Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Hameddibewoyane
Member
Posts: 3890
Joined: 25 Sep 2019, 02:42

ያፈተለኩ ሚስጥሮች Ethiowikileaks!

Post by Hameddibewoyane » 03 Nov 2019, 21:28

በእነ ጃዋር መሃመድ የተዘረጋው ስውር እጅ!
በአዲስ አበባና በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች የሚደርሱትን ጥቃቶች የተመለከተ ሰው በስውር ተደራጅተው የሚንቀሳቀሱ ሃይሎች እንዳሉ ይታዘባል። አቶ ታዬ ደንደዓ አምቦን ለመበጥበጥ ከ 10 በላይ ሙከራዎች መደረጋቸውን የጠቀሰበት ጽሁፍ፣ ዶ/ር አብይ አህመድ በቅርቡ ባወጡት መግለጫ “ይህ ሁሉ ለምን እንደመጣብን እናውቃለን። ከዚህ የበለጠ ፈተና ቢያጋጥመንም እንኳን የጀመርነውን ጉዞ አናቋርጥም” ማለታቸው፣ በተደጋጋሚ በባልደራሱ ሊ/መንበር እስክንድር ነጋ ላይ የሚደርሰው ጥቃት፣ ጃዋር ሙሃመድ “በሃይልም ቢሆን አያሸንፉንም” በማለት በትዕቢት የተናገረው ንግግር፣ አንድ የኦሮሞ ተወላጅ የሆነ የመከላከያ ሰራዊት አባል “ ሲ ኮማንዶ በሚል የመከላከያ አባላት መደረጀታቸውን መግለጹ እንዲሁም በመሳሪያ ሃይል የታገዘ ተደጋጋሚ ዘረፋ መፈጸሙና የመሳሰሉት ድርጊቶች፣ በስውር የሚንቀሳቀስ ( ሱ) ጸረ-መንግስት የሆነ ( ኑ) የኦሮሞ ድርጅት (ቶች) መኖሩን ወይም መኖራቸውን የሚያመልክት ነው። ይህ ስውር ሃይል በአንድ የዕዝ ሰንሰለት የሚመራ ይሁን አይሁን ማወቅ ባይቻልም ጸረ-አብይ፣ ጸረ-ኢዜማ፣ ጸረ-አማራ እና በአጠቃላይ ጸረ አንድነት አቋም እንዳለው ከንግግሩና ከድርጊቱ መታዘብ ይቻላል ።

በዚህ ስውር ሃይል ውስጥ የተወሰኑ የደህንነት፣ የመከላከያ፣ የፖሊስ እንዲሁም የኦዴፓ አባላት እንዳሉ፣ ጃዋርን የመሳሰሉ አክቲቪስቶችም እንደ አገናኝ ድልድይና ማዕከል ሆነው እያገለገሉ እንደሆነ እረዳለሁ። ይህን ስውር ሃይል በስውር የሚከታተልና የሚያዳክም፣ ምናልባትም በመንግስት ደህንነት ስር የተዋቀረ ሌላ ስውር ሃይልም እንዳለ ይሰማኛል። ለሁለቱም ስውር ሃይሎች የሚሰሩ 5ኛ ረድፈኞች እንዳሉም ማየት ይቻላል። መረጃዎችን ከአንዱ ወስደው ለሌላው ስለሚያቀብሉም አንደኛው ሃይል አሸንፎ እንዳይወጣ እንቅፋት የሆኑበት ይመስለኛል። ጸረ መንግስት የሆነው ስውር ሃይል በአላማና በዞን የተከፋፈለና እርስ በርሱ የሚጠራጠር በመሆኑ፣ የሚመኘውን በቀላሉ ማድረግ አልቻልም፣ የሚችልም አይመስለኝም። ይሁን እንጅ ህዝብን እየዘረፈና እያሸበረ ህዝቡ በመንግስት ላይ ተስፋ እንዲቆርጥ የማድረግ ስትራቴጂ እየተከተለ ለተወሰነ ጊዜ ሊቀጥል ይችላል። በተለይ በመጪው ምርጫ ላይ ኢዜማን የመሳሰሉ ሃይሎች አዲስ አበባ ላይ ቢያሸንፉ በተሰፋ መቁረጥ ስሜት ውስጥ ሆኖ ከተማዋን የብጥብጥ አውድማ ለማድረግ የመጨረሻ አማራጩን ሊጠቀም ይችላል።

አሁን የመንግስት ትልቁ ፈተና ይህን ለራሱም ለህዝብም ለአገርም ለዲሞክራሲ ግንባታም አደጋ የደቀነውን ስውር ሃይል ተቆጣጥሮ የህዝብን አመኔታ መልሶ ማግኘትና ሰላምና መረጋጋት መፍጠር ላይ ነው። ይህን ማድረግ ካልቻለ ግን ራስን ለመከላከል በሚል ምክንያት በአገሪቱ ውስጥ ስፍር ቁጥር የሌላቸው የስውር የብሄርና የሰፈር ድርጅቶች መፈጠራቸው አይቀሬ ነው። መንግስት አንዴ 8ኛው ሺ ውስጥ ከገባን በሁዋላ ወደ 7ኛው ሺ የሚመልሰን ሃይል እንደማይኖር አውቆ በፍጥነት የደህንነት መዋቅሩን ፈትሾ የማስተካከያ እርምጃ ይውሰድ።

Abdelaziz
Senior Member
Posts: 11365
Joined: 29 May 2013, 22:00

Re: ያፈተለኩ ሚስጥሮች Ethiowikileaks!

Post by Abdelaziz » 04 Nov 2019, 01:20

Your Hamasenay mitrileaks are the only real thing, none of the leaks the fagat waragay Seyum Teshome fabricated and that you had been copying and pasting here for days are not even remotely related to truth, your Ho'moshenay world is really leaky , surreal and perverted.

kibramlak
Member
Posts: 2155
Joined: 26 Sep 2013, 09:27

Re: ያፈተለኩ ሚስጥሮች Ethiowikileaks!

Post by kibramlak » 04 Nov 2019, 02:01

Excellent view and advice !
Hameddibewoyane wrote:
03 Nov 2019, 21:28

Post Reply