Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abdelaziz
Senior Member
Posts: 11365
Joined: 29 May 2013, 22:00

warning to Meshrefet

Post by Abdelaziz » 20 Nov 2019, 19:46

ጥንቃቄ፣ ጥንቃቄ፣ ጥንቃቄ
=================
Tsegaye Regassa Ararssa 11-20-19

አሁን ጉዳዩ ግልፅ እየሆነ ነው። ጠቅላይ ሚኒሥትሩ፣ የአባል ድርጅቶቻቸውን ሕገ-ደንብ፣ የምርጫ ሕጉን የውህደት ጉዳይ ድንጋጌ፣ የአባሎቻቸውንና የአጋር ድርጅቶች አባላትን ፍላጎት ሁሉ እየተጋፋ፣ በጉልበት (እና በሚዲያ ላይ በሚደረግ ቅጥፈት)፣ በውህደት ሥም የራሳቸውን አዲስ ድርጅት (ብልፅግና ፓርቲ) እያቋቋሙ ይገኛሉ። ግልፅ፣ ነገር ግን ከባድ፣ ምርጫ ከፊታችን ተደቅኗል። አንፃራዊ ሕጋዊነት ባለው ሂደት ወደ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ማዝገም፣ ወይም በውህደት ሥም መንግሥት አፍርሰን በመንገደኛ አምባገነን በሕገወጥ መንገድ መገዛት። ይሄን የሚያስብል ምክንያት አለ። የሚከተለው ነው፦
1. በምርጫ ሕጉ መሠረት፣ ፓርቲዎች ተዋሃዱ የሚባለው፣ ድርጅቶቹ የጋራ ፕሮግራም ይዘው፣ ሕገ-ደንብ አዘጋጅተው፣ የስምምነታቸውን ዝርዝር ጽሁፍ አቅርበው፣ የእያንዳንዱ አባል ድርጅት አባላት በተዋረድ ባሉ ኦርጋኖቻቸውና በጠቅላላ ጉባኤ ለመክሰም መስማማታቸውን የሚያሳይ ቃለ-ጉባኤ አያይዘው፣ ሌሎች የምርጫ ሕግ ድንጋጌዎችንና መመሪያዎችን አሟልተው ነው። ይህ አልተደረገም።
ኅወኃት ውህደቱን አልተቀበለም። አንድ አባል ድርጅት ካልተቀበለው ውህደቱ አልተሳካም ማለት ነው። አባል ድርጅቱን ገፍቶ፣ ሌሎችን (በተለምዶ አጋር ድርጅቶች የተባሉትን) ጨምሮ መደራጀት ደግሞ፣ አዲስ ድርጅት መፍጠር እንጂ መዋሃድ አይደለም።
ኦህዴድ በማዕከላዊ ኮሚቴ አልተቀበለውም። ይሄ ሳይሆን በቆረጣ ወደ ኢሕአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ወስደውታል። ይሄም ሕገወጥ ነው።
የየትኛውም አባል ድርጅት አባላት፣ በጉባኤ የመክሰምና የመዋሃዱን ሃሳብ በይፋ አልተቀበሉትም። ስብሰባም አልተጠራም። ውይይትም አልተካሄደም። ውሳኔም አልተወሰነም።
እስካሁን፣ ለውይይት የቀረበና የጸደቀ የውህዱ ፓርቲ ፕሮግራም የለም። ('ረቂቅ አለ' ተብሎ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጠቅሶ ነበር። እስካሁን ግን በጽሁፍ የቀረበ ምንም ነገር የለም።) በዚህ ሁኔታ፣ 'ለመቀበልም ላለመቀበልም ያስቸግረናል፣ አባሎቻችንን እና ሕዝባችንን ማወያየት አለብን፣ ወዘተ' የሚለው የኅወኃት ጥያቄም ቸል ተብሏል።
ረቂቅ የብልፅግና ፓርቲ ሕገ-ደንብ በማሕበራዊ ድረ-ገጽ ተሰራጭቷል። በዚህ ሕገ-ደንብ ላይ፣ ብዙ የሕገ-መንግሥትና የሕግ ጥያቄ የሚያስነሱ ጉዳዮች ቢኖሩም፣ በነዚህም ላይ ውይይት ተካሂዶ ስምምነት ላይ አልተደረሰም።
(በዚህ ሁኔታ ተዋሕዶአል ተብሎ የሚነገርለት ፓርቲ፣ ውሁድ ፓርቲ ሳይሆን አዲስ ፓርቲ ነው።)
2. በአባል ድርጅቶቹ ሕገ-ደንቦች መሠረት፣ የመክሰም ውሳኔውን የሚያጸድቁት፣ በጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ የሚደረገው፣ መክሰምና መዋሃድ፣ የእያንዳንዱን አባል በነፃ የመደራጀት መብትን ከማክበር ባሻገር፣ የፖለቲካ ራዕዩን፣ ለወደፊት በግሉ መከተል የሚፈልገውን የፖለቲካ ሕይወት፣ ህልሙንና መሻቱን፣ ለድርጅቱ ያበረከተውን መዋጮ፣ መስዋዕትነት፣ ንብረት፣ ወዘተ የሚመለከት በመሆኑ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሁን እያደረጉ እንዳሉት፣ ጠቅላላ ጉባኤን መሰብሰብ ሳያስፈልግ፣ በማዕከላዊ ኮሚቴና በሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ውሳኔ ብቻ "ውህደት ተፈፅሟል" ብሎ በየሚዲያው መግለፅ ማለት፡
ሀ) ሕገወጥ ነው።
ለ) ውሸት ነው።



ሐ) ሕዝብንና አባላቱን ማጭበርበር፣ የአገሪቱን ሕዝብም ማታለል ነው።
--------
3. ከሁሉም በላይ አደገኛው ነገር፣ የኢህአዴግ ከምርጫ በፊት መዋሃድና የአባል ድርጅቶቹ መክሰም (ውህደቱ እና መክሰሙ በተገቢው የሕግና የሕገ-ደንብ አግባብ ተፈፅሞ የሆነ ቢሆን እንኳን)፣ ውጤቱ፣ አሁን ያለውን መንግሥት ማፍረስና የሥልጣን ክፍተት (power vacuum) መፍጠሩ ነው። ምክንያቱም፣ የሚፈጠረው አዲስ ፓርቲ--ውሁድም ሆነ አዲስ--በሕዝብ ተመርጦ መንግሥት የማቃቋም ማንዴት ከተሰጠው ኢሕአዴግ ፈፅሞ የተለየ ነው።
ከምርጫ በፊት ኢሕአዴግን አፍርሶ በብልፅግና ፓርቲ መተካት፣ መንግሥትን ማፍረስ ነው።

ያለው መንግሥትና የኢሕአዴግ አደረጃጀት ለውጡን ለመምራት አልቻለም፣ አልተመቸም ከተባለ፣ መደረግ ያለበት ፓርላማውን በማፍረስ ወደ ምርጫ መግባት ነው እንጂ፣ ብልፅግና ፓርቲ በሚባል ሕገወጥ ቡድን "ለማስተዳደር" መሞከር፣ አምባገነንነት ወይም የመንገደኛ ጉልበተኛ መንግሥት መሆን ነው። ይሄ በቀላሉ ሊታይ አይገባውም።
------
በመሆኑም፦
1. የአባል ድርጅቶቹ አባላት፣ በአስቸኳይ ተሰብስበው የመክሰማቸውን ሁኔታ፣ የውህደቱን ሥርዓትና ውጤት በማጤንና በመምከር፣ የጠቅላይ ሚኒሥትሩን ሕገ-ወጥ አካሄድ መገምገም አለባቸው።
2. ኢ-ሕገመንግሥታዊ አካሄድ በማድረግ መንግሥቱንና ፓርላማውን የማፍረስ፣ ብሎም የሥልጣን ክፍተት ፈጥሮ አገርንና ሕዝብን እስካሁን ከነበረው በላይ ለአደጋ የሚያጋልጥ እርምጃ እየተወሰደ ስለሆነ፣ መከላከያ ሠራዊቱ፣ የሕግና የሕገ-መንግሥት ተቋማት ሁሉ፣ በጥንቃቄ ሁኔታዎችን እያጤኑ ለሚመጣው ቀውስ ሊዘጋጁ ይገባል።
------
በሚመለከታቸው ወገኖች ሁሉ፣ በጊዜ የእርምት እርምጃ ካልተወሰደ በቀር፣ በቀላሉ ወደማንወጣው አዘቅት እንደምንገባ በመገንዘብ፣ አስፈላጊውን የጥንቃቄ እርምጃ ሁሉ መውሰድ ይበጃል።
Source:


This is exactly identical to what weyane had been telling the illiterate Meshrefer.

Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4080
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

Re: warning to Meshrefet

Post by Za-Ilmaknun » 20 Nov 2019, 20:11

Advice to TPLF treasury ...Don't waste your precious none replenish-able resources on peoples such as Ararsa and Jawissa. They are more liabilities than assets.

Halafi Mengedi
Senior Member+
Posts: 45809
Joined: 30 May 2010, 23:04

Re: warning to Meshrefet

Post by Halafi Mengedi » 20 Nov 2019, 20:20

Za-Ilmaknun wrote:
20 Nov 2019, 20:11
Advice to TPLF treasury ...Don't waste your precious none replenish-able resources on peoples such as Ararsa and Jawissa. They are more liabilities than assets.
Anything is liability for Amhara, it is great an asset for Tigray ledger???

Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4080
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

Re: warning to Meshrefet

Post by Za-Ilmaknun » 22 Nov 2019, 12:51

Halafi Mengedi wrote:
20 Nov 2019, 20:20
Za-Ilmaknun wrote:
20 Nov 2019, 20:11
Advice to TPLF treasury ...Don't waste your precious none replenish-able resources on peoples such as Ararsa and Jawissa. They are more liabilities than assets.
Anything is liability for Amhara, it is great an asset for Tigray ledger???
I am not sure you understood what I was trying to say. Keep on hating and see it it moves the needle an inch. Your party is now irrelevant. Start to stand on your own and leave the rest of us. :mrgreen:

Post Reply