Page 1 of 1

ሰበር ዜና - እነ እስክንድር ነጋ ከጥቃት ተርፈው አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ይገኛሉ

Posted: 02 Nov 2019, 13:50
by MINILIK SALSAWI
እነ እስክንድር ነጋ ከጥቃት ተርፈው አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ይገኛሉ

የባለአደራ ምክር ቤቱ አመራሮች በቢሮ ስብሰባ አድርገው ሲወጡ የተወሰኑ ሰዎች ከበባ አድርገው ጉዳት ሊያደርሱባቸው እንደሞከሩ ተሰምቷል።

ከበባ ካደረጉባቸው መካከል አንድ ሰው በፖሊስ አስይዘው አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ውስጥ ይገኛሉ። ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የተያዘው ሰው ምርመራ እንዲደረግበት እየጠየቀ እንደሆነና ፖሊስ ግን ሰውየውን ሊለቀው እንደሆነ ታውቋል።

እነ እስክንድር ነጋ ሁኔታውን ለፖሊስ እያስረዱ ነው። ከበባ አድርገው ጉዳት ሊያደርሱብን ነበር ካሏቸው መካከል የተያዘው ላይ ፖሊስ ምርመራ እንዲያደርግ እየጠየቁ ነው። ሰዎቹ የተናበቡና ከፖሊስ እገዛ ያላቸው እንደሆኑ ለመጠርጠር በቂ ማሳያ አለን ብለዋል እነ እስክንድር። ከበባ ካደረጉት መካከል አንዱ ከመያዙ ውጭ ሌሎች መኪና ይዟቸው ተሰውሯል።

Re: ሰበር ዜና - እነ እስክንድር ነጋ ከጥቃት ተርፈው አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ይገኛሉ

Posted: 03 Nov 2019, 01:54
by MINILIK SALSAWI