Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Ejersa
Member
Posts: 3976
Joined: 05 Nov 2019, 10:39

በ OMN ስም የተሰበሰበውን ዶላር መታገዱ ተሰማ!!!!!

Post by Ejersa » 15 Nov 2019, 21:45

ጃዋር_መሃመድ በፌስቡክ እና OMN አማካኝነት እያደረገ ያለውን የዘር ማጥፋት ቅስቀሳ እና ከህወሓት ጋር በመመሳጠር ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለመግታት በሁሉም አቅጣጫ ርብርብ ሊደረግ ይገባል። በዚህ ጃዋርን በህግ ተጠያቂ ማድረግ አንዱ ሲሆን ሌላው ደግሞ ለዚህ የጥፋት ዓላማ የሚውለውን የገንዘብ ምንጭ ማድረቅ ነው። በዚህ ረገድ ጃዋር በፌስቡክ አማካኝነት የጀመረውን የገንዘብ ማሰባሰብ ለማስቆም ከፍተኛ ጥረት ተደርጓል። ከፌስቡክ ፕሬዜዳንት ጀምሮ በፌስቡክ ለአፍሪካና ምስራቅ አፍሪካ ጉዳይ ሃላፊዎች በሺህ የሚቆጠሩ የኢሜይል መልዕክቶች ተፅፈዋል። ከዚያ በኋላም ባሉት ቀናት ጃዋር መሃመድ እና ግብረአበሮቹ በፌስቡክና OMN የሚያወጧቸውን በጥላቻ የታጨቁ ሃሰተኛ መረጃዎችን ጉዳዩ ለሚመለከታቸው የፌስቡክ ሃላፊዎች ሪፖርት በማድረግ ላይ እንገኛለን። በዚህ መሠረት GuidStar.Org የተባለው ድርጅት OMN (የመለያ ቁጥር: EIN 46-5137810) ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች ኔትዎርክ አማካኝነት ገንዘብ እንዳይሰበሰብ አግዶታል። ከዚህ በተጨማሪ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከተው @Network4Good⁩ https://t.co/Ue00JGmahJ የተባለው ድርጅት ደግሞ OMN Internal Revenue Service (IRS) ያስገባው ማስረጃ እንዲመረመር ጠይቋል። ይህ ካለሆነ ግን OMN በፌስቡክ አማካኝነት የሰበሰበው ዶላር እንደማይሰጠው አረጋግጧል። የOMN ለIRS ያስገባው ዶክመንት ደግሞ ከፍተኛ መጭበርበር ያለበት ነው። ይህን ሊንክ በመጫን ሪፖርቱን አውርዶ መመልከት ይቻላል፦ https://t.co/kGB6rYfeod ሆኖም ግን ከሪፖርቱ ውስጥ በጣም የገረመኝ ነገር OMN 17 ደሞወዝ ተካፋዮች እንዳሉት ከገለፀ በኋላ ጃዋር ለብቻው 53,846 ዶላር ይከፈለዋል። የተቀሩት 16 ሰዎች ግን የበይ ተመልካች ናቸው ማለት ይቻላል። የአካውንቲንግና ፋይናንስ ባለሞያዎች ይህን ሪፖርት በአግባቡ መርምራችሁ የጃዋርን አጭበርባሪነት ማጋለጥ ይጠበቅባችኋል። ለማሳያ እንዲሆን የሪፖርቱን የወሰኑ ክፍሎች እዚህ የምለጥፋቸው ሲሆን ሙሉ ሪፖርቱን ደግሞ ይህን ሊንክ በመጫን ማውረድ ይቻላል።
ለአሜሪካ ገቢዎች መ/ቤት ያስገባውን ሪፖርት