ብየ እንደጠቀስኩት ኢሕአፓ በኢትዮጵያ ሕዝብ ከፍተኛ ድጋፍ አግኝቶ የነበረው የእውነት ኅብረ-ብሔር ፓርቲ ስለነበረና ከሞላ ጐደል ብሔሮቹን በጠቅላላ አቅፎ ስለነበር ነው። የድርጅቱ አባላት አማራ፡ ትግራይ፡ ኦሮሞ ብቻ ሳይሆኑ ጉራጌ፡ሲዳማ፡ ሃድያ፡ ካምባታ፡ ዶርዜ/ሃይዞ፡ አደሬ፡ ሱማሌ፡ አፋር፡ አገው፡ ሳሆ፡ ሺናሻ ሳይቀሩም ነበሩበት፣ ከዛም አልፎ ተርፎ ኤርትራውያን (ቢን ዓሚሮች ሳይቀሩ) የኢሕአፓ አባላት ሆነው ተሰልፈው ነበር። ስለሆነም ምልአተ ኢትዮጵያን ያስተናገደ ድርጅት እስካልተፈጠረ ድረስ የኢትዮጵያ ትንሳኤ አውን ሊሆን Aይችልም። ምናልባት ለወደፊቱ ወይ ኢሕአፓ/ዴሞክራስያዊ ወይ ደግሞ ልዩ ልዩ የብሔር ድርጅቶች ለኢትዮጵያ ድህንነትና ትንሳኤ ብለው ሃገራዊ ቅንጅት ከፈጠሩ የኢትዮጵያ ብሩህ ዕድል የሚከሰት ይመስለኛል።
p. 4-5
Last edited by YAY on 15 Dec 2019, 21:07, edited 1 time in total.

YAY
Member
Posts: 943
Joined: 21 Aug 2013, 11:51

Re: ጥያቄ ግዕዝ ቋንቋ ለምታዉቁ

Post by YAY » 15 Dec 2019, 21:02

Dear Naga Tuma,
[8] https://tinsaeamara.wordpress.com/author/tinsaeamhara/
ማተቤ መለሰ ተሰማ ጥር ወር 2009 ዓ.ም
እንዲህ የድሉ ጊዜ በራቀ ቁጥር ደግሞ በአማራው ነግድ ላይ በግልጽ የታወጀው የዘር ማጥፋት ዘመቻ ከመቸውም ጊዜ በላይ በረቀቀ ስልት ተጠናክሮ ቀጥሏል። በአኳያው«ባለቤቱ ካልጮኽ፣ ጎረቤት አይረዳም» እንዲሉ ነውና። አማራው እራሱ ተደራጅቶ እየደረሰበት ያለውን በደል ዝቅ ሲል የኢትዮጵያ ከፍሲል የዓለም ህብረተሰብ እንዲያውቀው የማድረግ ስራ መስራት አለበት የሚል እምነት አለኝ። ለዚህም በአማራው ላይ የደረስውንና እየደረሰ ያለውን ሰቆቃ እየተከታተለ መረጃዎችንና ማስርጃዎችን በማሰባሰብ ለሚመለከተው ማቅረብ የሚችል አካል የግድ ያስፈልጋል ማለት ነው።
ይህንን ሃላፊነት እንደተባለው የህብረ ብሄር ድርጅቶች መውሰድ አለባቸው እንዳንል። የሚያስኬድ አይሆንም። ምክናያቱም ህብረብሄር ድርጅቶች የሚያተኮሩት በአጠቃላዩ ወያኔን በማስወገዱ ትግል ላይ እንጅ አንዱን ብሄር ብቻ ነጥለው አማራው ግፍ ተሰርቶበታል፣ ያለሃጢያቱ ተወንጅሏል፣ አማራው ጨቋኝ አልነበረም፣ አይደለም። በማለት ለህዝብ ለማስረዳት። የተለየ መርሃግብር ነድፈው ስለ አማራው ብቻ ሊሰሩ ስለማይችሉ።
በዚህ ከተስማማን «የአገሩን በሬ፣ በአገሩ ገበሬ» ነውና። ይህንን ሃላፊነት በመውሰድ አማራው እራሱ ተደራጅቶ ህብረብሄር ድርጅቶች ሊሰሯቸው የማይችሏቸውንና በቀጥታም ለነጻነት ትግሉ ከፍተኛ ድርሻ ሊኖራቸው የሚችሉትን ከዚህ የሚከተሉትን ስራዎች መስራት አለበት ብየ አስባለሁ።

YAY
Member
Posts: 943
Joined: 21 Aug 2013, 11:51

Re: ጥያቄ ግዕዝ ቋንቋ ለምታዉቁ

Post by YAY » 15 Dec 2019, 21:12

Dear Naga Tuma,

[9] https://etfullgospel.org/index.php/am/2 ... 3-05-40-14
March 23, 2019 | by ethioexploreradmin

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን አቅም ግንባታ ራዕይና የራዕይ ማስፈጸሚያ ስልቶች

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን በ1950ዎች አጋማሽ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በወጣት ተማሪዎች መካከል በተነሳው የመንፈስ ቅዱስ መነቃቃት /revival/ የተጀመረች ስትሆን እስካሁን ድረስ በሁሉም የሀገሪቱ ክልሎች የወንጌል አርበኛና ለምድሪቱ የብርሃን ጮራ በመሆን የእግዚአብሄርን መንግስት እያስፋፋች ያለች ህብረ-ብሄር ናት ፡፡ በአጼ ኃይለ ስላሴና በኮሚኒዝም ዘመን በነበረው እንደ እሳት በሚያቃጥል ስደትና መከራ ውስጥ ትጠፋለች ተብሎ ሲጠበቅ በእግዚአብሄር ፀጋና እርዳታ እየባዛችና እያፈራች እዚህ ደርሳለች፡፡
የ2007 ዓ.ም መረጃ እንደሚያሳየው 2143 አጥቢያ ቤተክርስቲያናትና 7000 ህብረት ቤተክርስቲያናት በ33 ቀጣናዎች በመላው ሀገሪቱ ተደራጅተው ይገኛሉ፡፡ የምእመኗ ብዛት ወደ 4.5 ሚሊዮን ይጠጋል፡፡ በውጭ ሀገርም ወንጌልን ለማዳረስ ባደረገች ውጥረት በጂቡቲ፣ በሶማሊያና በቤይሩት አጥቢያ ቤተክርስቲያናትን ተክላለች፡፡

YAY
Member
Posts: 943
Joined: 21 Aug 2013, 11:51

Re: ጥያቄ ግዕዝ ቋንቋ ለምታዉቁ

Post by YAY » 15 Dec 2019, 21:25

Dear Naga Tuma,

[10] http://www.goolgule.com/eprdf-to-one-pa ... nd-midroc/
ኢህአዴግ ኅብረ ብሔር ፓርቲ ሲሆን ኤፈርትና ሚድሮክ ይዋሃዳሉ? April 1, 2016 06:51 am by Editor

ኢህአዴግን ወደ ኅብረ ብሔር ፓርቲ የማሸጋገር ሥራ እየተሰራ መሆኑንን ሃይለማርያም ደሳለኝ የአገሪቱን “ምሁራን” ባናገሩበት ወቅት ፍንጭ ሠጥተዋል። የዛሬ ሰባት ዓመት ከመስከረም 5 እስከ 7 ቀን 2001 ዓ.ም ሃዋሳ ተካሂዶ በነበረ የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባኤ አቶ መለስ ድርጅታቸው ወደ ብሄራዊ ፓርቲ ወይም አሃዳዊ ፓርቲ ስለመሸጋገሩ እየተጠና መሆኑንን ተናገረው በቀጣዩ ጉባኤ ሪፖርቱ እንደሚቀርብ ቃል ገብተው ነበር። ጥያቄው ዝም ብሎ የቀረበ ሳይሆን ታስቦበትና ከዚህ ቀደም የተሰጠውን መልስ በማስታወስ ነበር። ይህ የሚያሳየው አሃዳዊ ፓርቲ የመሆን ጉዳይ የዛሬ አለመሆኑን ነው። ....
በሌላ በኩል ኢህአዴግን ኅብረ ብሔር ፓርቲ እንዳይሆን በግንባር ቀደምትነት ቅሬታ የሚያሰማው ህወሃት ነው። በጉዳዩ ዙሪያ በቂ መረጃ ያላቸው እንደሚሉት ህወሃት በሃሳቡ የማይስማማው ኤፈርት የተሰኘው የድርጅቱ የንግድ ኢምፓየር ባካበተው ሃብትና ነጻ አውጪው ግንባር ካለው የቆየ ህልሙ በመነሳት እንደሆነ ይነገራል። ኢህአዴግ ኅብረ ብሔር ፓርቲ ከሆነ በቅድሚያ በግንባሩ ውስጥ ያሉት ድርጅቶች ይከስማሉ። ድርጅቶቹ ከከሰሙ ያላቸው ሃብት ይቀላቀላል። የሁሉም ድርጅቶች የንግድ ተቋማት ተዋህደው ከሁሉም ወገኖች የተውጣጡ የቦርድ አባልት እንዲመሩት ይደረጋል። ራሱን የትግራይ ነጻ አውጪ ግምባር ብሎ ለሚጠራው ህወሃት ይህ አካሄድ ትክክለኛ የውኅደት አሠራር ቢሆንም እስካሁን ሊዋጥለት ያልቻለ እውነታ ነው፡፡

YAY
Member
Posts: 943
Joined: 21 Aug 2013, 11:51

Re: ጥያቄ ግዕዝ ቋንቋ ለምታዉቁ

Post by YAY » 15 Dec 2019, 21:32

Dear Naga Tuma: Regardless of how "you" identify yourself, what are they saying?

[11]http://www.ethiolion.com/Pdf/01102017%2 ... %89%BD.pdf

የኢትዮጵያውያን የጋራ ማንነትና የብሄር ማንነት መግለጫ መርሆዎች
Ethiopian Research and Policy Institute Washington, DC. January 2017
ይህችን ዓለም ውብ ያደረጋት ህብረ ብሄራዊ ተፈጥሮዋ ነው።ዓለም ሁሉ አንድ ዓይነት ቢሆን ውበትን አንረዳም ነበር። ህብረ ብሄራዊነት የውበት መለኪያ ብቻ አይደለም። ህብረ ብሄራዊነት የጥንካሬም ዋና መለኪያ ነው። የተለያየ ጥበብ የተለያየ መረዳት ውስብስብ የሆነውን የሰው ልጆች ፍላጎት ለማርካት አማራጮችን ይሰጣል። ኢትዮጵያ ወደ መቶ የተጠጉ ብሄሮችና ነገዶች ያሏት ሃገር መሆኗ የውበትና የጥንካሬ ሃብት የሆነ ትልቅ ሃብት ነው። ይህንን ሃብት በቅጡ መያዝ በጅጉ ይጠይቃል። የኢትዮጵያን የማህበረ ፓለቲካ ጉዞ ስናይ ባለፉት ዘመናት የማንነት አያያዟ ችግር ስለ ነበረበት፤በብሄሮች መሃል ሚዛኑን የጠበቀ የባህል ቅብብሎሽ ባለመኖሩ ብሄሮች በግድ የሆነ ምስለት (forced assimilation) ተፈፀመብን ብለው እንዲነሱ አድርጓል። ይህ የምስለት ዘመን አልፎ ከሃያ አምስት ዓመት በፊት የመጣው የብሄር ፓለቲካና የብሄር ፌደራሊዝም ደግሞ ሃገሪቱን ወደ ልዩነት (separation) አምጥቷታል። የኢትዮጵያን ማህበረ ፓለቲካ ጠቅለል አድርገን ካየነው ጉዞው ከምስለት ወደ ልዩነት ((from assimilation to separation) ነው። ኢትዮጵያ በነዚህ በሁለቱም የማህበረ ፓለቲካ ጉዞ አልተደሰተችም። ህብረብሄራዊ ተፈጥሮዋን ውበትና ጥንካሬዋን ተንከባክቦ የሚይዝ ሲስተም ያስፈልጋል። በመሆኑም በኢትዮጵያ ፓለቲካ ውስጥ የመጫወቻ ምሰሶ የሆኑትን የብሄር ማንነትና የብሄራዊ ማንነት ጉዳይ በተገቢው መንገድ እንዲገለፁ ሲስተም መዘርጋት ያስፈልጋል። በመሆኑም የኢትዮጵያ ብሄሮች ከፍ ሲል በዘረዘር ናቸው መንገድ ራሳቸውን እንዲገልፁ ማድረግ መፍትሄ ነው።
Last edited by YAY on 25 Dec 2019, 02:45, edited 1 time in total.

YAY
Member
Posts: 943
Joined: 21 Aug 2013, 11:51

Re: ጥያቄ ግዕዝ ቋንቋ ለምታዉቁ

Post by YAY » 15 Dec 2019, 21:50

Dear Naga Tuma: Do "you" think the Ge'ez/Ge'iz terms would help us Horn of Africans?

[12]https://ethioexplorer.com/%E1%8A%A8%E1% ... n-the-opd/
ከኦህዴድ ሆድቃ የተገኘ ጥቁር ሰንዱቅ!!! Black Box in the OPDO’s Belly ሚሊዮን ዘአማኑኤል
March 23, 2019 | by ethioexploreradmin

አዲስ አበባ ፣መቐለ፣ ባህር ዳር፣ ሃዋሳ፣ አዳማ፣ ድሬዳዋ፣ ባህር ዳር፣ ጎንደር፣ህብረ ብሄር ከተሞች ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ የከተማው ህዝብ ብዛት ከመቶ 20 እጅ ነው፣ የገጠሩ ህዝብ ብዛት ደግሞ 80 በመቶ ነው፡፡
....
• አማራ ህዝብ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ 48.3 በመቶ፣ ድሬ ዳዋ ከተማ ውስጥ 27.7 በመቶና በሃራሪ ከተማ 32.6 በመቶ ከነዋሪዎቹ ድርሻ አለው፡፡
• ኦሮሞ ህዝብ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ 19.2 በመቶ፣ ድሬ ዳዋ ከተማ ውስጥ 48.0 በመቶና በሃራሪ ከተማ 52.3 በመቶ ከነዋሪዎቹ ድርሻ አለው፡፡
• ጉራጌ ህዝብ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ 17.5 በመቶ፣ ድሬ ዳዋ ከተማ ውስጥ 4.5 በመቶና በሃራሪ ከተማ 3.2 በመቶ ከነዋሪዎቹ ድርሻ አለው፡፡
• ትግራይ ህዝብ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ 7.6 በመቶ፣ ድሬ ዳዋ ከተማ ውስጥ 1.8 በመቶና በሃራሪ ከተማ 1.7 በመቶ ከነዋሪዎቹ ድርሻ አለው፡፡
• ሱማሌ ህዝብ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ 0.2 በመቶ፣ ድሬ ዳዋ ከተማ ውስጥ 13.9 በመቶና በሃራሪ ከተማ 1.7 በመቶ ከነዋሪዎቹ ድርሻ አለው፡፡
• ወላይታ ህዝብ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ 0.5 በመቶ፣ ድሬ ዳዋ ከተማ ውስጥ 0.2 በመቶና በሃራሪ ከተማ 0.1 በመቶ ከነዋሪዎቹ ድርሻ አለው፡፡
• ጋሞ ህዝብ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ 0.9 በመቶ፣ ድሬ ዳዋ ከተማ ውስጥ 0.0 በመቶና በሃራሪ ከተማ 0.0 በመቶ ከነዋሪዎቹ ድርሻ አለው፡፡
• ሃዲያ ህዝብ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ 0.4 በመቶ፣ ድሬ ዳዋ ከተማ ውስጥ 0.5 በመቶና በሃራሪ ከተማ 0.0 በመቶ ከነዋሪዎቹ ድርሻ አለው፡፡
• ሌሎች ኢትዩጵያዊ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ 3.0 በመቶ፣ ድሬ ዳዋ ከተማ ውስጥ 2.2 በመቶና በሃራሪ ከተማ 8.2 በመቶ ከነዋሪዎቹ ድርሻ አላቸው፡፡
• የውጭ ዜጎች በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ 2.0 በመቶ፣ ድሬ ዳዋ ከተማ ውስጥ 0.9 በመቶና በሃራሪ ከተማ 0.1 በመቶ ከነዋሪዎቹ ድርሻ አለው፡፡
....
{3} በሃዋሳ ከተማ በደቡብ ክልላዊ መንግስት ውስጥ የሲዳማ፣ የወላይታ፣ የጉራጌ ወዘተ የክልላዊ መንግሥት ጥያቄ የህዝቡን አብሮ የመኖር ህልውና ዘለቄታዊ ጥቅም በምን መልኩ ያስተናግዳል ሃዋሳ ከተማ ህብረ ብሄራዊ ዜጎች ህልውና ቀጣይነት ምን ይሆናል መልስ ያሻዋል፡፡
{4} በአዳማ ከተማ የህዝቡን አብሮ የመኖር ህልውና ዘለቄታዊ ጥቅም በምን መልኩ ያስተናግዳል አዳማ ከተማ ህብረ ብሄራዊ ዜጎች ህልውና ቀጣይነት ምን ይሆናል መልስ ያሻዋል፡፡
{5} በባህር ዳር ከተማ የህዝቡን አብሮ የመኖር ህልውና ዘለቄታዊ ጥቅም በምን መልኩ ያስተናግዳል የባህር ዳር ከተማ ህብረ ብሄራዊ ዜጎች ህልውና ቀጣይነት ምን ይሆናል መልስ ያሻዋል፡፡
{6} በአጠቃላይ ከመቶ ሽህ ህዝብ በላይ ያላቸው ህብረ ብሄራዊ ዜጎች የሚኖሩባቸው የከተሞች እጣ ፈንታ በኢትዮጵያ እንዴት ይቀጥላል፡- የአዲስ አበባ፣ ጎንደር ፣ መቀሌ ፣ ጂማ ፣ ጂግጂጋ ፣ ሻሸመኔ፣ ሶዶ፣ ብሸፍቱ፣ አርባ ምንጭ፣ ሶዶ፣ ሆሳዕና፣ ሀረር፣ ዲላ፣ ነቀምት፣ ደብረ ብርሃን፣ ደብረ ማርቆስ፣ አሰላ፣ ወዘተ የመሳሰሉ ከተሞች፣ የኢትዮጵያዊያን ዜጎች በምርጫ ራሳቸውን በእራሳቸው የማስተዳደር መብት አላቸው እንላለን፡:

YAY
Member
Posts: 943
Joined: 21 Aug 2013, 11:51

Re: ጥያቄ ግዕዝ ቋንቋ ለምታዉቁ

Post by YAY » 15 Dec 2019, 21:57

Dear Naga Tuma: Remember that I am an Eritrean, but read carefully what the Professor is saying

[13]https://www.addisadmassnews.com/index.p ... Itemid=214
“የኦፌኮ” ሊቀ መንበር ፕ/ር መረራ ጉዲና 17 August 2019:
ዋናው የኢትዮጵያ የፖለቲካ ችግር፣ የድርጅት ቅርጽ አይደለም፡፡ እኔ የነበርኩበት መኢሶንና ኢህአፓ በርዕዮተ አለማቸው፣ በድርጅታዊ ቅርጻቸው ህብረ ብሄር ነበሩ፡፡ በእርግጥ ከዚያ በኋላ የተመሰረቱ፣ ህብረ ብሄር ነን የሚሉ የፖለቲካ ድርጅቶችን፣ ህብረ ብሄራዊ ናቸው ለማለት ይቸግረኛል። ትንሽ ፋቅ ሲደረጉ ወይ የአማራን ወይ የኦሮሞን፤ ሲጠብም የአንድ አካባቢ ተወላጆች ስብስብ ሆነው ልናገኛቸው እንችላለን፡፡ ይሄ ደግሞ ዘንድ በሁሉም ዘንድ የቅርፅና የአደረጃጀት ችግር መኖሩን ያሳያል። ስለዚህ በተለይ ሕዝቡ፤ የተሻለ የፖለቲካ አቋምና ሃሳብ ማን ነው የሚያራምደው? ማን የተሻለ ፖሊሲ አለው? ማን በአንድነት ይመሩኛል የሚለው ላይ ማተኮር ይበጀዋል፡፡ ከዚህ ባለፈ ያለውን ለኢትዮጵያ ህዝብ መተው ይሻላል፡፡
ህብረ ብሔርም ይሁኑ የብሔር ድርጅቶች“አንድ ሀገር ነው ያለን” በሚለው ጉዳይ ላይ መግባባት ላይ መድረስ አለባቸው፡፡ ዋናው የምርጫ መለኪያ መሆን ያለበት፤ ማን በዲሞክራሲያዊ መንገድ ይመራል ወይም እየመራ ነው የሚለው ነው:: ህብረ ብሔሮችም ያሸንፉ፣ በብሔር የተዋቀሩ ፓርቲዎች፤ ዋናው ጉዳይ መሆን ያለበት፤ አንድ የጋራ ሀገር የመኖር ጉዳይ ነው፡፡ የ “አብን” ሀገር፣ የ “ኦነግ” ሀገር፣ የ “ህወኃት” አገር፣ የ “ኦፌኮ” ሀገር… የሚባል ነገር የለም፡፡ “አንድ ሀገር ነው ያለን” በሚለው ላይ ትክክለኛ ድርድር ያስፈልጋል ያልኩት ከዚህ አንፃር ነው፡፡ ይሄን ካላደረግን ግን አሁንም ባለፉት 50 ዓመታት በሄድንበት መንገድ ነው የምንሄደው:: የብሔር ፖለቲካም ሆነ የዜግነት ፖለቲካ የሚያራምዱ ሃይሎች፤ ከሰማይ የወረዱ አይደሉም:: ከዚሁ ማህበረሰብ የወጡ ናቸው፡፡ ነገሩ በዚህ ልክ ነው መታየት ያለበት፡፡
የብሔር እንቅስቃሴ አራማጆችን ለማፈን ጥረት ማድረግ በራሱ ሀገሪቷን ውድ ዋጋ ሊያስከፍላት ይችላል፡፡ የብሔር ንቅናቄዎችን፣ በሚቀጥሉት አስር ዓመታት ውስጥ እንኳ ጡረታ ማስወጣት የሚቻል አይመስለኝም፡፡ ስለዚህ በሀገር አንድነትና በመቻቻል ፖለቲካ ተደራድሮ፣ በቃል ኪዳን መተሳሰር ይሻላል:: መሀል መንገድ ላይ መገናኘት የግድ ነው፡፡
በሁለቱ የፖለቲካ ሃይሎች መካከል ጥርጣሬ የነገሰ ይመስላል እርግጥ ነው ፖለቲካ ሁሌም ከስጋት የተነጠለ አይደለም፡፡ ነገር ግን ብሔርተኞች ያሠጋሉ የሚሉ ሃይሎች፤ ከብሔርተኛ ሃይሎች የተሻለ ስራ ሰርተውና ህዝቡን አሳምነው መገኘት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ብሔርተኛ ድርጅቶችም ራሣቸውን ከኢትዮጵያ ነጥለው የትም እንደማይደርሱ ማወቅ አለባቸው:: “አብን” አማራን ገንጥሎ የትም አይደርስም፡፡ “ህወሓት” ትግራይን ገንጥሎ የትም አይደርስም:: “ኦነግ”ም ኦሮሞን ገንጥሎ የትም አይደርስም:: ስለዚህ የተሻለ የፖለቲካ ስርአትና የነገይቷን ኢትዮጵያ እንዴት አብሮ መፍጠር ይቻላል በሚሉ ጉዳዮች ላይ የበለጠ ጊዜን ማጥፋት የተሻለ ነው፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ ግን “አብን” ወይም “ኦነግ”ን ብንከስ፣ የኢትዮጵያን ችግር አንፈታም፡፡ እርስ በርስ መካሰሱ የትም አያደርሰንም፡፡ እነዚህን የብሔር ድርጅቶች “እኛ የተሻልን ኢትዮጵያውያን ነን” ማለቱ እምብዛም አይጠቅመንም፡፡ ይልቁንስ በኢትዮጵያ ህዝብ መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ መነጋገሩ ነው የሚሻለው፡፡ ምርጫው ይራዘም ማለትም የትም አያደርስም፡፡ ከዲሞክራሲ መሸሽ ዞሮ ዞሮ፣ አደጋ ነው፡፡

YAY
Member
Posts: 943
Joined: 21 Aug 2013, 11:51

Re: ጥያቄ ግዕዝ ቋንቋ ለምታዉቁ

Post by YAY » 15 Dec 2019, 22:10

Dear Naga Tuma: It was excellent that "you" asked, but ህብረ ብሔር or ህብረ ብሄር is not that simple. I hope it helps "you" formulate "your" ideas? Comments are welcome.

[14] https://addisstandard.com/wp-content/up ... ogram-.pdf
V. የኢህአዴግ እህት ድርጅቶችአጋር ድርጅቶች ሀገርን ባስተዲደርንበት ባለፉት ዓመታት በአመዛኙ ተመሳሳይ የፖለቲካ ዓላማ፣ፕሮግራም እና መሰረታዊ አቅጣጫ ይህን በመሆኑ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል እና ስህተቶችን በማረም ወደ ሚቀጥለው የትግል ምዕራፍ ለመሸጋገር አስቻይ አቅም አለን። በመሆኑም ይህ የጋራ ትግል ታሪክና የአላማ አንድነት ህብረ ብሄራዊ ውህድ ፓርቲ ለሆነው ብልጽግና ፓርቲ ስኬታማነት ከፍተኛ አስተዋጾ አለው። እንደድርጅት በወሳኝ ሀገራዊ ፖለቲካዊ አጀንዳዎች ዙሪያ ግንባር በመፍጠር ቢያንስ ላለፈት ሶስት አስርት አመታት ታግለናል። የመንግስት ስልጣን በመጨበጥ የጋራ የፖለቲካ ፕሮግራሞቻችንን ተግብረን ተጨባጭ ሀገራዊ እድገትን ማስመዝገብ ችለናል። የምናካሂደው ውህደት እያንዳንዱ የእህት ድርጅት የነበረውን የአላማና የተግባር ውህደት በአዲስ መንፈስ ይበልጥ በማጠናከር የተሻለ ኃይል እንድናሰባስብ በማድረግ በቀጣይ ለላቀ የአላማ አንድነትና ሀገራዊ ድል የሚያበቃ መልካም አጋጣሚን የሚፈጥር ይሆናል።
[p.4]

Naga Tuma
Member+
Posts: 5543
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ጥያቄ ግዕዝ ቋንቋ ለምታዉቁ

Post by Naga Tuma » 16 Dec 2019, 23:29

Abe Abraham wrote:
13 Dec 2019, 16:48
... Birhan that the Arabs borrowed from us. That is how Arabic is related to our languages. [/b][/color]
Abe Abraham,

Speaking of Birhan, you might want to know the following two words in Borana lanaguage (Afan Oromo): በሪ and በሪኤ. The first one means dawn and the second one means dawned. I imagine the Amharic word በራ has the same origin as በሪኤ. I am guessing the equivalent word sounds the same in Tigrigna and Ge'ez. If you go further and look at the origin of the English word bright, it makes you wonder more. Here are its variations in various languages: beorht (Old English,) bjartr (Old Norse,) bairhts (Gothic,) beraht (Old High German,) bjerk (Norwegian,) brokig (Swedish.) You may also wonder if other languages might also have had their own challenges of using their own Qubes in order to write a single word with the same meaning.

DefendTheTruth,

I remember watching a while back a YouTube video clip wherein Dr. Gemechu Megersa was asked a challenging question about an outlook of the Borana people. He appeared caught off guard about the question and gave a short response, which I think is correct. If I remember correctly, his short response was ነመ ጄዹ or something to that effect. Just the other day, I was listening to another YouTube video clip where an Afan Oromo speaking young man said ነመ፣ ሌንጨ፣ and so on (I don't remember all those that he listed.) Did the differentiation that you are reading and understand today exist when the ancient people started to say ነመ፣ በሪ፣ በሪኤ, and so on? That is a question that everybody should ask himself or herself and get a satisfying answer. If you can scientifically say humanity is one kind in a set, you can always conveniently get subsets based on the language they speak or the geographic area they occupy. Convenience is what leads to grammatically incorrect statements like this: "There are the Oromo people, there are the Amhara people, the Guraghe people and these are peoples of Ethiopia and can be called together part of the Ethiopian People."

YAY,

I have just gotten back to this thread. So, pardon me for my belated responses.

Thank you for providing various references that are new to me. I have been calling for a Borana-Ge'ez dictionary. I read the meanings of the Ge'ez words delightfully. They reinforce my call for that kind of dictionary. In a way, it takes us to the earliest days of spoken language. As I read through the words, I was imagining the landscape where those words were used. In Horus' response to you, it seems to me that the word ሃገር itself is related to ጋር, which appears to me a variation of ጋረ in Borana language. When you say ጉዞ, I ask if ጎዳና is also a Ge'ez word. If it is, then I jump to the word ጎዳኔ, which literally explains the meanings of many of the words you listed. When you provide a meaning for ኣሕባራ, I wonder if the word ኣቧራ is related to it and then I jump to ኣዋረ. ኣቧራ and ኣዋረ mean the same thing. We can talk about early human migration without the need for DNA study. Language study may be equally rich.

Now, going back to my question, I don't think I am confused about the term ህብረብሄር or ህብረ ብሄር. I understand you when you say: "I find it confusing more now, when different people seem to mean different things by the same term." As I wrote early on in this thread, ብሄር፣ ሃገር፣ እና የሃገር ድንበር ኣይነጣጠሉም። If you take the U.S. as an example, it has a defined geographic boundary and all of its citizens make a nation, not a multi-nation. I also have enough of a reading when it comes to the activism and venture to define Ethiopia as multi-nation, which is directly translated into ህብረብሄር or ህብረ ብሄር. When you have a country, you have a nation, not a multi-nation. That much is clear to me.

Horus,

I am reading that you are suggesting that the words ሃገር and ጋራ may be related. Did I misunderstand you?
Last edited by Naga Tuma on 17 Dec 2019, 01:09, edited 1 time in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 30911
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ጥያቄ ግዕዝ ቋንቋ ለምታዉቁ

Post by Horus » 16 Dec 2019, 23:58

Naga Tuma,

አው የአገር ስረ ቃሉ ገር ነው። የጋራ፣ የህብረት ማለትም የተያያዘ ነው። ጋራ ተራራ ማለቴ አይደለም ። አሁን ቀረ እንጂ ድሮ ፈጠጋር/ፈጠገር ይባል ነበር ለምሳሌ የዛሬው የረርና ከሰም ዙሪያ የነረው አገር። ቃሉ የሚመጣው ደር (ምድር፣ ቦታ) ከሚለው የሴም ስር ነው። ልክ መንደር፣ ጎንደር እንደ ሚባለው ። ኬር

Naga Tuma
Member+
Posts: 5543
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ጥያቄ ግዕዝ ቋንቋ ለምታዉቁ

Post by Naga Tuma » 17 Dec 2019, 00:06

YAY wrote:
15 Dec 2019, 22:10
It was excellent that "you" asked, but ህብረ ብሔር or ህብረ ብሄር is not that simple. I hope it helps "you" formulate "your" ideas?

YAY,

I really don't think that it is that complicated. We all need to be reminded of the source of the compound word ህብረብሄር or ኅብረ ብሄር. Those who intentionally used it and advanced its use envisioned separated smaller countries. They envisioned ብሄር in those separated smaller countries, not ህብረብሄር or ኅብረ ብሄር. Even as they advocated Ethiopia as a ህብረብሄር or ኅብረ ብሐር in order to undo it as a country, they strongly advocated those left in each of those separated smaller entities as a strong ብሄር. Now, do you understand the source of the confusion about having it both ways?

If there is a consensus for having a country instead of separated smaller countries, then we have a ብሄር in that country. People who advocate for a country are probably equating ህብረ ቋንቋ to ህብረ ብሄር. Perhaps, the more accurate term may be ህብረ ቋንቋ ብሄር, or multi-language nation.

Naga Tuma
Member+
Posts: 5543
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ጥያቄ ግዕዝ ቋንቋ ለምታዉቁ

Post by Naga Tuma » 17 Dec 2019, 00:18

Horus,

ገር ጋር ጋራ ጋረ ደር ዳር ዳርቻ ዳሪ፤ እነዚህን ቃላት እያየሁ እና እያስታወስኩ ትርጉሞቹ ተምታቱብኝ። ነጋን፣ ኬር

Horus
Senior Member+
Posts: 30911
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ጥያቄ ግዕዝ ቋንቋ ለምታዉቁ

Post by Horus » 17 Dec 2019, 02:02

ናጋ ቱማ፣
ዳሪ ምንድን ነው? የቀሩት ሁሉም አንድ ስር ይዘው ተዛማጅ ሜታፎር እየሰሩ ጥቅም ላይ የዋሉ ቃላት ናቸው።

ገር ፣ አገር
ጋራ ፣ ህብረት፣ ባንድ አገር የሚኖሩ ሰዎች
ጋረ ያው ጋር ማለት ነው። ምናልባት ድሮ ጋረ ማለት አበረ ብለው ይሆናል
(ግን የኦሮሞ ጋሪ፣ ጋሩማ አገር ሳይሆን ኬር ማለትም ደህና፣ ጤና፣ ዌልነስ ጋር ነው ሚያያዝ።)
ዳር፣ (ድንበር) ያው ከመሬት፣ ካገር ጋር ያለ ጽንስ ነው
ዳር እና ዳርቻ አንድ ነገር ነው

ዳሪ የኦሮሞ ቃል ከሆነ ነገረኝ ። ኬር !!

Rtt
Member
Posts: 192
Joined: 31 Jan 2019, 15:33

Re: ጥያቄ ግዕዝ ቋንቋ ለምታዉቁ

Post by Rtt » 17 Dec 2019, 14:59

EthioRedSea wrote:
13 Dec 2019, 18:56
Rtt,
The information you have brought is made by Amhara intelectuals and is false as this does not explain the similarity between Tigrigna and Armaic. We believ Armaic is the origin for all semitic languages. Geez, Amharic, Tigrigna and Guraghe languages are semitic. Tigrigna and Guraghe speakers are related to Middle Eastern people. Most Amhara do also. This is genetically proven and our culure (Semitc Ethiopian ) is ralted with Asians.We are asians and blacks- a mixture.
Most family names of Pakistan, Afgahnistan and Bangladesh are related to Tigrigna and Geez. So do most Arabic and yemen names. We should not be ashamed of our semitic roots.
How can you say its false without reading it?

That "Amahra" intellectual is a person who studied Amahraic and Ethio - semetic languges for decades.

Judge the book by its content and not by the ethincty of the Author! He has done his research and is breaking all the Myth regarding the "semetic" People and languages of Ethiopia. Their are also plenty Genetic researchs that are doing the same.

What does Bangladesh and Pakistan has to do with semetic? They are Muslims indo Aryan.

Ethoash
Senior Member+
Posts: 26144
Joined: 20 Apr 2013, 20:24

Re: ጥያቄ ግዕዝ ቋንቋ ለምታዉቁ

Post by Ethoash » 17 Dec 2019, 16:14

Rtt,

EthioRedSea

ገገማ ነው ምንም ብትለው የሚገባው ሰው አይደለም። እሱና አንድ አለ ደግሞ ምንም አይስሙህም ። ይልቁኑስ ሁለቴ መልስ ህላቸው ካልገባቸው ጥለሀቸው ብቻ ነው መሄድ ያለብህ። እነዚህ እኮ የታወቁ የኢራ ገገሞች ስራፍቶች ናቸው። አንድ ኤርትራዊ ነበር ኢትዬዽያ በቅኝ ተገዝታለች ብሎ እኛንም ወደ እነሱ ተርታ ሊከተን።። በጣሊያን ተይዛ ነበር ግን አሽንፈን ከኢትዬዽያ አስውጣናቸው ብትለው ምን ብትለው በፍፁም አይገባውም ታድያ እነዚህ ሁለት ከአንድ ውሃ ይቀዳሉ ልብህን አታውልቀው

Naga Tuma
Member+
Posts: 5543
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ጥያቄ ግዕዝ ቋንቋ ለምታዉቁ

Post by Naga Tuma » 18 Dec 2019, 03:05

Horus,

ካልተሳሳትኩ ዳሪ እና ዳርቻ ትርጉማቸዉ ኣንድ ነው።

Rtt
Member
Posts: 192
Joined: 31 Jan 2019, 15:33

Re: ጥያቄ ግዕዝ ቋንቋ ለምታዉቁ

Post by Rtt » 18 Dec 2019, 14:47

Ethoash wrote:
17 Dec 2019, 16:14
Rtt,

EthioRedSea

ገገማ ነው ምንም ብትለው የሚገባው ሰው አይደለም። እሱና አንድ አለ ደግሞ ምንም አይስሙህም ። ይልቁኑስ ሁለቴ መልስ ህላቸው ካልገባቸው ጥለሀቸው ብቻ ነው መሄድ ያለብህ። እነዚህ እኮ የታወቁ የኢራ ገገሞች ስራፍቶች ናቸው። አንድ ኤርትራዊ ነበር ኢትዬዽያ በቅኝ ተገዝታለች ብሎ እኛንም ወደ እነሱ ተርታ ሊከተን።። በጣሊያን ተይዛ ነበር ግን አሽንፈን ከኢትዬዽያ አስውጣናቸው ብትለው ምን ብትለው በፍፁም አይገባውም ታድያ እነዚህ ሁለት ከአንድ ውሃ ይቀዳሉ ልብህን አታውልቀው
Ethioash,

It's not about what a random person says, it's about providing proofs and facts. If you have a problem with what me and the other person you talked about, debate us with actual proof and facts!

Naga Tuma
Member+
Posts: 5543
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ጥያቄ ግዕዝ ቋንቋ ለምታዉቁ

Post by Naga Tuma » 21 Dec 2019, 01:12

One more word that probably has a long history: ጋለ (Borana/Afan Oromo,) ግመል (Amharic, Tigrigna(?)) and camel (English.)

Also in other languages: camelus (Latin, Old English, Middle English,) kamelos (Greek,) gamal (Hebrew.)

Horus
Senior Member+
Posts: 30911
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ጥያቄ ግዕዝ ቋንቋ ለምታዉቁ

Post by Horus » 21 Dec 2019, 02:04

Naga Tuma

ትክክል ። ይሀውልህ ለምሳሌ እስፔስ በአማርኛ ጠፈር ይባል ነበር ። ትክክል ነው፣ በኔ ግምት ጠፈር ማለት ዳር፣ ጫፍ፣ ኤጅ ማለት ነው። ይህም የእስፔስ ጽንስ ነው። የድሮ ሰዎች ጎበዝ ነበሩ ። አሁን ሀዋ ይባላል። ግ ን ሀዋ ባዶ ቦታ ወይም ቫኪዩም ማለት ነው እንጂ እስፔስ ወይም ጠፈር ማለት አይደለም ። ጠፈር ባዶ አይደለም፣ በፕላኔቶች፣ ኮከቦች፣ ሌላ አካላት የተሞላ እጹብ ድንቅ ቦታ ወይም ቤት ወይም እስፔት፣ እስፔስ ነው !!! ናጋ !

Post Reply