Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abaymado
Member
Posts: 4206
Joined: 27 Sep 2017, 21:56

በኢትዮጵያ ውስጥ አንድ ስታድዮም ብቻ በካፍ እውቅና አገኘ!!

Post by Abaymado » 29 Nov 2019, 12:53


ሁሉም ስታድየሞች ከደረጃ በታች መሆናቸውን ካፍ በማሳወቁ : ኢትዮጵያ ማንኛውንም ኢንተርናሽናል ጫዋታ ማስተናገድ አትችልም የሚል እንድምታ ነበረው:: ለባህርዳር እና ለመቀሌው ስታድየም እስከ ህዳር ድረስ ብቻ እንዲያጫውቱ ፍቃድ አግኝኝተው ነበር:: እስከዚያው ግን ስታድየሞቹ የሚጠበቅባቸውን ካላሟሉ: ጫዋታ ማስተናገድ እንደማይችሉ ነው የተነገረው:: አሁን ግን የመቀሌ ስታድዮም መብቱ ተገፎ ለባህርዳር ተሰቶታል::

ኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የባህርዳርና የመቀሌ ስታድየም ደረጃውን አለጠበቀም ሲባሉ ተረብሸው ነበር:: እናም የወልዲያ ስታድየም ደረጃው ይጣራልኝ ብለው አመልክተው ነበር : ካፍ ስታድየሙን ካጠና በኃላ: ደረጃውን እንደጠበቀ ዛሬ ተገልፆል:: ይህ አንድ እፎይታ ነው:::

ግን አሁንም መታሰብ ያለበት: አዲሱ የአዲስ አበባ ስታዲየም (አደይ አበባ ): ሁሉንም እንዲያሟላ ተደርጎ መሰራት አለበት::
መቀመጫው ድንጋይ ሳይሆን ወንበር መግባት አለበት:: የጥላ ፎቅ ሊሰራለት ይገባል:: በተጨማሪ የሜዳው ሳር ደረጃውን የጠበቀ አርተፊሻል ሳር ቢገባለት አሪፍ ነው:: ለዚህ ደሞ ከየትም ተብሎ ገንዘቡ መመደብ አለበት:: ይህ ካልሆነ የአገርዋን ስም የሚያጎድፍ ነው::


(መረጃ: amara mass media agency)