Page 1 of 1

አቶ ጌታቸው ረዳ የሉሊት ጌታቸው አሰፋ "ሎሌ" ነው! Ethio Wiki Leaks

Posted: 07 Nov 2019, 20:57
by Hameddibewoyane
አቶ ፍፁም ብርሃኔ በሆነ የዩቲዩብ ቻናል ላይ በሰጠው አስተያየት መሰረት “የአቶ ጌታቸው ረዳ የኢሜይል አካውንት ሃክ ተደርጓል የሚባለው ነገር ውሸት ነው” በማለት ተናግሯል። በመሰረቱ እንደ ፍፁም ላለ ሰው ውሸት ልምድና ልማዱ ስለሆነ ለምን ዋሸ አይባልም። ነገር ግን ውሸታም የሚናገረው ጥቂትም ቢሆኑ ሰምተውኝ የሚያምኑ ሰዎች ይኖራሉ በሚል እሳቤ ነው። እኛ ደግሞ በዚህ ረገድ አንድም ሰው መሳሳት የለበትም የሚል እምነት አለን። ስለዚህ አቶ ጌታቸው ረዳ ከሉሊት ጌታቸው አሰፋ ጋር በቨይበር ያደረገውን ውይይት እንሆ ጀባ ብለናችኋል። አቶ ጌታቸው ረዳ ለጌታቸው አሰፋ ብቻ ሳይሆን የልጁም ተላላኪ እንደሆነ በግልፅ ያሳያል። ጌችዬ ኢሜይልህ ምንድነው? የደቡብ አፍሪካና ኢትዮጵያ ጨዋታ ትኬት ግዛልኝ? ለአንድ ስራ አጥ ለሆነ ወዳጄ ሥራ ፈልግለት? በአጠቃላይ ጌታቸው ረዳ የጌታቸው አሰፋ ብቻ ሳይሆን የልጁ ሉሊት ሎሌ ነበር ማለት ይቻላል።