Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Ejersa
Member
Posts: 3976
Joined: 05 Nov 2019, 10:39

ሰበር መረጃ:- ትህነግ በሚመሰርተው የተላላኪዎች ግንባር በአባልነት የተመዘገቡ የፖለቲካ ቡድኖች ዝርዝር!

Post by Ejersa » 14 Nov 2019, 15:11

መቼም ቢሆን ሀገር ለመበተን ቦዝነው የማያውቁት ህወሓቶች ዛሬም መቀሌ መሽገው ያሸለቡ ቢመስሉም አይናቸውን ጨፍነው የእውር ድምብር ጉዞዋቸውን ቀጥለዋል! ከመሀል ተገፍታ መቀሌ ያለችው ህወሓት ውህደቱን ጉሮሮዋ እስኪደርቅ ድረስ ብትቃወምም ጠብ የሚል ነገር ስለጠፋ እና የኢህአዴግ ውህደት እውን የመሆኑ ነግር ሳይታለም የተፈታ መሆኑ ሲገባት በትላንትንልው እለት ትህነግ ሀገራዊ ግንባር ልትመሰርት ስበሰባ ተቀምጣ ነበር:: በዚህም ስብስባ አዲስ ሀገራዊ ግንባር ለመመስረት በገንዘብ እና በተለያዩ የድለላ ዘዴዎቿ ያሰባሰበቻቸው ግለሰቦች እና ቡድኖች የሚከተሉት ናችው:-
1) አየለ ጫሚሶ ከቅንጅት፣
2) መስፍን ሽፈራው ከመኢብን፣
3) ትግስቱ አወል ከአንድነት ፖርቲ፣
4) አላምረው ይርዳው ከአገው ሸንጎ፣
5) ከጌዲዮ ህዝቦች ደሞክራሲ ድርጅት፣
6) ዶክተር ሚሊዮን ከሲአን፣
7) ዶክተር ሙሉጌታ በአካሉ (ስሙ ካልተለየ ከሲዳማ ድርጅት)፣
8) ኦሞ ህዝቦች ዴሞክራሲ ህብረት፣
9) የገዳ ስርዓት አራማጅ ፓርቲ፣
10) ወላይታ ዴሞክራሲያዊ ፖርቲ፣
11) የአፋር ፓርቲ አርዱፍ የሚባልና አፋር ዴሞክራሲ ፓርቲ፣
12) የአርጎባ ፓርቲ፣
13) የቅማንት ዴሞክራሲ ድርጅት፣
14) ከቤኔ ሻንጉልና ጋምቤላ ተቃዋሚ ፓርቲ (ስማቸው አልተለየም)፣
15) እንዲሁም ከሶማሌ፣ አፋር እና ድሬዳዋ በስም ያልተለዩ ሽማግሌዎች ተሳትፈው ነበር

በትላንቱ ስብሰባ የተገኙትን ባይገልፁም ከሲአን ሚሊዮን በህመም፣ ከአፋር መሀመድ ኡስማን ምክንያቱ ባልተገለፁ፣ የቅማንት ተወካይ በመንገድ ችግር፣ የቤኔሻንጉሉም የአውሮፕላን ትኬት በማጣቱ እንዳልተገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ:: ትህነግ 27 ዓመት ስታጨበረብር ኖራ እሁንም በድሮ በሬ ካላረስኩ እያለች የምትጋጋጠውን እና የቸገረው እርጉዝ ያገባል ሆኖባት የጅል ስራዋን ተያይዛዋለች ይሄ ስራዋም የት እንደሚያደርሳት ጊዜ ያሳየናል።
EthioWikiLeaks