Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Maxi
Member+
Posts: 5951
Joined: 06 Mar 2014, 04:33

ወያኔ በለማ መገርሳን ላይ እርምጃ በመውሰድ አብይ አህመድ ለማ መገርሳን ገደለው ብላ ልታለቃቅስ እንደምትችል መረጃ ወጣ!!

Post by Maxi » 02 Dec 2019, 11:32

ወያኔ በለማ መገርሳን ላይ እርምጃ በመውሰድ አብይ አህመድ ለማ መገርሳን ገደለው ብላ ልታለቃቅስ እንደምትችል መረጃ ወጣ!! :P :P :P
Nahusenay Belay
November 29 at 8:10 PM ·

ለማ መገርሳ ሆይ! የቀድሞ ወዳጅህ ናሁሰናይ ከመቐለ ይህን ባለ 6 ነጥብ መልእክት ልኮልሃል፦

1. ጠባቂዎችህን ሙሉ በሙሉ ከአብይ ንኪኪ እና ትእዛዝ አፅዳ፡፡ የጥበቃ ጥንካሬው ሶስት እጥፍ ጨምር፡፡ በተለይ በሜ/ጄነራል ሓሰን ኢብራሂም የተመደቡልህን ጠባቂዎች በጠቅላላው አባርር፡፡

2. ቁልፍ የፁሁፍ፥ የድምፅ፥ የምስልና እና የቪድዮ መረጃዎችን አባዝተህ በተለያዩ ቦታዎች አስቀምጥ፡፡ ይህ የሂወት ዋስትናህን ከፍ ያደርገዋል፡፡

3. በፍጥነት መናገር ያለብህን እውነት አፍረጥርጦ መናገር፡፡ እንደ ኦሮሞ ህዝብ መሪነትህ፤ የኦሮሞ ህዝብ ብሄራዊ ጥቅሞች ላይ የተጋረጠውን አደጋ በግልፅ ጠቅሶ መጋፈጥ፡፡ የኦሮሞ ህዝብ እውነት የማወቅ መብቱ መከበር አለበት፡፡

4. በዋናነት ኮነሬል አብይ የኦሮሞን ህዝብ መሪ አልባ አድርጎ፥ ሃይሉን በትኖ፥ አዳክሞ፥ እንደ ኮነሬል መንግስቱ ሃ/ማርያም ፈላጭ ቆራጭ ለመሆን ፈልጎ ድርጅቱን እንዳፈረሰ በግልፅ ለህዝቡ መናገር ( ለማ ይህንን ሃሳብ ለአንድ የጀርመን ዲፕሎማት ተናግረሀው ነበር፡፡ ጀርመኑ ከህዝብህ አይበልጥም)

5. የኦሮሞ ህዝብ ያስረከበህን ብሄራዊ ድርጅት አስበልተህ ንሰሃ ገብተህ አርፎ ለመቀመጥ አይመስለኝም ልዩነትህን በይፋ ያወጀከው፡፡ ከሁሉም በፊት ግን የኦሮሞ ህዝብ ላይ ለተደረገው ሸፈጥ፥ ማጭበርበር፥ ክህደት ይቅርታ ጠይቅ፡፡ከዛ በሃላ በፍጥነት ቀጣይ የትግል አቅጣጫውን ይፋ አድርገህ ወደ ብሄራዊ ትግል መግባት አለብህ፡፡ መካስ አለብህ፡፡ መሮጥ አለብህ፤ ግዜ የለም፡፡

6. በመጨረሻም ኮነሬል አብይ ምን ሊያደርግ እንደሚችል ከማንም በላይ አንተ ታውቃለህና፥ ቀበሮ ሆነህ ወጥመዶቹን እለፋቸው፡፡ ለማስፈራርያም ለመደራደርያም የሚሆኑ የአብይ ወንጀሎች ቁጥር ስፍር እንደሌላቸው አውቀህ በፍጥነት ከመከላከል ወደ ማጥቃት ተሸጋገር፡፡ ያኔ ትግልህ ትርጉም ይኖረዋል፡፡

ይቅናህ!