Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30849
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ጠ/ሚ አቢይ የኖቤል ጥያቄን ፊት ለፊት መመልስ ይሻለዋል !!

Post by Horus » 09 Dec 2019, 02:44

እኔ ቃል መፍለጥ አልወድም ።

አቢይ የኖቤል ኮሚቴም ሆነ የልጆቹን ጥያቄ ፊት ለፊት አለም ምንም መሽኮርመም ቢመልስ ለራሱ በጣም ይጠቅመዋል !

አለም ሁሉ የኢትዮጵያ ቀውስና ችግር ምን እንደ ሆነ ያቃል ።

አለም ሁሉ ያቢይ ጥንካሬ ምን እንደ ሆነ ያቃል ።

አለም ሁሉ ያቢይ ድክመት ምን እንደ ሆነ ያቃል ።

አቢይ በራሱ አፍ ድክመቱና ስህተቱ ቢናገር ያለም ሁሉ ድጋፍ ያሰጠዋል ።

ለምን ቢሉ አለም ሁሉ እውነተኛ፣ ደፋር፣ በራሱ የሚተማመን ግን ስህተት የሚሰራን ሰው እንደ ጀግና ስለምያይ ማለት ነው ።

ድክመቱን የማይፈራ ጀግና ነውና! ስህተቱን የማይደብቅ ሃቀኛ ታማኝ ነውና !!

አቢይ እውነተኛ ከሆነ የኢትዮጵያን ሕዝብ ማመን አለበት !

ሕዝቡ አቢይን የሚወደው ድክመቱን ሁሉ እያወቁ እንጂ እግዚአብሄር ነው ብሎ አይደለም !!

በተቃራኒው ስህተቱን ፣ ድክመቱን የሚደብቅ በመሪነት ሳይሆን በፈሪነት የሚታይ የኔ ብጤ ስለሆነ ማለት ነው !!
Last edited by Horus on 09 Dec 2019, 03:02, edited 1 time in total.

Revelations
Senior Member+
Posts: 33713
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: ጠ/ሚ አቢይ የኖቤል ጥያቄን ፊት ለፊት መመልስ ይሻለዋል !!

Post by Revelations » 09 Dec 2019, 03:00

As you can see in this video, he already gave the interview in Addis on the side of the road, at night and without being asked, where he can be shy! :lol: :lol: :lol:
Please wait, video is loading...

Horus
Senior Member+
Posts: 30849
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ጠ/ሚ አቢይ የኖቤል ጥያቄን ፊት ለፊት መመልስ ይሻለዋል !!

Post by Horus » 09 Dec 2019, 03:13

ረቨላቲኦን፣

እኔ ይህ ገጠመኝ ምን እንደ ሆነ አላቅም ። አቢይ የፖለቲካ ተጫዋች ነው ። ጠላቶቹ የኢትዮጵያ ሕዝብ አይደሉም ፣ የራሱ የጎሳ ስልጣን ተሻሚዎች ናቸው ። እሱ እኒህን የውስጥ ባላንጣዎቹን የሚሻገረው የማይፈራ፣ ግልጽ፣ በራሱ ሚያምን፣ በህዝቡ ሚያምን መሪ ሲሆን እንጂ በዚህ ዘመን ከሚዲያና ከልጆች ጥያቄ በመሸሽ አይደለም ።

እኔ ኒኮሎ ማኪያቬሊ አይደለሁም ። አቢይም ሆነ ያቢይ መካሪዎችም ይህን ገጽ ያንብቡ አያንብቡ አላቅም ።

ግን የምለው ነገር በሳይንስም፣ በሳይኮሎጂም የተረጋገጠ ነው ።

Dawi
Member
Posts: 4311
Joined: 30 Aug 2016, 03:47

Re: ጠ/ሚ አቢይ የኖቤል ጥያቄን ፊት ለፊት መመልስ ይሻለዋል !!

Post by Dawi » 09 Dec 2019, 04:02

Horus,

አቢይ የኖቤል ኮሚቴውን ጉዳይ ቅድሚያ የሚሰጥበት ምክንያት አይታየኝም፤

እኔ እንደሚመስለኝ "መሸረፈት" ጃ-ቄሮን አሁን መጋፈጥ አይፈልግም፣ ስለሱም አሁን ማውራት አይፈልግም፣ የለማም ሰልፍ በደንብ አልተረጋገጠም፣ ሌሎች እንደባላደራስ ያሉት ጉሮሮውን ይነቁት፣ ለማም ቦታውን ይያዝ፣ አብዛኛው አማርኛ የማይናገረው ቄሮ ዕውነቱን በራሱ ሰዐት አውቆ ጽንፈኛውን ጃ-ቄሮን አንቅሮ ይተፋዋል ብየ አምናለሁ፣

"ድክመቱን የሚደብቅ በመሪነት ሳይሆን በፈሪነት የሚታይ" ብዙ ሰው ብሎታል፣ እኔ አይመስለኝም፣ አቅሙን ያውቃል ባይ ነኝ።
Horus wrote:
09 Dec 2019, 02:44
እኔ ቃል መፍለጥ አልወድም ።

አቢይ የኖቤል ኮሚቴም ሆነ የልጆቹን ጥያቄ ፊት ለፊት አለም ምንም መሽኮርመም ቢመልስ ለራሱ በጣም ይጠቅመዋል !

አለም ሁሉ የኢትዮጵያ ቀውስና ችግር ምን እንደ ሆነ ያቃል ።

አለም ሁሉ ያቢይ ጥንካሬ ምን እንደ ሆነ ያቃል ።

አለም ሁሉ ያቢይ ድክመት ምን እንደ ሆነ ያቃል ።

አቢይ በራሱ አፍ ድክመቱና ስህተቱ ቢናገር ያለም ሁሉ ድጋፍ ያሰጠዋል ።

ለምን ቢሉ አለም ሁሉ እውነተኛ፣ ደፋር፣ በራሱ የሚተማመን ግን ስህተት የሚሰራን ሰው እንደ ጀግና ስለምያይ ማለት ነው ።

ድክመቱን የማይፈራ ጀግና ነውና! ስህተቱን የማይደብቅ ሃቀኛ ታማኝ ነውና !!

አቢይ እውነተኛ ከሆነ የኢትዮጵያን ሕዝብ ማመን አለበት !

ሕዝቡ አቢይን የሚወደው ድክመቱን ሁሉ እያወቁ እንጂ እግዚአብሄር ነው ብሎ አይደለም !!

በተቃራኒው ስህተቱን ፣ ድክመቱን የሚደብቅ በመሪነት ሳይሆን በፈሪነት የሚታይ የኔ ብጤ ስለሆነ ማለት ነው !!

Horus
Senior Member+
Posts: 30849
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ጠ/ሚ አቢይ የኖቤል ጥያቄን ፊት ለፊት መመልስ ይሻለዋል !!

Post by Horus » 09 Dec 2019, 04:06

Dawi,

ጃዋር፣ ቄሮ፣ ዎያኔ፣ ኦነግ፣ ወይም ሌላ አቢይን የማይወድ ቡድን መኖሩ ሁሉም ያቃል።

በነዚህ ቡድኖች ላይ አቢይ እንደ ፈለገ አለባብሶ መመልስ ይችላል ፣ ፖለቲካኛ ስለሆነ ።

ግን ደስ የማይሉኝ ወይም አወዛጋቢ ጥያቄዎችን ስለምፈራ አለመልስም ማለት ፍጹም ድክመት ነው።

በጥያቄው ግዜ መመልስ የማይችላቸው ነገሮች ካሉ ይህን አሁን መመልስ አልችልም ወዘተ ይላል እንጂ ጥያቄና መልስ አልካፈልም ማለት ፍጹም ፈሪነት ነው ፣ ከሱ የሚጠበቅ አይደለምና ባያረገው እጅግ ይሻላል ።

Post Reply