Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Zreal
Member
Posts: 486
Joined: 15 Mar 2019, 20:33

የትግራይን ሰፊ ጉሮሮ የሚያንቅ አዲስ የበጀት ድልድልን የሚወስን ረቂቅ አዋጅ ቀረበ!!

Post by Zreal » 17 Nov 2019, 03:58





የትግራይን ሰፊ ጉሮሮ የሚያንቅ አዲስ የበጀት ድልድልን የሚወስን ረቂቅ አዋጅ ቀረበ!!



የፌዴራል መንግሥት በክልሎች የሚዘረጋቸውን የመሠረተ ልማት አውታሮች ፍትሐዊ ሥርጭት የሚከታተል ኮሚሽን የሚያቋቁም ረቂቅ አዋጅ ቀረበ

ethiopianreporter.com

17 November 2019

ዮሐንስ አንበርብር

ኮሚሽኑ የድጎማና የጋራ ገቢዎች ክፍፍል የሚደረግበትን ቀመር የማዘጋጀት ኃላፊነት ይኖረዋል

በፌዴራል መንግሥት ባለቤትነት በክልሎች ውስጥ የሚዘረጉ የመሠረተ ልማት አውታሮች፣ በክልሎች መካከል የሚኖራቸውን ፍትሐዊ ሥርጭት የሚከታተልና በገለልተኛ ባለሙያዎች የሚዋቀር ኮሚሽን የሚያቋቁም ረቂቅ ሕግ ለፓርላማ ቀረበ።

ረቂቅ ሕጉ እንዲቋቋም የሚጠይቀው ኮሚሽን የመሠረተ ልማቶች ፍትሐዊ ሥርጭትን ተከታትሎ ጉድለቶችንና መስተካከል ይገባቸዋል የሚላቸውን ምክረ ሐሳቦች፣ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አቅርቦ ውሳኔ እንዲሰጥበት እንደሚያደርግ የሕግ ሰነዱ ያመለክታል።

የሚቋቋመው ተቋም ስያሜ “የፌዴራል ድጎማና የጋራ ገቢዎች ክፍፍል ኮሚሽን” ሲሆን፣ የፌዴራሉ መንግሥት ለክልሎች የሚሰጠውን ዓመታዊ ድጎማ የሚደለደልበት ወይም ለፌዴራሉ መንግሥትና ለክልሎች የጋራ ተብለው በሕገ መንግሥቱ የተመደቡ ገቢዎች በሁለቱ መካከል የሚከፋፈልበትን ቀመር በሚመለከት፣ ተፈላጊውን በጥናት ላይ የተመሠረተ ምክረ ሐሳብ በማዘጋጀት ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የማቅረብ ኃላፊነትም ይኖረዋል።

ረቂቅ አዋጁን ያሰናዳው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ረቂቁ እንዲፀድቅለት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የላከ ሲሆን፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም በረቂቅ ሕጉ ይዘት ላይ ሐሙስ ኅዳር 4 ቀን 2012 ዓ.ም. የመጀመሪያ ውይይት ካደረገ በኃላ፣ ለዝርዝር ዕይታ ለሕግ ፍትሕና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቶታል።

ረቂቁ ኮሚሽኑን ከማቋቋም ባለፈም ክልሎች ከፌዴራል መንግሥት የሚያገኙትን የበጀት ድጎማ ዓይነትና የሚከፋፈሉበትን፣ እንዲሁም ክልሎችና የፌዴራል መንግሥት የጋራ ገቢዎች የሚከፋፈሉበትን መርህ እንደ አዲስ የሚወስንና ክፍፍሉ የሚፈጸምበትን ሥነ ሥርዓት የሚያበጅ ነው።

ረቂቅ የሕግ ማዕቀፉን ያዘጋጀው ጉዳዩን በተመለከተ ሕገ መንግሥታዊ ሥልጣን የተሰጠው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሲሆን፣ የሕግ ማዕቀፉ የመጀመሪያ ረቂቅ ተጠናቆ ከክልል መንግሥታት ጋር ውይይት እየተደረገበት ነው። እስካሁን የፌዴራል መንግሥት የሚመድበውን የድጎማ በጀት ለክልሎች የሚደለድልበትም ሆነ፣ የጋራ ገቢዎች የሚከፋፈሉበት የአሠራር ሥርዓት ወጥነትና ቅንጅት የጎደለው ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት በክፍፍሉ ሚዛናዊነትና ውጤታማነት ላይ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስተዋሉ የመጡ ክፍተቶችን ለመቅረፍ ይቻል ዘንድ መደበኛ የአሠራር ሥርዓት ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣ አዲስ የሕግ ማዕቀፍ ለማዘጋጀት መቻሉን የረቂቁ መግቢያ ያመለክታል። ...........

Read more


https://www.ethiopianreporter.com/article/17317