Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Hameddibewoyane
Member
Posts: 3890
Joined: 25 Sep 2019, 02:42

Walmart ወደ ኢትዮጵያ እንዲገባ አምስት የህወሓት ባለስልጣናት መሞት አለባቸው” አቶ ጌታቸው ረዳ

Post by Hameddibewoyane » 06 Nov 2019, 21:20

አቶ ጌታቸው ረዳ ኃይለኛ ደላላ ነው። የድለላ ስራ የሚሰራው ደግሞ ዝም ብሎ ሳይሆን እንደ ሼህ መሃመድ አል-ሙዲን ላለ ባለሃብት፣ እንደ ሪክ ማቸር ባለቤት ያለ ባለስልጣን፣ እንዲሁም እንደ ዋልማርት (Walmart) ላለ ትልቅ ዓለም-አቀፍ ድርጅት ነው። ዋልማርት የኢትዮጵያን ገበያ ለመቆጣጠር ከፍተኛ ፍላጎት ነበረው። አቶ ጌታቸው ረዳ ደግሞ የድለላ ስራ ለመስራት ቀብዱ ተቀብሏል። ሆኖም ግን ዋልማርት ወደ ኢትዮጵያ ገበያ እንዲገባ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መፅደቅ አለበት። ጌቾ ይህን ለማድረግ ያደረገው ጥረት አልተሳካም። ይህን ተከትሎ ከአንድ ማንነቱ ካልታወቀ ግለሰብ ጋር (ስልኩ ግን ይታወቃል) ጋር ስለ ሁኔታው በቫይበር ያደረገው ቻት እንሆ በረከት ብለናችኋል። ከታች በምስሉ ላይ እንደተገለፀው አቶ ጌታቸው ረዳ ዋልማርት ወደ ኢትዮጵያ ገበያ እንዲገባ አምስት ከፍተኛ የኢኮኖሚ አማካሪዎች መሞት እንዳለባቸው በግልፅ ይናገራል። አሁንም ቢሆን የያዘው ይዞት እንጂ ጌቾ እነ ስብሃት ነጋ፣ አባይ ፀሓዬ እና ስዩም መስፍን ከመሰሎ ሽማግሌዎች ጋር አብሮ መቆየት አይፈልግም። እንኳን አሁን የዛሬ አምስት አመት ቢሞቱለት ደስታውን አይችለውም።


Post Reply