Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Ejersa
Member
Posts: 3976
Joined: 05 Nov 2019, 10:39

ዛሬ ወልድያ ሆስፒታል ሊሆን የነበረው የተንኮል ድርጊት!

Post by Ejersa » 15 Nov 2019, 12:12

ይህ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ግለሰብ በምናያት ያሪስ ተሽከርካሪ ወልድያ ሆስፒታል ሰርጅካል ዋርድ ይገኝና የሆስፒታሉን ባለሙያዎች የመጣሁት ከኦሮሚያ ክልል ተልኬ ነው። አመጣጤም በቅርቡ በዩኒቨርሲቲው በተፈጠረው ግጭት ምክኒያት ጉዳት የደረሰባቸውን ተማሪዎች ለመጎብኘት እና ደህንነታቸውን ለማረጋገጥ ነው። እናም እነሱን እንዳገኝ ፍቀዱልኝ ብሎ ይጠይቃል።

ሙያተኞቹም አሁን እኛ ህሙማንን የምንከታተልበት ስዓት ስለሆነ የራውንድ ስራችንን ከጨረስን ቡኋላ መጎብኘት ትችላለሁ ብለው ወደ ስራቸው ያመራሉ።
ሰርጅካል ዋርድ ያሉት ሙያተኞች በዚህ መልስ ሲያሰናብቱት ግለሰቡ ወደ ሜዲካል ዋርድ ያመራና በኩፍኝ ምክኒያት ከዩኒቨርስቲው ወደ ሆስፒታሉ ተልከው በመታከም ላይ ወዳሉት ተማሪዎች ከሙያተኛች በስተቀር ሌላ ሰው እንዳይገኝ በተከለከለ ክፍል ጋውን በመልበስ ሀኪም በመምሰል ሲገባ የግለሰቡ ሁኔታ ያላማራቸው የክትትል/ደህንነት አባላት ሲከታተሉት ነበር እና ሩቅ ሳይሄድ በቁጣጥር ስር አውለው ወልድያ ፖሊስ ጣቢያ በምርመራ ሙያተኞች እና የፖሊስ ጣቢያው አመራሮች በምርመራ ላይ ይገኛል።

እንግዲህ ከዚህ ምን የምንረዳው ነገር አለ?? ወደሚለው ጉዳይ እናምራ።
በአማራ እና ኦሮሞ ህዝቦች መካከል ስምምነት እንዳይኖር እና የንፁሃን ደም እንዲፈስ ሙሉ ጊዜውን ሰውቶ የሚሰራ ሃይል አለ የምንለውም ያለ ምክኒያት አይደልም።

አስቡት ይሄ ሰው ተሳክቶለት በሆስፒታሉ በተኛ ተማሪ ላይ ህልፈተ ህይወት ቢፈጠር በሁለቱ ክልል ህዝቦች እና መንግስታት መካከል ምን ሊፈጠር እንደሚችል።
ከኦሮሚያ ክልል የመጡ ተማሪዎች ወልድያ ዩኒቨርሲቲ ሞቱ ተብሎ ኦሮሚያ በሚገኝ አማራ ላይ እርምጃ ውሰድ በማለት ግጭትን የፈጠረ ሃይል የተንኮል መንገዱን ቀይሮ መጥቷል።በመንግስት ጤና ድርጅት የሚታከም ተማሪ ተመርዞ ሞተ ለማስባል የሴራ አካሄዳቸውን ቀይረው መጥተዋል።

የጤና ተቋማት ያለ አድሎ በገለልተኛነት መንፈስ አገልግሎታቸውን በሚሰጡበት ሁኔታ ከህሊና ውጭ የሆነ ፍጻሜ በዚህ ሆስፒታል ሲፈጠር ምን ያህል ኪሳራ እንዳለው እስኪ እንገምት፡፡

በዚህ አጋጣሚ የወልድያ ሆስፒታል ሙያተኞችን፡ የአካባቢው የደህንነት እና የፖሊስ አባላት ላሳዩት አገራዊ ሃላፊነት የተሞላበት ትጋት ማመስገን እወዳለሁ።ለታካሚዎች ጥብቅ ጥበቃ ሊደረግ ይገባል።
የአካባቢያችንን ድህንነት እና ጸጥታ በጋራ እንጠብቅ !!!




Post Reply