Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abaymado
Member
Posts: 4208
Joined: 27 Sep 2017, 21:56

የአቶ ዩሐንስ ቧ ያለው አስደናቂ ንግግር! “ብአዴን በምንም መልኩ የአማራን ሕዝብ እያስጨረሰ አይቀጥልም::” “የተሸከምነው የትግስታችን ቀንበር ከብዶናል::”

Post by Abaymado » 29 Oct 2019, 11:00


ከሰሜን ሸዋ ነዋሪዎች ጋር ያደረጉት ንግግር ዋና ዋናዎቹ:

1. የተሸከምነው የትግስታችን ቀንበር ከብዶናል:: ይህ መታወቅ አለበት::

2. በሐረር: በድሬዳዋ : በአዲስአበባና በተለያዩ ኦሮምያ አካባቢዎች በንፁሃን ላይ የተፈፀመው ጥቃት : የአማራን ሕዝብ አስተዋይነትና ትዕግስት ለመስረቅ የሚደረግ ጥረት ነው::

3. ያለፈው ስርዓት ብዙ ነገር ሰርቆናል: መሬት : ብር :ልማት :ፕሮጀክቶችን : ማተርያሎችን: ይህ ሁሉ ከሁሉም ኢትዮጵያውያን የተሰረቀ ነው:::

4. ያለፈው ስርዓት የአማራን ሕዝብ ከሁሉም በተለየ መልኩ የአማራን ሕዝብ ቁጥር ሰርቆበታል:: ስርዓቱ ያልሰረቀበት ጀግንነቱን: ሞራሉን ወኔውን : መተሳሰሩን :አንድነቱን:ክልሉንና ሀገር ወዳደነቱን ነው::

5. ፅንፈኞች የሚፈፅሙት ሞልቶ እየፈሰሰ ነው:: የዚህ ሁሉ ግፍ መቀጠል ምክንያቱ የቀረንን ሀብት ለመስረቅ ነው ::

6. ይቺን አገር የሰላምና የፍቅር አገር እናርግ በሚል እንጂ ዝምታው ከሌላው በማነስ አይደለም::

7. አገር ሲፈርስ አማራ ብቻ ይጎዳል ብሎ የምጃጃል ካለ አማራ ከማንም አያንስም::

8. ብአዴን በምንም መልኩ የአማራን ሕዝብ እያስጨረሰ አይቀጥልም::

9. እኛ የምንፈልገው ተላላኪዎችንና እንጨት ይዘው የሚዞሩትን አይደለም : ላኪውን ነው::


Post Reply