Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abaymado
Member
Posts: 4207
Joined: 27 Sep 2017, 21:56

ኢህአዲግ እሮብ ውህደቱን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል::ለማንኛውም አብን ከብአዴን ጋር ለመዋሃድ ማሰብ የለበትም!

Post by Abaymado » 11 Nov 2019, 10:53

እሮብ ምናልባት ወሳኝ ቀን ነው : ማለት የኢህአዲግ ነገር ተስፋ የሚጣልበት ወይ ደሞ የባሰ የሚንገዳገድበት ነው:: ዋናው ተገዳዳሪ ደሞ ኦህዴድ ነው:: የወያኔ አቅዋም እንደሆነ ቀድሞውኑ የታወቀ ነገር ነው:: ደቡብና ብአዴን የኢህአዴግን ውህደት ይደግፋሉ ተብሎ ይጠበቃል:: ትንሽም ቢሆን የኦህዴድ አባላት ድጋፍ እንደሚሰጡ ይጠበቃል:: እናም የኢህአዲግ ውህደት እውን የሚሆን ይመስላል:: ግን ጥያቄው ምን ያህሉ ኦህዴዶችና እነማን ይቃወማሉ?

ብአዴን ከአብን ጋር መዋሃድ ይፈልጋል: ይህ ግን ሊሆን የሚገባው ብአዴን ከኢህአዴግ ከወጣ ወይም ውህደቱ ካልተሳካ ነው:: አለበለዚያ የአማራ ጥቅም ይነካል:: ከመዋሃዳቸው በፊት ብአዴን ሊያስተካክል የሚገባው ነገር አለ::ውህደቱ መፈፀም የለበትም::