Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Hameddibewoyane
Member
Posts: 3890
Joined: 25 Sep 2019, 02:42

የህወሓትና ፅንፈኛ ኦነጎች ለቅሶ "በብልፅግና" ፓርቲ ላይ!!!!

Post by Hameddibewoyane » 03 Dec 2019, 03:22

ለብሔር ብሔረሰቦች መብት ጥብቅና ቆመናል የሚሉት ህወሓትና የኦሮሞ ፅንፈኞች "በኢህአዴግ መቃብር ላይ" የተመሰረተውን ብልፅግና ፓርቲ አምርረው እየተቃወሙ ነው።

ህወሓትና ኦነግ የደርግ መንግስትን መውደቅ ተከትሎ የኢትዮጵያን ፖለቲካ ያለተቀናቃኝ መቆጣጠራቸው ይታወሳል። ሆኖም የበላይ ለመሆን በነበራቸው ሽኩቻ ምክኒያት ደም ተቃብተው ፉክክሩ በህወሓት አሸናፊነት ተደመደመ። እናም ኦነግን ከጨዋታ ውጭ ያደረገው ህወሓት የራሱን የበላይነት የሚያስጠብቅበት ስርዓት በመመስረት ብሔርብሔረሰቦችን "እህት እና አጋር" በሚባሉ ከረጢቶች አጭቆ ወደ ከፍተኛው የስልጣን እርከን ድርሽ እንዳይሉ ቀይ መስመር አስምሮ ለ27 አመታት ያሻውን ሲያደርግ ኖሯል። እሱም በተራው በህዝብ ትግል ተገፍቶ ጥጉን ይዟል።

ይሁንና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እነዚህ በብሔርብሔረሰብ ጨዋታ የተሸነፉ ሁለት ኃይሎች በአብይ አስተዳደር ላይ ግንባር ፈጥረው ማሴር ጀምረዋል። በህወሓት ይዘወር በነበረው ኢህአዴግ ውስጥ ከአጋር ድርጅቶች ውስጥ ጠቅላይ ሚኒስትር መሆን አይቻልም ነበር፤ ዛሬ ግን እነሙስጠፋ ዑመርን የመሳሰሉ ሰዎች ኢትዮጵያን በጠቅላይ ሚኒስትርነት የመምራት ዕድሉ አላቸው። ስለዚህ ህወሓት ለብሔረሰቦች እኩልነት የሚያስብ ከሆነ የአጋር ድርጅቶች ወደ እኩልነት መምጣት ለምን ያበሳጨዋል?

የኦሮሞ ፅንፈኞች ደግሞ የህወሓትን ወደ መቐለ መሸሽ ተከትሎ ራሳቸውን በህወሓት ቦታ በማስቀመጥ ብሔርብሔረሰቦችን ረግጠው ለመግዛት ቋምጠው ነበር። በዚህም ምክኒያት ህወሓት የዘረጋው ስርዓት እንዳይነካብን ሲሉ ይጮሃሉ። ዛሬ ሁሉንም ብሔረሰቦች እኩል የሚያሳትፍ ፓርቲ ሲመሰረት ለቅሶ ተቀምጠዋል።

ስለዚህ ህወሓትም ሆነ የኦሮሞ ፅንፈኞች ፍላጎት ሌሎች ብሔሮችን ረግጦ የመግዛት እኩይ አላማ መሆኑ ግልፅ ሆኗል። እንግዲህ እነዚህ ኃይሎች ማወቅ ያለባቸው ወሳኝ ጉዳይ ከእንግዲህ በአንድ ብሔር የበላይነት የምትመራ ኢትዮጵያ አትኖርም። እነዚህ ኃይሎች ተመልሰው ወደ ስልጣን ከመጡ የኢትዮጵያ ህዝብ ሞቷል ማለት ነው።