Page 1 of 1

የኦሮሞ ፖለቲካ ሽኩቻ አለ በተባሉ መንገዶች ሁሉ እራሱን እየገለጠ ወይም manifest እያደረገ ነዉ!!

Posted: 02 Dec 2019, 11:51
by Maxi
የኦሮሞ ፖለቲካ ሽኩቻ አለ በተባሉ መንገዶች ሁሉ እራሱን እየገለጠ ወይም manifest እያደረገ ነዉ፡፡ በሚስት የትዉልድ ቦታ ሳይቀር ቡድን ተይዟል፡፡ ለማንኛዉም አሰላለፉ ከሞላ ጎደል እንዲህ ነዉ

- ዶ/ር አብይን የትዉልድ አካባቢያቸዉ ማለትም ጅማን እና ባብዛኛዉ የሽዋ አካባቢ ፖለቲከኞች እና ህዝብ ይደግፋቸዋል (ከኦሮሞ ዉጭ ያለዉ እንዳለ ሁኖ)

- ለማ መገርሳ- ወለጋን እና አካባቢዉን ይዘዋል፡፡ በነገራችን ላይ ወለጋ ላይ ያለዉ ችግር የዚሁ ፖለቲካ አንድ አካል ነዉ፡፡ ደጋፊህን መከላከያ ልከህ ወንጀለኛን በመያዝ አታበሳጭም፡፡

- ጃዋር ሞሀመድን- ከፊል አሩሲ እና ሀረርጌ አካባቢዉን ያንቀሳቅሳል፡፡

ይህ ከላይ ያየነዉ ክፍፍል እንግዲህ አብዛኛዉ አካባቢን (ዞንን) መሰረት ያደረገ እና የዘር ሀረግን በተለየም በኦሮሞ ጎሳዊ ስትራክቸር የተቃኘ ነዉ፡፡

የኦሮሞ ፖለቲካ ክፍፍልም ሃይማኖታዊ ይዘት አለዉ፡፡

- ሀረር፤ ከፊል አርሲን እና ባሌን የያዘዉ ጃዋር ባብዛኛዉ በሙስሊሙ ወገን የሚደገፍ ሲሆን

- ወለጋን እና አካባቢዉን የያዘዉ ለማ በፕሮቴስታንት ክርስቲያኑ የሚደገፍ ነዉ

- የኦርቶዶክስ ክርስቲያን ተከታይ የሆነዉ አብዛኛዉ ሽዋ የአብይ ቡድንን ሲደግፍ እንዲሁም በሃይማኖትም ሆነ በጎሳዊ እሳቤ ሞደሬት የሚባለዉ አካባቢ በሙሉ ጅማን ጨምሮ አብይን ይደግፋል፡፡

ሌላዉ ክፍፍል የፓወር ነዉ

አብይ ስልጣኑን እያጠናከረ መሄዱ ለጃዋርም ሆነ ለለማ የማይቀበሉት ነገር ሁኖባቸዋል፡፡ አብይ የኖቤል ሽልማት እንዳሸነፈ እና ስሙ በሚዲያዎች ሲገን ለዚህ ያበቃሁት እኔ ነኝ አይነት እሳቤ በመያዙ እና በመቅናቱ አብይ በዛን ሰሞን ባገኘዉ አቴንሽን ልክ ጃዋርም ማግኘት ነበረበት፡፡ ጃዋር አቴንሽን ለማግኘት የሞከረበት አካሄድ ጭራሽኑ የራሱን የፖለቲካ ህይወትም ችግር ዉስጥ የከተተበት አጋጣሚ ነዉ፡፡ ከ 86 በላይ ዜጎች እንዲገደሉ ቀጥተኛ ምክንያት ሆኗል፡፡ ይሄም እሱ ባሰበዉ መልኩ ሰፊ ድጋፍ ማግኘት አይደለም እንዲያዉም የኦሮሞ ፖለቲካን ሰንጥቅ በማስፋት እንዲሁም ህብረተሰቡ እርስ በርሱ እንዲጋጭ እና እንዲተላለቅ አድርጓል፡፡ ይሄም በሰባዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች እንዲሁም የኢትዮጵያን ፖለቲካ በሚከታተሉ ግለሰቦች እና ድርጅቶች አይነ ቁራኛ ዉስጥ ጥሎታል፡፡

ኦቦ ለማ የዚህ ለዉጥ ጠንሳሽ እና ባለቤት እኔ ነኝ ብሎ ያስባል፡፡ የሀገሪቱ የመከላከያ ሚኒስቴር ከመሆን በላይ ሌላ ስልጣን እና ተሰሚነት የለም፡፡ ነገር ግን የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ሆኖም ተሰሚነቴ ቀነስ ይላል፡፡ ይህ የመጣዉ አብይ ብልጽግና ፓርቲን በይፋ ወደ መመስረቱ ስለሄደ ይሄም አብይን ሌላ ተጨማሪ ፓወር ስለሚሰጠዉ ለማ የራሱ የወደፊቱ እንዳለዉም ተሰሚነቱ ሙሉ ለሙሉ ይጠፋል ብሎ ስላሰበ ተቃዉሞ ወጥቷል፡፡ ለማ የፈለገዉ የነበር ሀገር በአንድ እግሯ እንድትቆም ነዉ፡፡ ነገር ግን ለማም ያሰበዉን ያህል ድጋፍ ሞቢላይዝ ማድረግ አልቻለም፡፡ ለማ በቪኦኤ የተቃዉሞ ሃሳቡን ማሰማቱ ሀገሪቱ በሙሉ በእርሱ ዙሪያ የምትሰለፍ መስላዉ ነበር፡፡ አሁንም የኦሮሞ ፖለቲካን ሰንጥቅ ከማስፋት የዘለለ ምንም ፋይዳ የለዉም፡፡ ለማ መገርሳ ከአብይ ገር ከመታረቅ የዘለለ ሌላ አማራጭ የለዉም፡፡ ሰዉየዉ ስልጣን የሚዎድ እና አድራጊ ፈጣሪ ነኝ ብሎ የሚያስብ ሰዉ በመሆኑ ትቂት ተለምኖ እዛዉ ተመልሶ አብይ ጋር ይቀጥላል፡፡ ምክንያቱም ጥሎ መሄድ ለለማ የሚያጎናጽፈዉ ምንም አይነት ፓወር የለም፡፡

አብይ በዚህ የፖለቲካ ሽኩቻ ዉስጥ ኦሮሚያ ላይ ሊያጣ የሚችለዉን ድምጽ ከኦሮሚያ ዉጭ ያሉ አካባቢዎችን እንደ ማካካሻ በመያዝ ለመንቀሳቀስ እየሞከረ ነዉ፡፡ ለምሳሌ ሶማሌ፤ አፋር፤ ጋምቤላ እና የመሳሰሉት ከኦሮሚያ አካባቢ በከፊል የሚያጣዉን ድጋፍ ያጣጣለታል፡፡ የመጨረሻ ዉጤቱ ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት ቢከብድም ለጊዜዉ በኦሮሞ ፖለቲካ ዉስጥ አሸንፎ ሊወጣ የሚችለዉ የአብይ ቡድን ይመስላል፡፡

ነገር ግን የአብይ ቡድንም ቢሆን ደካማ እና በቀላሉ ሊሸነፍ የሚችል ነዉ፡፡ ኦርጋናይዝድ የሆነ አይደለም፡፡ አሁን ላይ የአብይ በኦሮሞ ፖለቲከኞች ላይ እያሳየ ያለዉ ጉልበት የመጣዉ ከአማራ ፖለቲከኞች (ከብአዴን) ባለዉ ድጋፍ ነዉ፡፡ ጠቅለል ስናደርገዉ ለስታሊን ሌኒን (ቀድሞት ሳይሞት) ነበረዉ፤ ለመንግቱ እነ ለገሰ አስፋዉ ነበሩት፤ ለመለስ በረከት ነበረዉ፤ ለአብይ ይሄ ነዉ የሚባል ስትራቴጅካል ሰዉ የለዉም፡፡ ስለዚህም ይህ ቡድን መሰረቱ የጸና ስለማይሆን በቀላሉ የመናወጥ እድሉ ሰፊ ነዉ፡፡ ቀሪዉን አብረን የምናየዉ ይሆናል፡፡

Re: የኦሮሞ ፖለቲካ ሽኩቻ አለ በተባሉ መንገዶች ሁሉ እራሱን እየገለጠ ወይም manifest እያደረገ ነዉ!!

Posted: 02 Dec 2019, 12:15
by Dani_Wako
Maxi,

very accurate observation. I have a friend in Adama who is related to one of ODPs central committee member. The way he put the current situation is just like you described it above. His conclusion is that Abiy is gaining ground in every zones of Oromia, and now the majority of ODPs are siding with Abiy. That is how he got the landslide majority vote for the medemer and party merger. Also, the fact that the international community like AU, EU and US is behind Abiy, gave him the muscle he needed. Lema is total marginalized or sidelined and spends his day to day life dealing with routing ministerial duties.

Re: የኦሮሞ ፖለቲካ ሽኩቻ አለ በተባሉ መንገዶች ሁሉ እራሱን እየገለጠ ወይም manifest እያደረገ ነዉ!!

Posted: 02 Dec 2019, 12:30
by Masud
Maxi,
You tried to create some kind of confusion , you failed. You better know the reality. The reality is that Dr. Lemma Megersa and Obbo Jawar Mohammad have huge support across Oromia regardless of age, sex, or religion.

Yes, Abiy is constituency-less and homeless who is seeking asylum from Amhara.

Re: የኦሮሞ ፖለቲካ ሽኩቻ አለ በተባሉ መንገዶች ሁሉ እራሱን እየገለጠ ወይም manifest እያደረገ ነዉ!!

Posted: 02 Dec 2019, 13:29
by Dani_Wako
Masud,
you are telling us about your day dreams. We are discussing about the reality on the ground. Please, let's not mix stories. This is the kind of emotion based mistakes that is lowering the credibility of discussions on this blog.

a Friend.