Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Maxi
Member+
Posts: 5951
Joined: 06 Mar 2014, 04:33

በ2 ወራት ብቻ ከ1 ቢልዮን ብር በላይ አክስዮን የሰበሰው የአማራ ባንክ በአስገራሚ ግስጋሴ ላይ ነው!!

Post by Maxi » 20 Nov 2019, 08:25

በ2 ወራት ብቻ ከ1 ቢልዮን ብር በላይ አክስዮን የሰበሰው የአማራ ባንክ በአስገራሚ ግስጋሴ ላይ ነው!!


Getachew Shiferaw

በከፍተኛ ግስጋሴ ላይ የሚገኘው ባንክ! አማራ ባንክ!

~የተፈቀደ ካፒታል ብር 2,000,000,000.00 (ሁለት ቢሊየን ብር)፤

~ የአክስዮን ሽያጭ የተጀመረው ነሃሴ 11 ቀን 2011 ዓ.ም፤

~እስካሁን የተፈረመ (subscribed) አክስዮን፦ ከብር 1,085,000,000.00 (አንድ ቢሊየን ሰማኒያ አምስት ሚሊየን ብር) በላይ፤

~ እስካሁን በጥሬ ገንዘብ የተከፈለ ካፒታል (paid up) አክስዮን፦ ከብር 843,000,000.00 (ስምንት መቶ አርባ ሦስት ሚሊየን ብር) በላይ፤

~ አክስዮኑ አሁንም በሽያጭ ላይ ይገኛል፣ ህዳር 30 ቀን ሽያጩ የሚዘጋበት ቀን ይሆናል።

~ ሽያጩ በይፋ እስከሚዘጋበት ቀን ድረስ አክስዮን ለሚገዙ ባለአክስዮኖች፣ የመስራችነት መብት የተጠበቀ ነው፤ ከዚህ በፊት አክስዮን የገዙ ባለአክስዮኖች ድጋሜ መግዛት ይችላሉ።

~ ትውልደ ኢትዮጵያውያን የውጭ ሀገር ዜጎች አክስዮን መግዛት የሚችሉት በውጭ ምንዛሬ ብቻ ነው።

~ ትውልደ ኢትዮጵያውያን የውጭ ሀገር ዜጎች በትዕግስት እንድትጠብቁ ተጠይቃችኋል፣ የብሄራዊ ባንክ መመሪያ እንደወጣ ክፍያ የምትፈጽሙባቸው የውጭ ምንዛሬ የባንክ ሂሳቦች እና ማሟላት ያለባችሁ መመዘኛዎች ይለቀቃሉ።

በምስረታ ላይ ያለው አማራ ባንክ አ.ማ አክስዮን ሽያጭ በከፍተኛ ፍጥነት እየተሸጠ ይገኛል፣ በሀገራችን ኢትዮጵያ የግል ባንኮች ምስረታ ታሪክ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ አክስዮን በመሸጥ፣ የአክስዮን ሽያጭ ሪከርድ ያስመዘገበ ሲሆን፣ ባንኩን በጠንካራ የካፒታል መሰረት ላይ ለመገንባት በማቀድ የአክስዮን ሽያጩን አጠናክሮ ቀጥሏል።

በባንክ ስራ ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 1159/2011 መሰረት የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና ሙሉ በሙሉ የውጭ ሀገር ዜግነት ባላቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያውን ባለቤትነት የተቋቋሙ ኩባንያዎች አክስዮን ለመግዛት የሚችሉ ሲሆን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያውን የውጭ ሀገር ዜጎች አክስዮን መግዛት የሚችሉት በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ተቀባይነት ባለው የውጭ ምንዛሬ ብቻ ነው። ትውልደ ኢትዮጵያውያን የውጭ ሀገር ዜጎች የብሄራዊ ባንክ መመሪያ እስኪወጣ ድረስ በትዕግስት ጠብቁ ተብሏል፤ የብሄራዊ ባንክ መመሪያ ስራ ላይ እንደዋለ ክፍያ የምትፈጽሙባቸው የውጭ ምንዛሬ የባንክ ሂሳቦች እና ስዊፍት ኮዶቻቸው ይፋ ይደረጋሉ።

በምስረታ ላይ ያለው የአማራ ባንክ አ.ማ የአክስዮን ሽያጭ እስከ ህዳር 30 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ የሚቀጥል ሲሆን፣ እስከ ህዳር 30 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ አክስዮን ለሚገዙ የመስራችነት መብት የተጠበቀ ነው።

የባንኩ አደራጆች የባንኩን ምስረታ የሚያበስረውን ጠቅላላ ጉባኤ ለማከናወን በዝግጅት ላይ ናቸው። ዝግጅታቸውን እንደጨረሱ የጠቅላላ ጉባኤውን ጥሪ በሚዲያ የሚያሳውቁ ይሆናል።

Please wait, video is loading...