Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 5545
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

ክስ ኣለኝ

Post by Naga Tuma » 04 Nov 2019, 22:18

ተከሳሽ፥ የሲጋር እናት፣ በምድር ላይ ይሁን በገነት ባሉበት

ልዩ ችሎታቸዉ፥ ጥንታዊ የኢትዮጵያን ስልጣኔን ጠንቅቀዉ ያጠኑ እና የኣወቁ

እማኝ፥ ይህንኑ ልዩ ችሎታቸዉን፣ የማስፈራራትን እና ማቅራራት ልዩነት፣ ወልደዉ ኣስተምራዉት ያሳደጉት ልጃቸዉ ሲጋር በመረጃ መድረክ በኣደባባይ ሲገልጽ የተሰማ

ጥንታዊ የኢትዮጵያ ስለጣኔ ኤርትራ ዉስጥ ስለመኖሩ ምስክሮች፥ ኤርትራ ዉስጥ ኖረዉ ያዩ ስማቸዉ የታወቀ ኢትዮጵያን። ለምሳሌ ሻለቃ ዳዊት ወልደግዮርጊስ፣ ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ፣ ኢትዮጵያዊነትን በጥልቀት የስተዋሉት ኤርትራ ዉስጥ ኖረዉ ካዩ በኃላ መሆኑን በኣደባባይ የተናገሩትን ጨምሮ

የዚህ ክስ ስሞታ፥ ልዩ ችሎታቸዉን ያስተማሩትን ልጅ ወደ ኢትዮጵያ ዘልቆ እንድያስተምር ሳይሆን ናቅፋ ሄዶ እንዲመሽግ መንገድ ማሳየታቸዉ

እኝህ የኢትዮጵያ ጥንታዊ ስልጣኔ ጥልቅ እዉቀት ያላቸዉ እናት የኖቤል ሽልማት ወደ ምድረ ኢትዮጵያ ይገባል መባሉን በቅርቡ የሰሙ ጊዜ ክላ ሽልማቱ ኣይጥዬ በወጣትነት እድሜዉ ያጠለቀዉን ኩታ ከኣእምሮዬ ኣይፍቅም ብለዋል የሚል ግምት ኣለ

የደረሰ ጉዳት፥ በቅርቡ ኢትዮጵያ ዉስጥ ተከሰተ የተባለዉ ኣሰቃቂ እልቂት ይህ ጥንታዊ የኢትዮጵያ ስልጣኔ እዉቀት ማነስ መሆኑ እና ለዚህም ስልጣኔ ማነስ ሲጋር የተማረዉ ልዩ ችሎታ በርቀት መቅረቱ ኣስተዋጽኦ ኣለዉ ተብሎ ይገመታል

የኣሰቃቂዉ እልቂት እማኞች፥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን መሪዎች፣ ስማቸዉ የታወቀ የኢትዮጵያ የፖለቲካ መሪዎች፣ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ ፕሮፌሰር መረራ ጉድና፣ የሰዉ ልጅ ይቅርና ከብት ሲጎራ በስመ ኣብ እና ብስምላሂ ቀድሞ ማለትን ጥንት ጊዜ ያስተማሩ ነብዮች፣ እየሱስ እና መሃመድ

ይህ ክስ መሰረታዊ እና የሰዉ ልጅ ስልጣኔን የሚመለከት ነዉ ብዬ ስለማምን ይሰማልኝ

ይህን ክስ የማሰማዉ የህግ ባለሙያ በመሆን ሳይሆን በሰማሁት እልቂት እና የታሪክ ጠባሳ በጥልቅ ያዘንኩኝ ዜጋ ስለሆንኩ ነዉ