Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
MatiT
Senior Member
Posts: 11549
Joined: 16 Feb 2013, 10:18

የፌደራሉ መንግስትና የለውጡ አመራር ህወሃትን አይቀጡ ቅጣት ለመቅጣት ዝግጅት ማድረግ ይገባል/ ከኤርትራ መንግስትም ጋር ሁለንተናዊ የጋራ መከላከያና ደህንነት ስምምነት ማድረግ/ ንዓምን ዘለቀ

Post by MatiT » 15 Nov 2019, 20:23

የፌደራሉ መንግስትና የለውጡ አመራር ህወሃትን አይቀጡ ቅጣት ለመቅጣት ዝግጅት ማድረግ ይገባል።

1ኛ። የፌደራሉ መንግስት ለትግራይ ክልል የመደበውን በጀት ለማገድ ዝግጅቶች መጀመር ያለበት ይመስለኛል

2ኛ፣ የህወአት መሪዎች ንብረት የሆነውን የኢፊርት ኩባንያዎች፣ እርሻዎችን፣ ፋብሪካዎች በተመሳሳይ ማገድ፣ ማሸግ፡

3ኛ፣ በአለም አቀፍ ማህበረስብና በወዳጅ ሀገሮች ትብብር የህወሃትና የደጋፊዎቻቸውን ገንዘብ፣ በሀገር ውስጥም በውጭ ሀገራትም የማሳገድ፣ ለኢትዮጵያ ህዝብ ተመላሽ እንዲሆኑ ልዩ ልዩ እርምጃዎች መወስድ፡

4ኛ። ከመሰረታዊ የአለታዊ ፍጆታና ፣ ምግብና የመሳሰሉ ውጭ ከመሃል ሃገር ወደ ትግራይ የሚገቡ ማንኛቸውም የኢንዱትሪ ምርቶች፣ ሸቀጦች አገልግሎቶች ማገድ ።

5ኛ። ሊያደርሱ የሚችሉትን ሁለንተናዊ ቀውስና ሌላም የእብደት እርምጃዎች ለመከላከል፣ ከኤርትራ መንግስት ጋር ሁለንተናዊ የጋራ የመከላከያና የደህንነት ስምምነቶች በአስቸኳይ ለማድረግ የሚቻልበት ሁኔታዎችን መፈለግ አስፈላጊዎቹና ወሳኝ እርምጃዎች ይመስሉኛል፡

ወያኔ የሚባል እኩይ ሃይል የጋራ አገራችን ኢትዮጵያን አገራዊ ትርምስ ውስጥ ብትገባ ፈጽሞ የማይጨነቁበት መሆኑን ሲጀምሩም የተነሱበት የፓለቲካ አላማ፣ ታሪካቸው ፣ እስካሁንም የቀጠሉበት አንደበታቸው፣ የተካኑበት መሰሪነትና ተንኮል ያረጋግጣል። የኢትዮጵያ ካንስር ሆና የቆየ፣ አሁን ለገባንበት የብሄር የጥላቻና የቅራኔ ፓለቲካ፣ በማህበረስቦች መካከል የጥላቻ ግንቦች እንዲሰሩ ትልቁን ሚና የተጫወተ ፣ ይህን የጥፋትና የክፋት ክምችት ሃይል ብዙ ሲታገስ የቆየው የፌዴራሉ መንግስትና የለውጡ አመራር ፣ የዚህን የኢትዮጵያ ጸር፣ የህዝቦች ፣ የትግራይም ህዝብ ጠላት የሆነ ሃይል ክንፎች ከወዲሁ ለመምታት ልዩ ልዩ እርምጃዎችን አጥንቶ ቀድሞ ለመገኘት መንቀሳቀስ ያለበት ይመስለኛል።

እነዚህን እርምጃዎች በመውስድ ኢትዮጵያን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥረን ካልዘረፍን እናፈርሰዋለን ብለው ከአንድ አመት በላይ የቆየ ትርምስ፣ ግጭቶች፣ ቅራኔዎችን በማስፋፍት ትልቁን አፍራሽ ሚና የተጫወቱት፣ ያረጁ ያፈጁ፣ ከ21ኛ ክፍል ዘመን ጋር ፈጽሞ መሄድ ያልቻሉ የፓለቲካ ድኩማኖች አይቀጡ መቅጣት፣ እቅማቸውንም እንዲያውቁ አስፈላጊ ይመስሉኛል።.

ይህ የጥፋትና የክፋት ክምችት የሆነ የፓለቲካ ድርጅት ሀገራችን የምትገኝበትን በርክታ ምስቅልቅሎች በማጦዝ፣ በገንዘብና በመረጃ እቅማቸው በማባባስ የጥፋት ድርጊቶቻቸውን ሲፈጽሙ ከረሙ። ክመሸጉበት ለማንሰራራት፣ ብሎም የኢትዮጵያን ሃገረ መንግስት ማዕከል ዳግም ለመቆጣጠር ያላቸውን ቀቢጸ ተስፋ ዕውን ለማድረግ፣ የለመዱትንም ግፈኛ መንግስታዊ ሽብርና መንግስታዊ ዘረፋ በመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ኪሳራ ለማስቀጠል ሙከራቸውን ለማድረግ ባለመቻላቸው፣ ዛሬ “ትግራይን ገንጥለን የራሳችን ሀገር ማቆም አለብን" ወደ ሚለውን ወደ ቅዠት የሚወሳዳቸውን የ45 አመት መሰሪና መሰረታዊውን ግባቸውን ለመፈጸም እንዳኮበኮቡ ሰሞኑን የሚወጡ መረጃዎች እየጠቆሙ ነው።