Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Ejersa
Member
Posts: 3976
Joined: 05 Nov 2019, 10:39

የኢህአዴግን ውህደት የሚቃወሙት እነማን ናቸው? Abeba Tekalign

Post by Ejersa » 07 Nov 2019, 19:32

👉የኢህአዴግን ውህደት የሚቃወሙ ስልጣናቸውን በብቃት፣ በአቅም እና ለህዝብ ባላቸው ተቀባይነት አግኝተነዋል ብለው የማያምኑ፣ ውህደት ከመጣ ብቃት መመዘኛ ስለሚሆን ስልጣኔን አጣለሁ የሚል ስጋት ያለባቸው ነው ፡፡

👉የኢህአዴግ የውህደት ሃሳብ አሁን የመጣ አይደለም፡፡ ከ1996 ዓ.ም ጀምሮ ጉባኤ በተዘጋጀባቸው መድረኮች ሁሉ ሲነሳ የነበረ ነው፡፡ በወቅቱ “ጊዜው ገና ነው” ከማለት ውጪ ውህደት አያስፈልግም የሚል ተቃውሞ ተነስቶ አያውቅም፡፡

👉እንደአሁኑ ፌዴራሊዝምን ይደፍቃል፣ ይጨፈልቃል የሚል ሃሳብ አልነበረም፡፡

👉“አሁን ውህደቱን የሚቃወሙ እና በጥርጣሬ የሚያዩ ፓርቲዎች በፊት ውህደቱን ይደግፉት ነበር ።
የውህደቱ ተቃዋሚዎች በብቃት፣ በአቅም እና ለህዝብ ባላቸው ተቀባይነት ስልጣን አለማግኘታቸው የሚያሳስባቸው ናቸው፡፡

👉ብዙ የፌዴራል አገሮች ተሞክሮ እንደሚያሳየው አንድ ፓርቲ በምርጫ ተፎካክሮ ካሸነፈ በፌዴራል ሥርዓት ስር ያሉ የክልል መንግስታትንም ያስተዳድራል።

👉የኢህአዴግ ውህደት አሃዳዊ ሥርዓትን ያመጣል፤ ብዝሀነትን ይጨፈልቃል የሚለው ስጋት ከዓለም አቀፍ ተሞክሮ አንጻር አብሮ የሚሄድ አይደለም፤ ተቀባይነትም የለውም።

👉ኢህአዴግ ውህድ ፓርቲ ሲሆን በየክልል መንግስታት ውስጥ ቅርጫፎች ይኖሩታል።

👉ውህደቱ ዴሞክራሲያዊ ምህዳሩን ያሰፋል እንጂ አሃዳዊ ሥርዓት የሚያመጣ አይደለም ።

👉በሌላ በኩል ኢህአዴግ አምስቱ አጋር የሚላቸውን ፓርቲዎች በምንም ሚዛንና ምክንያት ያልተወያዩባቸውን ፖሊሲዎች እንዲፈጸሙ ግዴታ እንደሚጥልባቸው ገልጸው ይህ አካሄድ ኢህአዴግ አግላይ ድርጅት እንደሆነ ያሳያል ብለዋል።

👉በዚህም የተነሳ አጋር ፓርቲዎችን በአገሪቱ ጉዳይ ላይ ተሳታፊ ለማድረግ በውህደቱ እንዲካተቱ ማድረግ አስፈላጊና ተገቢም ነው ።