Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Dani_Wako
Member
Posts: 127
Joined: 09 Aug 2018, 15:16

የኢህአዴግ ውህደት በዋልታ ረገጥ እሳቤዎች ለተወጠረችው ኢትዮጵያ ወደ መካከል እንድትመጣ አማራጭ ይሆናል- ም/ጠ/ሚ አቶ ደመቀ

Post by Dani_Wako » 20 Nov 2019, 11:57

አዲስ አበባ ፣ህዳር 9፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ውህደት በዋልታ ረገጥ እሳቤዎች ለተወጠረችው ኢትዮጵያ ወደ መካከል እንድትመጣ አማራጭ እንደሚሆን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ተናግረዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው ዕለት የኢህአዴግን ውህደት አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም ኢህአዴግ እንደ ድርጅት በከፍተኛ የመዋቅር ችግር ውስጥ መቆየቱን አስታውሰዋል።

ይህም ኢትዮጵያን በብሄርና በሀገራዊ ማንነት በሚሉ ሁለት ዋልታ ረገጥ እሳቤዎች እንድትወጠር ማድረጉን ነው ያብራሩት።

ውህድ ፓርቲው ሀገራዊ አንድነትንና ብዝሃነትን እንዲሁም የግልና የቡድን መብቶችን ባከበረ መልኩ ለኢትዮጵያ ብልጽግና ይሰራል ብለዋል።

ህብረ ብሄራዊ ፌዴራሊዝም፣ አሳታፊነት፣ በዜጎች ለውጥ የሚለካ እድገት የውህደቱ ማጠንጠኛ ተጨማሪ ሃሳብ መሆናቸውንም አስታውቀዋል።

የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ለሶስት ቀናት ባካሄደው ስብሰባ በድርጅቱ ውህደት፣ በአዲሱ ፓርቲ ፕሮግራምና በህገ ደንብ ዙሪያ መወያየቱ ይታወቃል።

በውይይቱም ስራ አስፈጻሚው በሶስቱም አጀንዳዎች ላይ የሚያግባባና የሚያቀራርብ ሃሳብ ማንጸባረቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ መግለጻቸው ይታወሳል።

ምንጭ ፦ኢዜአ

Dani_Wako
Member
Posts: 127
Joined: 09 Aug 2018, 15:16

Re: የኢህአዴግ ውህደት በዋልታ ረገጥ እሳቤዎች ለተወጠረችው ኢትዮጵያ ወደ መካከል እንድትመጣ አማራጭ ይሆናል- ም/ጠ/ሚ አቶ ደመቀ

Post by Dani_Wako » 20 Nov 2019, 12:02

Demeke Mekonnen - the Real hero! Chased TPLF from Arat Killo (by withdrawing his candidacy for PM position at the 11th hour); and now, behind the curtain: envisioned, formulated, and drafted a Party to which no sane Ethiopian will say NO to. By doing so, buried TPLF for good. Viva!!!!!

Post Reply