Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Ejersa
Member
Posts: 3976
Joined: 05 Nov 2019, 10:39

የመቀሌ ነዋሪዎች ለአየለ ጫሚሶና ትዕግስቱ አወል ዳጎስ ያለ ውሎ አበል እንዲከፍሉ ተወሰነ!!!!

Post by Ejersa » 16 Nov 2019, 09:57


ዶ/ር ደብረፂዮን እዚህ በኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ እየተሳተፉ ያሉት የራሳቸውን ዲፋክቶ ፓርቲ መስርተው እኮ ነው። ይህ ዲፋክቶ ፓርቲ በቀጣዩ ህዳር 14ና 15/2012 ዓ.ም መቀሌ ላይ ይመሰረታል። ስለዚህ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች አዲስ አበባ ላይ ሲዋሃዱ የህወሓት ተላላኪዎች ደግሞ መቀሌ ላይ ውህደት ይፈፅማሉ። ህወሓት “የፌዴራሊስት ኃይሎች” የሚል የቁልምጫ ስም ያወጣላቸው፤ ቅንጅትን ያፈረሰው አየለ ጫሚሶ፣ አንድነትን የሸጠው ትዕግስቱ አወል፣ ኦብኮን የለወጠው ቶሎሳ ተስፋዬ፣ አቶ ወርቁ የሚባለው የገዳ ስርዓት አራማጅ፣ ዶ/ር ሙልጌታ፣ አላምረው ይርዳው፣ መሳፍንት ሽፈራው እና እነሱን የመሳሰሉ አሸርጋጆችን ነው። እነዚህ ሰዎች መቀሌ ገብተው ከመሸጉ ሰንብተዋል። የህወሓት አገልጋይ እና ተላላኪ ለመሆን ወስነዋል። ህወሓት ደግሞ ዳጎስ ያለ የውሎ አበል ይከፍላቸዋል።

ችግሩ ምንም ያህል ገንዘብ ብትዘርፍ ስራ ተሰርቶበት ተጨማሪ ገንዘብ ካላመጣ ያልቃል። በተለይ ደግሞ እንደ ህወሓት ሁለት አመት ሙሉ ሆቴል ውስጥ የምትኖር፣ ዘወትር ውስኬ የምትጠጣ፣ ለተላላኪ፥ ለአሸርጋጅ፥ ለቦምብ አፈንጂ፣ ለፀብ ጫሪ፣ ለአጭበርባሪ፣ ለፍርፋሪ ፌደራሊስቶች የወር ደሞወዝ የሚያስንቅ ውሎ አበል የምትከፍል ከሆነ የዘረፍከው ብር ማለቁ አይቀርም። እንሆ ከውስጥ ያገኘነው መረጃ እንደሚጠቁመው የህወሓት ካዝና ተሟጥጦ አልቋል። ልብ አድርጉ ህወሓት እና ኢፈርት ይለያያሉ። ኢፈርት የስብሃት ነጋ እና የቤተሰቦቹ የግል ኩባንያ እንጂ የትግራይ ህዝብ ሆነ የህወሓት ንብረት አይደለም። ይህን ደግሞ ከተወሰኑ አመታት በፊት የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ኢፈርትን ባለቤትነት ለማዞር ሲወያይ አቶ ስብሃት ነጋ እንቅጯን ነግሯቸዋል። ዶ/ር ደብረፂዮን ለእንግዶቹ የሚከፍለው ብር አጥቷል። እንዲህ ፊቱን ያጨፈገገው ለዚህ እንደሆነ መገመት ይቻላል። ነገር ግን ለህወሓት ተላላኪዎቹ ከሚያኮርፉበት የትግራይ ህዝብ ቢሰቃይ ይመርጣል። በመሆኑም ደፂ ለአቶ ዳንኤል አሰፋ (የጌታቸው አሰፋ ወንድም) የመቀሌ ከተማ መስተዳደር ለእነ አየለ ጫሚሶ ከምግብና መኝታ ውጪ በቀን 500 ብር ውሎ አበል እንዲከፍል ትዕዛዝ ሰጥቷል።

የአዲስ አበባ ህዝብ አንቅሮ የተፋውን የመቀሌ ህዝብ ይወድለታል እንዴ?? በተለይ ደግሞ የአየለ ጫሚሶ ነገር እጅግ በጣም ይመስጠኛል!! በጣም ገራሚ ሰው እኮ ነው!!!