Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum

Revelations
Senior Member+
Posts: 33738
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: ዶዶላ ላይ የተፈጸመው ዘግናኝ ጭፍጨፋ በተጎጅዎች አንደበት። [VIDEO]

Post by Revelations » 30 Oct 2019, 12:30

የክርስቲያኖች ሰቆቃ በሐረርጌ
_____________________

ሰሞኑን በምሥራቅ ሐረርጌ በባሌ በምዕራብ አርሲ እና አዲስ አበባ አፍንጫ ሥር ደግሞ በወለቴ ብሔርን እና ሃይማኖትን መሠረት ያደረገ ዘግናኝ ጭፍጨፋ ከ70 በላይ ኢትዮጵያውያን በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል:: ንብረታቸው ተቃጥሏ:: በግድ ሃይማኖት ቀይረዋ::

በርካታ "ሚዲያዎች" ግን ጉዳዩን እንዳላየ እና እንዳልሰማ ሆነው ወይ አልፈውታል ወይ "በአንዳንድ አካባቢዎች በተከሰቱ ግጭቶች" የሚል ዲፕሎማሲያዊ ገለጻ አለዝበው ልአልፈውታል:

ጉዳዩን በቅርበት ስንከታተል ለሰነበትን ዜጎች ግን የሆነውን ስለምናውቅ በመሸፋፈን የሚታለፍ ሳይሆን ኢትዮጵያ በታሪኳ ካየቻቸው ወደር አልባ ጭካኔዎች ተርታ የምንመዘግበው ታሪክ ሲሆን ሃዘኑም አጥንት ድረስ ዘልቆ የሚሰማ ጥልቅ ነው::

በምሥራቅ ሐረርጌ የሆነውን በቦታው የሚገኙ እና ከሜንጫ ስለት ያመለጡ ኢትዮጵያውያን በቁቤ የሚከተለውን ዘገባ ልከውልኛል:: ትርጉሙ እንደወርደ እነሆ !
_____________________

ጎሮ ጉቱ ወረዳ

ይህ ወረዳ 28 ቀበሌዎች እና 2 የከተማ አስተዳደር የለው ሲሆን በሙሉ ወረዳው የሆነው ጥፋት ተመሳሳይ ነው፡፡ ይህም ተግባር ፡-

የክርስቲያኖችን ንብረት ሙሉ በሙሉ ማውደም እና የተመቻቸ አጋጣሚ ሲያገኙ ነብስ ማጥፋት ነው፡፡ እኔም አንድ ቤተክርስቲያን ውስጥ ስውር ቦታ ላይ በመሆን በዓይኔ በብረቱ ያየሁትንና ከገጠር በስልክ ያገኘሁተን ጥቂተ መረጃዎችን እንደዚህ ጻፍኩ፡፡

1. የወረዳዋ ከተማ ካራ ሚሌ

ነፍስና ንብረትን በማጥፋት ላይ ያተኮሩ ሲሆን ነፍስ ማጥፋት ሳይሳካላቸው ስቀር ንብረት አውድመዋል፡፡ ያቃጠሏቸው ቤቶች ብዙ ንብረት ያላቸው ባለሃብቶች ሲሆኑ ሁሉም ክርስቲያኖች ነበሩ፡፡ ለምሳሌ፡-

ሀ. የባለሃብት አስፋው ተደሰ ቤት
ለ. የባለሃብት መኮንን ወልዱ ሆቴልን በማቃጠል የመኖሪያ ቤቱን ዘርፈዋል፡፡
ሐ. ጌታቸው ሲዳ
መ. ምህረት ጋሻው
ረ. ተግስት ውብየ፤ ሆቴልና የቤት ዕቃ፤
ሰ. አብርሃ እሸቴ
ሸ. ትንሳኤ ማሞ
ቀ. ሒሩት
በ. አሸቱ ተራ
ተ. ስንታየሁ ውበየ
ቸ. ምህት ቤትና ንብረታቸው የወደማባቸው ናቸው፡፡

(በዚህ ከተማ ውስጥ የደረሰው ውድመት ይህ ብቻ ሳይሆን በዐይኔ ዐይቼ ያስታወስኩትን ብቻ ነው የፃኩት)'

2. ባሮዳ ከተማ፡-


በዚህ ከተማ ውስጥ ሕይወት ጠፍቷል፡፡ ብዙ ንብረት ያለውና ጠንካራ ክርስቲያን የሆነው አቶ ዳመና ፤ የዳመና ወንድምና ሚስቱን እንደ ሽንኩርት ከትፈው ገድለዋቸዋል፡፡

"አስከሬኑን እናቃጥለዋለን እንጂ በኛ መሬት ላይ አይቀበርም" በማለት አስክሬኑን ደብቀው የፌደራል ፖሊስ በ3ኛው ቀን ማታ በቅዱስ ጊዮርጊስ ፅቤተክርስቲያን እዛው ባሮደ ውስጥ ቀብሮታል፡፡

በአጠቃላይ ባሮዳ ውስጥ የክርስቲያኖችን ሃብት ንብረት አውድመዋል፡፡ ቀሪውን ደግሞ ዘርፈዋል፡፡ በተጨማሪም ከነዚህ ሁለት ከተሞች ክርቲያኖች ወደ ሌላ ቦታ ተሰደዋል፡፡ በተለይ ባሮዳ ከተማ ሙሉ
በሙሉ ክርስቲያኖች ተሰደዋል፡፡

3. ገጠር፡-

በተመሳሳይ ሁኔታ የከርስቲያኖች ቤትና ንብረት በማቃጠልና በመዝረፍ አውድመዋል፡፡ ይህም ማገገም እንዳይችሉ ታስቦ የተደረገ ነው፡፡ ሁሉንም የገጠር አከባቢ ውስጥ ያለውን ችግር ለመረዳት እኔም ከሚፈለጉት አካላት አንዱ ስለሆንኩኝ ያጣሯቸው ጥቂቶቹ እነዚ ናቸው፡-

- መንዲሳ ቀበሌ

(ጎጥ አንድ ውስጥ)
ሀ. ጋንጌሶ

1. ሙሉ በሙሉ ንብረታቸው የተቃጠለባቸው፡-
- ዘውዱ ወንድሙ
- ብስራት መኮንን
- ፈቃዱ መኮንን
- መኮንን በለጠ

2. የተዘረፉና የተቃጠለባቸው

- ጌትነት እንዳለው
- እንዳለው አየለ
- አክሊሌ በለጠ
- ሺመልስ በለጠ
- ሙሉ ግዛው
- ብሬ ግዛው
- ባየ ደርቤ
- ሺመልስ በላይ
- ዘነባ በላይ
- ጌታሁን ማሞ
- ስዩም በላይ
- ኃይሉ ገበየው
- ደጀኔ ተፈራ
- አየናቸው ጋሸው
- ሚሊዮን ታፈሰ
- ጥጉ ጥላሁን (2 ሶላር)
- ጣሰው ካሳየ
- ዘለማየሁ ደምሴ
- አበበ ማሞ
- ዘወቀ ጸጋ
- ፀጋ አሸቱ(7,000 ጥሬ ብር ፤ሁለት ትላልቅ ሶላር፤ ሁለት ሬድዮ)
- ደረጀ ፀጋ(ሙሉ የቤት ንብረትና 18,000 ጥሬ ብር )
- ሶሎሞን ታፈሰ

ለ. መንዲሳ ከራቡ ሰፈር

(በግድ የሰለሙ ንብረታቸው የተዘረፈ)

- ስንታየሁ አለማየሁ 5 ቤተሰብ ጋር፣ ካሰለሙ በኋላ የወጣለት ስም ኦባሳ የሚል ሲሆን ለባለቤቱ ደግሞ ጫለቱ የሚል ነው፡፡
- ተፈራሽ ፍቃዱ 3 ቤተሰባ ጋር በግድ እምነታቸውን የቀየሩ (ለእኚህ እናት የወጣላቸው ስም ኣዮ ፋጡማ የሚል ነው)
- ታየ አለማየሁ 7 ቤተሰባ ጋር፤
- ስንታየሁ ሽኔ 4 ቤተሰብ ጋር፤
- እንዳለ ከተማ 3ቤተሰብ ጋር፤
- በለጠ አስራት 7ቤተሰብ ጋር፤
- ግርማ አስራት 6 ቤተሰብ፤
- አሽኔ ሞልቶት 3 ቤተሰብ፤

ቤታቸውና ንብረቴቸው የተቃጠለባቸው


- አለማየሁ ወንድፍራው 2 ቤት
- መላኩ ብርሃኔ
- አደፍርስ ግርማ ናቸው፡፡

(ማሳሰቢያ ፡- ይህ መንዲሳ ዴራ ጎጥ የሚባል አን ድ ሰፈር ወይም ጎጥ ነው፡፡
ጋንጌሶ ውስጥ የቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ተቃጥሏል፡፡)


ሐ. ቡራክሳ ገጠር
ቤት እና ንብረታቸው የወደመባቸው ክርስቲያኖች፡-

- በላይ መኮንን
- ተሸመ አፈወርቅ
- ግርማ አሥራት
- መኮንን ስዩም
- ተረፈ
- ዮናስ ናቸው፡፡

በነገራችን ላይ የጻፍኩልህ የተከሰተውን ችግር በሙሉ ሳይሆን በተቻለኝ መጠን ያገኘሁትን እና የዐይን ምሥክር የሆንኩበትን ብቻ ነው፡፡ በዚህ ወቅት መረጃዎችን መሰብሰብ አስቸጋሪና ለሞት ጭምር የሚያጋልጥ አደገኛ ሥራ ነው፡፡
_____________________

ይህንን ዝርዝር ስታነቡ ኢትዮጵያ ለምን እንዳለቀሰች ይገባሃል:: የአባቶችህ እንባን ምንክንያቱን ትረዳለህ:: የሚራራ አንጀት ከሌለህ ባዘኑት እና በሚያለቅሱት አታሹፍ:: የምጣዱ ሳለ የእንቅቡ ተንጣጣ እንደሚባለው የተቃጠሉት እና የታረዱት እያሉ "ለምን ግፋችን ተነገረብን?" በሚል ግብዝነት የሚወራጩ ድኩማን ትንሽ እፍረት ቢኖራችሁ አፍ አለን ብላችሁ አትናገሩም ነበር:: የሰማእታቱ ደም ይፋረዳችሁ!

Revelations
Senior Member+
Posts: 33738
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: ዶዶላ ላይ የተፈጸመው ዘግናኝ ጭፍጨፋ በተጎጅዎች አንደበት። [VIDEO]

Post by Revelations » 30 Oct 2019, 13:14

Please wait, video is loading...

Post Reply