Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sholagebya
Member
Posts: 494
Joined: 27 Oct 2014, 15:59

ሰው ዕድሜ ልኩን የፓለቲካ ስህተት እንደሰራ ይቀራል ?

Post by sholagebya » 03 Dec 2019, 08:33

ሰው ዕድሜ ልኩን የፓለቲካ ስህተት እንደሰራ ይቀራል ? አዛውንት ሲሆን ችኮላውን ቀነስ አድርጎ ቢታገስ ምን አለበት ? ኢሕአፓ ን ክዶ ከወያኔ ጋር ታግሎ ወያኔን ለሥልጣን አብቅቶ እነሱ እንደ አሮጌ ቁና ወረውረው ሲጥሉት የበረከት ስምኦን አምላኪ ሆነ :: አሁን ደግሞ “ የ ብልጽግና ፓርቲ ፈራሚዎች በአማረኛ አልፈረሙም ስማቸውም ሁሉም ሙስሊሞች ናቸው ...” ብሎ ያላዝናል :: ከዚህ በላይ ሰው ከቶ ሊወርድ ይችል ይሆን ? የሚሰድበው ሰው ስለበዛበት የፌስቡክ ገጹን አስተያየት መስጫ disable አድርጎታል እንጂ እስከ ዶቃ ማሰሪያው ይነገረው ነበር :: ከሁሉ የሚገርመው ነገር የሕዝብ ስብሰባ ያዘጋጀው ወገን እሱን የሚጋብዘው ምን ብለው ነው ? ለዚህ ነው ዴያስፓራው ስብሰባ የማይሔደው :: አንዱ የድሮ ጓድ “ ወጥቸ አልወጣሁም “ የሚለውን ቆንጆ ርዕስ ያለው መጽሐፉን ግዛኝ ቢለው , “የመጽሐፉ ርዕስ ቆንጆ ቢሆንም የማውቀውን የተበላሸ ታሪህን ስለማውቀው እንደገና ማንበብ አልፈልግም ብሎታል :: አቶ ያሬድ ጥበቡ የትናንት የተበላሸውን የባንዳ ታሪኩን ዛሬም በእርጅና ዘመኑ ለማስተካከል የማይፈልግ አሳዛኝ ፍጡር ነው :: ትኩረት ካልነፈግነው በስተቀር የበለጠ ይጨማለቃልና ኢግኖር እንግጨው እስኪ ?