Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Ejersa
Member
Posts: 3976
Joined: 05 Nov 2019, 10:39

ግልገል አያቶላ "ሀገር በመዳፌ ስለሆነች ካነጠስኩ "ትወድቃለች" ይላል ታዬ ደንደኣ!

Post by Ejersa » 17 Nov 2019, 13:35

አንዳንዱ ሚናዉን የዘነጋ ይመስላል። "ሀገር በመዳፌ ስለሆነች ካነጠስኩ ትወድቃለች" ይላል። እሱ ካልፈለገ በኢትዮጵያ ፀሓይ የማትወጣ ይመስለዋል። በድጋፍ ስም በሁሉም ጉዳይ አማካሪና ወሳኝ መሆን ይፈልጋል። የኦዲፒ አመራር እሱ ወይም እሷ ያፀደቁትን ብቻ እንዲፈርም ይጠብቃል። ለሱ ያልገባዉን ሁሉ እንደ ስህተት ይቆጥራል። ይህ እንዴት ይቻላል? ሰዉ እንዴት በዝህ ደራጃ ራሱን አግዝፎ ይመለከታል? ደግሞ ጌታቸዉ አሰፋን ሲያመልክ የከረመ ዛሬ የጌታዉን ጌታ እንዴት ይጠራጠራል?

የኦዲፒ አመራር ምን፣ ለምን፣ መቼ እና እንዴት እንደሚያደርግ ያዉቃል። ያመነበትን ይወስናል። ደጋፊዎቹ ይህን አዉቀዉ ሚናቸዉን ይጫወቱ ዘንድ ይጠበቃል። ያለበለዝያ ግልገል አያቶላ ወይም የጠቅላዩ ጠቅላይ አድርጎ ራስን መሳል ያስከትላል። ያ ደግሞ የሚና መደበላለቅን ያመጣል። ሁሉም በልኩ ቢሆን ይሻላል። አንተ ፈልገህ የፃፍከዉን ብቻ ለመፈረም የተቀመጠ አመራር የለም። የጠቅላዩ ጠቅላይ መሆን ፈፅሞ አይቻልም። ሁላችንም በቁመታችን ተሰልፈን ሚናችንን ብንጫወት ለሀገር ይበጃል።

አንዳንዶች በፓርቲ ሪፎርሙ ማግስት ችግር እንዳይፈጣር ይሰጋሉ። መስጋታቸዉ ለሀገራቸዉ ያላቸዉን ፍቅር ያሳያል። ችግሩ ፈርቶ ማስፈራራታቸዉ ነዉ። በእርግጥ ከተለመደዉ ሁኔታ ወደ አዲስ ሁኔታ መሻገር በራሱ ያስፈራል። አከራካሪ ነገሮች ሲኖሩ ደግሞ ይበልጥ ግራ ያገባል። ነገር ግን በሪፎርሙ ምክንያት የሚፈጠር ችግር የለም። ቢፈጠርም ከልኩ አያልፍም። በህግ አግባብ ታርሞ መስመር ይይዛል። ሪፎርሙ በተጀመረዉ አቅጣጫ ሄዶ በተያዘለት ጊዜ ይሳካል። የኢትዮጵያ ህዝብም #ከEPP ጋር ወደ ሁሉ አቀፍ ብልፅግና ይሸጋገራል። ሠላም፣ ነፃነት፣ እኩልነት እና ወንድማማችነት በኢትዮጵያ እና በምስራቅ አፍሪካ በሚገባ ይሰፍናል! ራዕያችን እዉን ይሆናል!